Soccer Ethiopia

አንደኛ ሊግ

የስታዲየሞች ግምገማ ዛሬ ተጠናቀቀ

በተዋቀረ ሦስት ኮሚቴዎች አማካኝነት በየሀገሪቱ በተመረጡ ስታዲየሞች እና መሠረተ ልማቶች ዙሪያ ሲደረግ የነበረው ግምገማ ዛሬ ተጠናቋል፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ሌሎች አካላትንም በአባልነት አካቶ በተዋቀሩ ሦስት ኮሚቴዎች አማካኝነት ውድድሮች በድጋሚ እንዲጀምሩ እና በተመረጡ ሜዳዎች ውድድሮች እንዲደረጉ ቅድመ ግምገማ ላለፉት ስምንት ቀናት ሲደረግ ቆይቶ ዛሬ ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡ ኮሚቴዎቹ ተዟዙረው አስራ ሰባት ሜዳዎች […]

የታሰሩት ተጫዋቾች ጉዳይ…

የሾኔ ባድዋቾ ከተማ ተጫዋቾች ደመወዝ ለመጠየቅ ወደ ቢሮ በሚሄዱበት ሰዓት ለእስር መዳረጋቸው ከሰሞኑ በአብይ ርዕስነት በበርካቶች ዘንድ ትኩረትን ያገኘ ዜና ሆኗል። በሣምንቱ አጋማሽ ነበር አስር ቡድኖችን አቅፎ በሚገኘው የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ ምድብ ረ ላይ በዘጠኝ ነጥቦች በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ የሚገኘው የሾኔ ባድዋቾ ከተማ ተጫዋቾች የአምስት ወራት ደመወዝ አልተከፈለንም በሚል በተደጋጋሚ ለክለቡ በደብዳቤ ቅሬታ ቢያቀርቡም […]

የ2011 ኮከቦች የገንዘብ ሽልማት በዚህ ሳምንት ተግባራዊ ይሆናል ተባለ

ተደጋጋሚ ቅሬታ በተሸላሚዎቹ ዘንድ ሲነሳበት የቆየው የ2011 የሊጎቹ ኮከቦች ሽልማት ከወራቶች መጓተት በኃላ ከዚህ ሳምንት ጀምሮ የገንዘብ ሽልማቱ መከፈል ይጀምራል፡፡ በ2011 በወንዶች ከአንደኛ ሊግ እስከ ፕሪምየር ሊግ በሴቶች ደግሞ የፕሪምየር ሊግ እና ሁለተኛ ዲቪዚዮን፣ በተጨማሪም ከ20 ዓመት በታች ወንዶች ፕሪምየር ሊግ ላይ በከፍተኛ ግብ አግቢነት፣ ኮከብ ተጫዋችነት፣ ኮከብ ግብ ጠባቂነት፣ ኮከብ አሰልጣኝነት፣ ምስጉን ዋና እና […]

የ2012 የኢትዮጵያ ሊጎች ሙሉ ለሙሉ እንዲሰረዙ ተደረገ

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረጉ የሊግ ውድድሮች ሙሉ ለሙሉ እንዲሰረዝ ተደረገ። በተጨማሪም በቀጣይ ዓመት ኢትዮጵያን በአህጉራዊ ውድድሮች የሚወክል ክለብ እንዳይኖር ተደርጓል። በታህሳስ ወር በቻይና ሁቤይ ከተማ በተከሰተው ኮሮና ቫይረስ ምክንያት በዓለም ላይ የሚደረጉ የሊግ ውድድሮች ቆመዋል። ሊጎችን የሚያስተዳድሩ አካላትም የሊጎቻቸውን ቀጣይ እጣ ፈንታ በማጤን ውሳኔዎችን እየወሰኑ ይገኛሉ። በሃገራችንም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ሊጉን ከሚያስተዳድረው […]

ወጣቱ ግብ ጠባቂ የተጋጣሚን ተጫዋች ሕይወት አድኗል

የሐውዜኑ ግብ ጠባቂ ናኦድ ገብረእግዚአብሔር የምላስ መዋጥ አደጋ የደረሰበት የአዲስ አበባ ፖሊስ ተጫዋችን ሕይወት አትርፏል። ከቀናት በፊት በአንደኛ ሊግ ጨዋታዎች አንዱ በነበረው የሐውዜን እና የአዲስ አበባ ፖሊስ አስደንጋጭ ክስተት አስተናግዶ ነበር። በጨዋታው እንቅስቃሴ ውስጥ አንድ የአዲስ አበባ ፖሊስ ተጫዋች ከተጋጣሚ አጥቂ ጋር ተጋጭቶ ራሱን በመሳቱ የምላስ መንሸራተት እና የመተንፈሻ ትቦ መዘጋት አጋጥሞት ነበር። ሆኖም የተቃራኒ […]

