አንደኛ ሊግ (Page 2)

ሊጀመሩ የሳምንታት እድሜ የቀራቸው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግም ሆነ ሌሎች የውስጥ ውድድሮች በሙሉ አቅማቸው በተባሉበት ቀናት ይጀምሩ ይሆን? የኢትዮጵያ የሊግ ውድድሮች የሚጀምሩበት ቀናት ይፋ መደረጋቸውን ተከትሎ በሁሉም ወገን የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ይገኛል። በተለይ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጥቂት ክለቦች ካልሆነ በቀር አብዛኛዎቹ ክለቦች የቅድመ ዝግጅት ሥራቸውን እያከናወኑ ይገኛል። አወዳዳሪውም አካል የዕጣ ማውጣትዝርዝር

የ2013 የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ ውድድር በታኅሣሥ ወር እንደሚጀመር ተገለፀ። የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በስሩ ከሚያካሂዳቸው ውድድሮች መካከል አንዱ የሆነው የሀገሪቱ ሦስተኛ የሊግ እርከን አንደኛ ሊግ የ2013 መርሀ ግብሩን በተመረጡ ሜዳዎች በስድስት ምድብ ተከፍሎ በሀምሳ አምስት ክለቦች መካከል እንደሚካሄድ ይጠበቃል፡፡ የዘንድሮው የአንደኛ ሊግ ውድድር በኅዳር ወር መጨረሻ ከአጠቃላይ ክለቦቹ ጋር ውይይት እናዝርዝር

በተዋቀረ ሦስት ኮሚቴዎች አማካኝነት በየሀገሪቱ በተመረጡ ስታዲየሞች እና መሠረተ ልማቶች ዙሪያ ሲደረግ የነበረው ግምገማ ዛሬ ተጠናቋል፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ሌሎች አካላትንም በአባልነት አካቶ በተዋቀሩ ሦስት ኮሚቴዎች አማካኝነት ውድድሮች በድጋሚ እንዲጀምሩ እና በተመረጡ ሜዳዎች ውድድሮች እንዲደረጉ ቅድመ ግምገማ ላለፉት ስምንት ቀናት ሲደረግ ቆይቶ ዛሬ ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡ዝርዝር

የሾኔ ባድዋቾ ከተማ ተጫዋቾች ደመወዝ ለመጠየቅ ወደ ቢሮ በሚሄዱበት ሰዓት ለእስር መዳረጋቸው ከሰሞኑ በአብይ ርዕስነት በበርካቶች ዘንድ ትኩረትን ያገኘ ዜና ሆኗል። በሣምንቱ አጋማሽ ነበር አስር ቡድኖችን አቅፎ በሚገኘው የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ ምድብ ረ ላይ በዘጠኝ ነጥቦች በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ የሚገኘው የሾኔ ባድዋቾ ከተማ ተጫዋቾች የአምስት ወራት ደመወዝ አልተከፈለንም በሚልዝርዝር

ተደጋጋሚ ቅሬታ በተሸላሚዎቹ ዘንድ ሲነሳበት የቆየው የ2011 የሊጎቹ ኮከቦች ሽልማት ከወራቶች መጓተት በኃላ ከዚህ ሳምንት ጀምሮ የገንዘብ ሽልማቱ መከፈል ይጀምራል፡፡ በ2011 በወንዶች ከአንደኛ ሊግ እስከ ፕሪምየር ሊግ በሴቶች ደግሞ የፕሪምየር ሊግ እና ሁለተኛ ዲቪዚዮን፣ በተጨማሪም ከ20 ዓመት በታች ወንዶች ፕሪምየር ሊግ ላይ በከፍተኛ ግብ አግቢነት፣ ኮከብ ተጫዋችነት፣ ኮከብ ግብ ጠባቂነት፣ዝርዝር

