ወልቂጤ ከተማ

ያለፉትን ሁለት ዓመታት ከሰራተኞቹ ጋር ያሳለፈው የመሐል ተከላካይ ከክለቡ ጋር በስምምነት ተለያይቷል። 2012 ላይ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ዋናው የሀገሪቱ የሊግ እርከን ያደገው ወልቂጤ ከተማ ባደገበት ዓመት የመሐል ተከላካዩን ቶማስ ስምረቱ ከኢትዮጵያ ቡና አስፈርሞ እንደነበር ይታወሳል። ተከላካዩ በኮቪድ-19 ምክንያት የተሰረዘውን ግማሽ እና የ2013 የውድድር ዓመትን በክለቡ በመቆየት ግልጋሎት ሲሰጥ ነበር።ዝርዝር

👉 “…ቅፅ እና ማኅተም ተሰጥቶት ያንን ላልተገባ አላማ ሲያውል ተደርሶበት ከኃላፊነት የተነሳ ግለሰብ ነው” 👉 “ለተጫዋቾች የሚጠጡበት ቦታ ተመቻችቶ አንድ ወር ሙሉ መጠጥ ቤት እየጠጡ እንዲያመሹ ሲደረግ ነበር” 👉 “ከ80% በላይ የምንፈልጋቸውን ተጫዋችን ይዘናል” የወልቂጤ ከተማ ዙርያ እየተነሱ ባሉ ጉዳዮችን በማስመልከት ባስነበብነው ፅሁፍ ዙሪያ የክለቡ ሥራ አስኪያጅ ተከታዩን ማብራሪያ ሰጥተዋል።ዝርዝር

በክረምቱ መነጋገርያ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል የፕሪምየር ሊጉ ተሳታፊው ወልቂጤ ከተማ ደጋፊዎች በክለቡ ላይ ያነሱት ተቃውሞ እና ጥያቄ ይጠቀሳል። ይህ ጉዳይ ምንድነው ስንል ጠይቀን ተከታዩን ፅሁፍ አሰናድተናል። በ2012 ወደ ፕሪምየር ሊግ ያደጉት ሠራተኞቹ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በፕሪምየር ሊጉ የመጀመሪያ ሙሉ የውድድር ዘመናቸው መልካም አጀማመር ቢያደርጉም በተለይ ሁለተኛው የውድድር አጋማሽ ያጋጠመውን የውጤትዝርዝር

በዝውውር መስኮቱ እንቅስቃሴ ሳያደርግ የቆየው ወልቂጤ ከተማ ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል። የውጪ ተጫዋችም ከፈረሙት መካከል ይገኝበታል።  ለቀጣዩ የውድድር ዓመት የተቀዛቀዘ እንቅስቃሴ ያደረገውና ይህን ተከትሎ በደጋፊዎች ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ የገጠመው ክለቡ ከዚህ ቀደም የአሰልጣኙን ውል ማራዘም እና ከወጣት ቡድኑ ተጫዋቾች ለማሳደግ ላይ ብቻ ተገድቦ መቆየቱ የሚታወስ ነው። አሁን ደግሞ ለማስፈረም እንደተስማሙዝርዝር

ወልቂጤ ከተማ ሦስት ግቦችን አስቆጥሮ ኮልፌ ቀራኒዮን ከረታበት ጨዋታ በመቀጠል ሁለቱም አሰልጣኞች የድህረ ጨዋታ ሀሳባቸውን ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል። ጳውሎስ ጌታቸው – ወልቂጤ ከተማ ስለጨዋታው “ጨዋታው እንዳያችሁት ከባድ ነበር፡፡ምክንያቱም ሁለቱም ቡድኖች ኳስን ይዘው የሚጫወቱ ቡድኖች ስለሆኑ። በአጠቃላይ ግን ከጨዋታ በስተጀርባ እዚህ ድረስ የመጡ ደጋፊዎቻችን ማመስገን እፈልጋለሁ። ምክንያቱም ከፕሪምየር ሊግ ወጥተናል ብለውዝርዝር