“ከሁኔታው በኋላ ህዝቡ ጥሩ ትብብር ባያደርግልን በሕይወት የመቆየቴ ነገርም ጥያቄ ምልክት ውስጥ ነበር” ኤፍሬም ኪሮስ

ባለፈው ዓመት ሚያዚያ ወር ላይ የዋልታ ፖሊስ ትግራይ ተጫዋቾች ጨዋታ አድርገው ወደ መቐለ በሚመለሱበት ወቅት ባልታወቁ ታጣቂዎች በተተኮሰ ጥይት ከባድ ጉዳት ደርሶበት የነበረውና ከበድ ያለ የመተንፈሻ ቀዶ ጥገና ያደረገው ኤፍሬም ኪሮስ ከከባዱ ጉዳት በማገገም ወደ ሜዳ ተመልሶ በመጀመርያዎቹ ሁለት ጨዋታዎች ሦስት ግቦች አስቆጥሯል። ወደ እግር ኳስ ለመመለስ ይቅርና በሕይወት ለመቆየትም ከባድ የሆነ ጉዳት የደረሰበት ይህ […]

የኦሮሚያ ዋንጫ በገላን ከተማ አሸናፊነት ተጠናቋል

ለቀናት በቢሾፍቱ ከተማ በአምስት ቡድኖች መካከል ሲካሄድ የቆየው የኦሮሚያ ዋንጫ ዛሬ ፍፃሜውን ሲያገኝ ገላን ከተማ የውድድሩ አሸናፊ ሆኗል። የኦሮሚያ ዳኞችና ኮሚሽነሮች ማኅበር ከኦሮሚያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር በተዘጋጀው በዚህ ውድድር አምስት ቡድኖች ተሳትፈዋል። ዛሬ ፍፃሜውን አግኝቶ የተሻለ ነጥብ በመሰብሰብ ገላን ከተማ የውድድሩ አጠቃላይ አሸናፊ ሆኖ አጠናቋል። ረቡዕ ኀዳር 24 ቀን 2012 ሞጆ ከተማ 0–2 ገላን […]

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ኮከቦች ምርጫ ዛሬ ምሽት ተካሄደ

በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ስር በተካሄዱ ስድስት የውድድር ዓይነቶች የ2011 ኮከቦች የሽልማት መርሃግብር ዛሬ ምሽቱን በካፒታል ሆቴልና ስፓ ተካሂዷል። የ2011 ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተጫዋቾችና አሰልጣኞች እጩዎች ከነበረባቸው ጨዋታ መልስ በመርሃግብሩ እንዲታደሙ በማሰብ ከተያዘለት ሰዓት እጅጉን ዘግይቶ በጀመረው በዚሁ መርሃግብር በፌደሪሽኑ ስር በሚካሄዱ ውድድሮች በዓመቱ የተሻለ አፈፃፀም የነበራቸው ተጫዋቾች አሰልጣኞችና ዳኞች እውቅና የተሰጠ ሲሆን ዘንድሮ በተለየ መልኩ […]

ነገ የሚካሄደው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ኮከቦች ምርጫ እጩዎች ታውቀዋል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በ2011 ባካሄዳቸው 6 ሊጎች ላይ ጎልተው የወጡ ተጫዋቾች እና የተለያዩ የእግርኳስ ባለሙያዎችን ቅዳሜ ኅዳር 27 ቀን 2012 በካፒታል ሆቴል ከምሽቱ 12፡00 በሚደረግ ሥነ-ሥርዓት ለመሸለም ተዘጋጅቷል። የሽልማቶቹ ዘርፍ ኮከብ አሠልጣኝ፣ ኮከብ ተጫዋች፣ ኮከብ ግብ አስቆጣሪ፣ ኮከብ ግብ ጠባቂ እንዲሁም ምስጉን ዋና ዳኛ እና ምስጉን ረዳት ዳኛ ሲሆኑ በተጨማሪም የሕይወት ዘመን ተሸላሚ እና […]

ኦሮሚያ ዋንጫ ዛሬ ተጀመረ

በአምስት ቡድኖች መካከል በቢሾፍቱ ከተማ የሚካሄደው የኦሮሚያ ከፍተኛ ሊግ እና አንደኛ ሊግ ቡድኖች የሚካፈሉበት ውድደር ዛሬ ተጀምሯል። የኦሮሚያ ዳኞችና ኮሚሽነሮች ማኀበር ከኦሮሚያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር በተዘጋጀው በዚህ ውድድር አምስት ቡድኖች የሚካፈሉ ይሆናል። ገላን ከተማ፣ ቢሾፍቱ ከተማ፣ ባቱ ከተማ፣ ዱከም ከተማ እና ሞጆ ከተማ ተሳታፊ ቡድኖች ናቸው። የዛሬ ጨዋታ ውጤት ቢሾፍቱ ከተማ 1–0 ሞጆ ከተማ […]

ሶከር ኢትዮጵያ

ሶከር ኢትዮጵያ በ ‘አብርሀም ገ/ማርያም የማስታወቂያ ድርጅት’ ስር የሚሰራ ድረገፅ ሲሆን በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በሚያተኩሩ ዜናዎች፣ ቁጥራዊ መረጃዎች፣ ታሪኮች፣ ጥልቅ ዘገባዎች፣ አስተያየቶች እና ትንታኔዎች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

ዘርፍ

ማኅደር

top