Soccer Ethiopia

ፕሪምየር ሊግ

የሊግ ኩባንያው ሥራ አስኪያጅ ስለ ዘንድሮው ፕሪምየር ሊግ ዕጣፈንታ ይናገራሉ

ከወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ጋር ተያይዞ የ2013 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አስመልክቶ ከሼር ካምፓኒው ሥራ አስኪያጅ አቶ ክፍሌ ጋር የተደረገ ቆይታ። በትናንትናው ዘገባችን የዘንድሮ ዓመት የውድድር ዘመን በተለይ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሚጀመርበት ቀን የሳምንታት እድሜ በቀረበት በአሁኑ ሰዓት ባሳለፍነው ቅዳሜ የሊግ ካምፓኒው የዕጣ ማውጣት ሥነስርዓት በማካሄድ ቡድኖቹ ተጋጣሚዎችን እንዲያውቁ አድርጓል። ከዚህ ባለፈ አሁን ባለው ሀገራዊ ጉዳይ ጋር […]

የዲኤስቲቪ ባለሙያዎች ከክለቦች ጋር ውይይት እያደረጉ ሲሆን አዳዲስ መመሪያዎችም ቀርበዋል

የዲኤስቲቪ ባለሙያዎች ከሊግ ኩባንያው ጋር በጋራ በመሆን በብሮድካስት ደንብ አተገባበር ዙሪያ የክለብ የበላይ አመራሮችን እያወያየ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2013 የውድድር ዘመን ታህሳስ 3 ይጀመራል ተብሎ ቀነ ቀጠሮ ተይዞለታል፡፡ ሊጉ የኮቪድ 19 መመርያዎችን ተግባራዊ በማድረግ የመጀመሪያው ዙር ውድድሮችም በሦስት የሀገሪቱ ስታዲየሞች እንደሚከናወንም ከቀናት በፊት መገለፁ ይታወሳል፡፡ በሊግ ካምፓኒው የሚመራው የዘንድሮው የፕሪምየር ሊግ ውድድር ስያሜው ሆነ […]

የፕሪምየር ሊጉ የዕጣ ማውጣት መርሐ-ግብር ዛሬ ተከናውኗል

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር የ2013 የሊጉን ጨዋታዎች መርሐ-ግብር በደማቅ ሥነ-ስርዓት ዛሬ ከሰዓት አውጥቷል። ይጀመራል ተብሎ ከተነገረው 40 ደቂቃዎችን ዘግይቶ በተጀመረው በዚህ ሥነ-ስርዓት ላይ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ ጂራ፣ የፕሪምየር ሊጉ አክሲዮን ማኅበር የቦርድ ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ እንዲሁም የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች የነበሩት ሙሉጌታ ከበደ እና አሸናፊ በጋሻው ከክለብ ተወካዮች […]

ሊግ ኩባንያው አዲስ ውሳኔ አስተላልፏል

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር አዲስ ውሳኔ ላይ መድረሱን ይፋ አድርጓል። አንድ ዓመት የሞላው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር ከደቂቃዎች በፊት የ2013 ውድድር የዕጣ ማውጣት መርሐ-ግብር በካፒታል ሆቴል እና ስፓ አከናውኗል። የዕጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓቱ ከቀጥር በኋላ ከመደረጉ በፊትም ማኅበሩ ክለቦችን ዝግ በሆነ ስብሰባ በማስቀመጥ አወያይቷል። በስብሰባውም የማኅበሩ አባላት (ክለቦች) አንድ ውሳኔ ላይ መድረሳቸው ይፋ ሆኗል። […]

ሊግ ኩባንያው ከክለቦች ጋር ስብሰባ ተቀምጧል

የ2013 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዕጣ ማውጣት ሥነ ሥርዓት ዛሬ ይካሄዳል። ከዚህ መርሐግብር አስቀድሞ በአሁኑ ሰዓት የሊግ ኩባንያው በካፒታል ሆቴል ከክለቦች ጋር ስብሰባ ተቀምጧል። በትናንትናው ዕለት ረጅም ሰዓት የፈጀ የውስጥ ስብሰባውን ያደረገው የፕሪምየር ሊጉ አወዳዳሪ አካል በዋናነት ከዲኤስ ቲቪ ጋር ተያይዞ የመጣው የልዑካን ቡድን መስተካከል ባለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ዙርያ ሰፊ ውይይት አድርገዋል። ከዚህ በተጨማሪም ከዛሬው የዕጣት […]

የፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች የሚደረጉባቸው ቀሪ ስታዲየሞች ታወቁ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2013 የውድድር ዘመን የመጀመሪያው ዙር ጨዋታዎች ከአዲስ አበባ በመቀጠል የሚደረጉባቸው ስታዲየሞች ተለይተው ታውቀዋል፡፡ ሊጉ የፊታችን ቅዳሜ በሚወጣው ዕጣ ድልድል የመጀመሪያው ዙር ሙሉ መርሐ ግብር ይወጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ውድድሩ በታኅሣሥ ወር ሲጀመር ኩባንያው የኮቪድ 19 ወረርሺኝን ለመቀነስ እንዲረዳው ውድድሮቹ የሚደረጉበትን ስታዲየም ቁጥር በመቀነስ ከጤና ጥበቃ ጋር በጋራ ስታዲየሞችን ከገመገመ በኃላ ለመጀመሪያው ዙር ጨዋታዎች […]

የፕሪምየር ሊጉ የዕጣ ማውጣት ሥነ ስርዓት የሚደረግበት ቀን ታውቋል

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዕጣ ማውጣት ሥነ ስርዓት በቀጣይ ሳምንት ይደረጋል። የ2013 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ታኅሣሥ 3 በአዲስ አበባ ስታዲየም በሚደረጉ ጨዋታዎች በይፋ ይጀመራል፡፡ የዚህ ውድድር የዕጣ ማውጣት ሥነ ስርዓቱ በቀጣዩ ሳምንት ቅዳሜ ኅዳር 5 ከቀኑ 8:00 በአዲስ አበባ እንደሚወጣም የኩባንያው የፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ክፍሌ ሰይፈ በተለይ ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡ አቶ ክፍሌ “ቀደም ብለን ለማውጣት […]

የፕሪምየር ሊጉ ተጫዋቾች እና የኮሮና ቫይረስ  ጉዳይ…

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ የሆኑ ክለቦች ለተጫዋቾቻቸው የኮቪድ 19 ምርመራን እያደረጉ የሚገኝ ሲሆን በውጤቱም በቫይረሱ የተያዙ ተጫዋቾች እኛ አሰልጣኞች እየተገኙ ነው። የኢትዮጵያ ፕሪምየር ታኅሣሥ 3 እንደሚጀመር የሊግ ካምፓኒው ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ አስራ ስድስት ክለቦችን የሚያወዳድረው የሀገሪቱ ትልቁ የሊግ ዕርከን ካለፉት ዓመታት ዘንድሮ በይበልጥ በተሻለ ቁመና ላይ ሆኖ እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሼር ካምፓኒ በበላይነት […]

የፕሪምየር ሊጉ የዕጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓት የቀጥታ የቴሌቪዥን ሽፋን ያገኛል

ከዚህ ቀደም ከተለመደው የዕጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓት በተለየ መልኩ ይከናውናል የተባለለት መርሐ-ግብር በቴሌቪዢን እንደሚተላለፍ ተገለፀ። የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አ/ማ ባስቀመጠው የውድድር ፕሮቶኮል መሠረት ለክለቦች ቅድሚያ ትዕዛዝን ካስተላለፈ በኃላ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ታኅሣሥ 3 እንደሚጀመር ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ ዘንድሮ ሊጉ ካለፉት ዓመታት በተለየ ተመልካች በማይገኝበት እና በቀጣዩ ሳምንት ይፋ በሚደረጉ በተመረጡ ሜዳዎች ላይ ብቻ ይደረጋል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ […]

የፕሪምየር ሊጉ አክሲዮን ማኅበር አንደኛ መደበኛ ጉባዔ የዛሬ ውሎ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር ዛሬ በኢንተርኮንትኔንታል አዲስ ሆቴል ከክለብ ተወካዮች ጋር ጉባዔውን አካሂዷል። ጉባዔው ዋንኛ ትኩረቱን በ2013 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር ላይ ማድረጉ የታወቀ ሲሆን ሀያ ሶስት ገፆች ባሉት የውድድር ደንብ ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት ተደርጓል። የአክሲዮን ማኅበሩ ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ፣ የስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ኤልያስ ሽኩር እና የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ጂራ ንግግር […]

ሶከር ኢትዮጵያ

ሶከር ኢትዮጵያ በ ‘አብርሀም ገ/ማርያም የማስታወቂያ ድርጅት’ ስር የሚሰራ ድረገፅ ሲሆን በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በሚያተኩሩ ዜናዎች፣ ቁጥራዊ መረጃዎች፣ ታሪኮች፣ ጥልቅ ዘገባዎች፣ አስተያየቶች እና ትንታኔዎች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

ዘርፍ

ማኅደር

top