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረጉ የሊግ ውድድሮች ሙሉ ለሙሉ እንዲሰረዝ ተደረገ። በተጨማሪም በቀጣይ ዓመት ኢትዮጵያን በአህጉራዊ ውድድሮች የሚወክል ክለብ እንዳይኖር ተደርጓል። በታህሳስ ወር በቻይና ሁቤይ ከተማ በተከሰተው ኮሮና ቫይረስ ምክንያት በዓለም ላይ የሚደረጉ የሊግ ውድድሮች ቆመዋል። ሊጎችን የሚያስተዳድሩ አካላትም የሊጎቻቸውን ቀጣይ እጣ ፈንታ በማጤን ውሳኔዎችን እየወሰኑ ይገኛሉ። በሃገራችንም የኢትዮጵያዝርዝር

የሐውዜኑ ግብ ጠባቂ ናኦድ ገብረእግዚአብሔር የምላስ መዋጥ አደጋ የደረሰበት የአዲስ አበባ ፖሊስ ተጫዋችን ሕይወት አትርፏል። ከቀናት በፊት በአንደኛ ሊግ ጨዋታዎች አንዱ በነበረው የሐውዜን እና የአዲስ አበባ ፖሊስ አስደንጋጭ ክስተት አስተናግዶ ነበር። በጨዋታው እንቅስቃሴ ውስጥ አንድ የአዲስ አበባ ፖሊስ ተጫዋች ከተጋጣሚ አጥቂ ጋር ተጋጭቶ ራሱን በመሳቱ የምላስ መንሸራተት እና የመተንፈሻ ትቦዝርዝር

ባለፈው ዓመት ሚያዚያ ወር ላይ የዋልታ ፖሊስ ትግራይ ተጫዋቾች ጨዋታ አድርገው ወደ መቐለ በሚመለሱበት ወቅት ባልታወቁ ታጣቂዎች በተተኮሰ ጥይት ከባድ ጉዳት ደርሶበት የነበረውና ከበድ ያለ የመተንፈሻ ቀዶ ጥገና ያደረገው ኤፍሬም ኪሮስ ከከባዱ ጉዳት በማገገም ወደ ሜዳ ተመልሶ በመጀመርያዎቹ ሁለት ጨዋታዎች ሦስት ግቦች አስቆጥሯል። ወደ እግር ኳስ ለመመለስ ይቅርና በሕይወት ለመቆየትምዝርዝር

ለቀናት በቢሾፍቱ ከተማ በአምስት ቡድኖች መካከል ሲካሄድ የቆየው የኦሮሚያ ዋንጫ ዛሬ ፍፃሜውን ሲያገኝ ገላን ከተማ የውድድሩ አሸናፊ ሆኗል። የኦሮሚያ ዳኞችና ኮሚሽነሮች ማኅበር ከኦሮሚያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር በተዘጋጀው በዚህ ውድድር አምስት ቡድኖች ተሳትፈዋል። ዛሬ ፍፃሜውን አግኝቶ የተሻለ ነጥብ በመሰብሰብ ገላን ከተማ የውድድሩ አጠቃላይ አሸናፊ ሆኖ አጠናቋል። ረቡዕ ኀዳር 24 ቀንዝርዝር

በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ስር በተካሄዱ ስድስት የውድድር ዓይነቶች የ2011 ኮከቦች የሽልማት መርሃግብር ዛሬ ምሽቱን በካፒታል ሆቴልና ስፓ ተካሂዷል። የ2011 ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተጫዋቾችና አሰልጣኞች እጩዎች ከነበረባቸው ጨዋታ መልስ በመርሃግብሩ እንዲታደሙ በማሰብ ከተያዘለት ሰዓት እጅጉን ዘግይቶ በጀመረው በዚሁ መርሃግብር በፌደሪሽኑ ስር በሚካሄዱ ውድድሮች በዓመቱ የተሻለ አፈፃፀም የነበራቸው ተጫዋቾች አሰልጣኞችና ዳኞች እውቅናዝርዝር