የትግራይ ክልል ክለቦችን ለመተካት የሚደረገው የማሟያ የመጨረሻ ጨዋታ በተመሳሳይ ሰዓት ከተደረጉ እና በሀዋሳ ሰው ሰራሽ ሜዳ ላይ በተከወነ መርሐግብር ወልቂጤ ከተማ ኮልፌ ቀራኒዮን 3-0 በመርታት አዳማን ተከትሎ ማለፉን አረጋግጧል፡፡ በጅማ አባ ጅፋር ተረተው ወደ ዛሬው ጨዋታ የመጡት ኮልፌ ቀራኒዮዎች በአንድ ተጫዋች ላይ ብቻ ለውጥ አድርገዋል፡፡ በቅያሬውም ሀቢብ ከሚል ወጥቶ ክንዱዝርዝር

በተመሳሳይ ሰዓት ከሚደረጉ ጨዋታዎች አንዱ የሆነው እና በሰው ሰራሹ ሜዳ የሚከወነው ወደ ፕሪምየር ሊጉ የመግባት ዕድል ባላቸው ሁለት ቡድኖች መካከል የሚደረገውን ይህን ጨዋታ ወቅታዊ መረጃዎችን አጠናቅረናል፡፡ በአንፃሩ በጅማ አባ ጅፋር ሽንፈት አስተናግደው ወደ ዛሬው መርሐግብር ብቅ ያሉት የአሰልጣኝ መሀመድኑር ንማዎቹ ኮልፌ ቀራኒዮች ከባለፈው ጨዋታ ተሰላፊዎች ውስጥ ሀቢብ ከማልን በክንዱ ባየልኝዝርዝር

ወልቂጤ የዲሲፕሊን ጥሰት ፈፅመዋል በማለት ከወራት በፊት ከክለቡ አግልሏቸው የቆዩቱን ሦስት ተጫዋቾች ወደ ክለቡ መልሷቸዋል። ፍሬው ሰለሞን ፣ ይበልጣል ሽባባው እና አዳነ በላይነህ “አላስፈላጊ ቦታ ተገኝተዋል” በማለት ወልቂጤ ከወራት በፊት ከቡድኑ ካምፕ እንዲገለሉ መወሰኑ ይታወሳል። ወልቂጤዎች በቅርቡ እንደ አማራጭ በቀረበው የዙር ውድድር ዳግም በሊጉ የመቆየት ተስፋቸውን ለማለምለም በአዲሱ አሰልጣኛቸው ጳውሎስዝርዝር

ከፍተኛ ሊጉ መውረዱን ያረጋገጠ ቢሆንም በቅርቡ እንደ አማራጭ በቀረበው የዙር ውድድር ላይ ለመሳተፍ ዕድል ያገኘው ወልቂጤ ከተማ የዓመቱ አራተኛ አሰልጣኝ ወደ ክለቡ አምጥቷል፡፡ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ አጀማመሩ ያማረ ቢመስልም በመጨረሻ ግን ከሊጉ መውረዱን ያረጋገጠው ወልቂጤ በአሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው እየተመራ ዓመቱን ቢጀምርም አሰልጣኙ ባጋጠማቸው ህመም ምክንያት ከክለቡ ጋር የተለያዩ ይመሰላል፡፡ ክለቡምዝርዝር

የከሰዓቱ ጨዋታ ከተጠናቀቀ በኋላ የአሰልጣኞች እና የሱፐር ስፖርት ቆይታ ይህን መሳይ ነበር። አሰልጣኝ ፍራንክ ናታል – ቅዱስ ጊዮርጊስ ስለጨዋታው ብዙ ዕድሎች የፈጠርንበት ጨዋታ ነበር። በመጀመሪያው አጋማሽ ርቀን መሄድ ነበረብን። ያን ባለማድረጋችን ጨዋታውን ራሳችን ላይ አክብደናል። ነገር ግን ወደ ጨዋታው ለመመለስ እና ግብ ለማስቆጠር ተጫዋቾች ያሳዩት መነሳሳት አስደሳች ነበር። ያም በመጨረሻዝርዝር