አዳማ ከተማ (Page 3)

ከደቂቃዎች በኋላ የሚጀምረው ጨዋታ ላይ የተደረጉ የአሰላለፍ ለውጦች ይህንን ይመስላሉ። አዳማ ከተማ ከወልቂጤ ከተማ ጋር ነጥብ ከተጋራበት ጨዋታ ሦስት ለውጦች አድርጓል። በዚህም ትዕግስቱ አበራ ፣ ደሳለኝ ደባሽ እና ማማዱ ኩሊባሊ ጨዋታውን ሲጀምሩ ደስታ ጌቻሞ ፣ በቃሉ ገነነ እና ያሬድ ብርሀኑ ከአሰላለፍ የወጡ ተጫዋቾች ናቸው። ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር ነጥብ የተጋሩት ፋሲልዝርዝር

የነገውን ቀዳሚ ጨዋታ በዳሰሳችን ለመመልከት ሞክረናል። በሰንጠረዡ አናት እና ግርጌ የሚገኙት ቡድኖችን የሚያገናኛው ጨዋታ ውጤት ለሁለቱም የተለያየ ትርጉም ይኖረዋል። ለፋሲል ከነማ ከተከታዩ ጋር ያለውን ልዩነት ይበልጥ አስፍቶ በጊዜ ዋንጫውን በእጁ ለማስገባት የሚያደርገው ጥረት ውስጥ የሚከወን ጨዋታ ነው። በተቃራኒው አዳማ ከተማ ቢያንስ ከበላዩ ያለው ጅማ አባ ጅፋር ጋር በነጥብ ለመስተካከል እናዝርዝር

ከ17ኛው ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ በኋላ ተጋጣሚ አሰልጣኞች ከሱፐር ስፖርት ጋር ተከታዩን ቆይታ አድርገዋል። አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ – ሲዳማ ቡና ስለጨዋታው ዋጋ የዚህ ጨዋታ ዋጋው በጣም ብዙ ነው። ከረጅም ጊዜ በኋላ ነው ወደ አሸናፊነት የተመለስነው። ለቡድናችን የስነ ልቦና የበላይነትን የሚጨምር ነው። ወደ አሸናፊነት መመለስ በራሱ አንድ ትልቅ እርምጃ ነው። ስለቡድኑ የጨዋታዝርዝር

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 17ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሐ ግብር አዳማ ከተማን የገጠመው ሲዳማ ቡና 3-0 በማሸነፍ ከአምስት ተከታታየሰ ሽንፈት በኋላ አገግሟል። ሲዳማ ቡናዎች ሊጉ ከእረፍት ከመቋረጡ በፊት ከነበረው ስብስብ ፍቅሩ ወዴሳ፣ አበባየሁ ዮሐንስ፣ ፈቱዲን ጀማል፣ ሽመልስ ተገኝ፣ ግርማ በቀለ እና ዮናስ ገረመውን በአዲስ ፈራሚው ፋቢያን ፋርኖሌ እንዲሁም አማኑኤል እንዳለ፣ ሰንደይዝርዝር

የ17ኛውን ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ የተመለከቱ ነጥቦችን እንዲህ አንስተናል። የኮቪድ ወረርሺኝ ጥላ ያጠላበት ይህ ጨዋታ ሁለት ተመሳሳይ ሁኔታ ላይ ያሉ ቡድኖችን ያገናኛል። ከውጤት አንፃር በወራጅ ቀጠናው ውስጥ ከመገኘታቸው ባለፈ አዳዲስ አሰልጣኞችን አምጥተው እና ተጫዋቾችን አስፈርመው ከመውረድ ለመትረፍ እያደረጉት ያለው ጥረትም ሲዳማ እና አዳማን ያመሳስላቸዋል። በባህር ዳሩ ውድድር አራት አዳዲስ ተጫዋቾችን የተጠቀመውዝርዝር

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ግርጌ ላይ የሚገኙት አዳማ ከተማዎች አራት የውጪ ዜጋ ተጫዋቾችን በዛሬው ዕለት አስፈርመዋል። በአሠልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ የሚመሩት አዳማ ከተማዎች በዘንድሮው የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ እያሳዩ ያሉት አቋም የወረደ ነው። ይህንን ተከትሎም ክለቡ በውድድር ዓመቱ የሠበሰባቸውን ነጥቦች ሁለት አሀዝ ማድረስ ሳይችል በደረጃ ሠንጠረዡ ግርጌ ላይ ተቀምጧል። አሠልጣኙም ክለቡን ከተረከቡዝርዝር

ከከሰዓቱ ጨዋታ በኋላ የተጋጣሚ አሰልጣኞች እና የሱፐር ስፖርት ቆይታ ይህንን መሳይ ነበር። አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ – አዳማ ከተማ ስለጨዋታው ጨዋታው ጥሩ ያልነበርንበት ነው። በተለይ ከዕረፍት በኋላ ብዙ ኳሶችን መጠቀም ይችሉ ነበር ፤ አልተጠቀሙም። ቡድኑ ላይ በተለይ በሥነ-ልቦናው በኩል በጣም ቶሎ ነው የሚወርዱት ልጆቹ። በዛ ላይ የአካል ብቃት ችግርም ይታያል። ብዙዝርዝር

በአዳማ እና ባህር ዳር ከተማ መካከል የተደረገው ጨዋታ በባህር ዳር አንድ ለምንም አሸናፊነት ተጠናቋል። አዳማ ከተማዎች በወላይታ ድቻ አንድ ለምንም ከተረቱበት ጨዋታ ሁለት ተጫዋቾችን ለውጠው ወደ ሜዳ ገብተዋል። በዚህም በጨዋታው አስደንጋጭ አደጋ አጋጥሞት የነበረውን ታሪክ ጌትነትን እና በቃሉ ገነነን በዳንኤል ተሾመ እና እዮብ ማቲዮስ ተክተዋል። አሠልጣኝ ፋሲል ተካልኝ በበኩላቸው የውድድርዝርዝር