ኢትዮጵያ ቡና

በአሠልጣኝ ካሣዬ አራጌ የሚመራው ኢትዮጵያ ቡና ልምድ ያለውን የመስመር ተከላካይ ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል። በዘንድሮ የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በ13 ነጥቦች ተበልጦ ዋንጫውን በፋሲል ከነማ ያጣው ኢትዮጵያ ቡና ክፍተቶቼ ባላቸው ቦታዎች ላይ ዝውውሮችን ማድረግ ጀምሯል። ከሁለት ቀናት በፊት የግብ ዘቡ በረከት አማረን ዝውውር ያጠናቀቀው ክለቡ ከሌሎች ተጫዋቾች ጋርም ድርድር ላይ መሆኑዝርዝር

በዝውውር ገበያው ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት ቡናማዎቹ የአንድ ዓመት ኮንትራት ካለው ተከላካያቸው ጋር በስምምነት ተለያይተዋል። በአሠልጣኝ ካሳዬ አራጌ የሚመራው ኢትዮጵያ ቡና በ2014 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እና በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎች ተጠናክሮ ለመቅረብ ከሰባት ቀናት በፊት በተከፈተው የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ላይ እየተሳተፈ ይገኛል። ቡድኑ አዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ ለመቀላቀል እንቅስቃሴዝርዝር

ተክለማርያም ሻንቆን ያጣው ኢትዮጵያ ቡና በምትኩ ተጫዋች በይፋ አስፈርሟል። ክለቡን የተቀላቀለው ተጫዋች የግብ ዘቡ በረከት አማረ ነው። በ2012 የውድድር ዘመን ከቡናማዎቹ ጋር ቆይቶ የነበረው በረከት ዓምና ወደ መቐለ 70 እንደርታ አምርቶ እንደነበር አይዘነጋም። በኮቪድ-19 ሊጉ እስከተቋረጠበት ጊዜ ድረስም በመቐለ ቆይቶ ዘንድሮ ግማሽ ዓመት ላይ ወደ ጅማ አባጅፋር አምርቶ መጨወት ቀጥሎዝርዝር

በዘንድሮ የውድድር ዓመት ጥሩ ብቃት ያሳየው አሥራት ቱንጆ ከቡናማዎቹ ጋር የመቀጠል እና አለመቀጠሉ ጉዳይ እየለየ መጥቷል። በ2009 ክረምት ጅማ አባ ጅፋርን ለቆ ኢትዮጵያ ቡናን የተቀላቀለው አሥራት ቱንጆ በቡናማው መለያ ራሱን እያጎለበት ለቡድኑ ወሳኝ ተጫዋች ሆኗል። በተለይ ለአሠልጣኝ ካሣዬ አራጌ አጨዋወት አመቺ የሆነው የመስመር ተከላካዩ ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ ስሙ ከተለያዩ ክለቦችዝርዝር

በስካይ ላይት ሆቴል ምሸቱን በተካሄደው የዕውቅና ፕሮግራም ላይ ልዩ ሽልማት የተበረከተለት ኮከቡ አቡበከር ናስር በቀጣይ ዓመት በኢትዮጵያ ቡና እንደሚቆይ ፍንጭ ሰጥቷል። በ2013 የውድድር ዘመን አብዛኛዎችን የክብር ሽልማት ጠቅልሎ የወሰደው አቡበከር ናስር በዛሬው ዕለት በስካይ ላይት ሆቴል በተካሄደው የዕውቅና ሥነ ስርዓት ላይ ኮከብ ተጫዋች ልዩ ዋንጫ እና አንድ ነጥብ አራት ሚሊዮንዝርዝር

የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ዋናው የወንዶች ቡድኑ ወደ ኮፌዴሬሽን ዋንጫ ማለፉን በመንተራስ እንዲሁም በሌሎች ቡድኖቹ የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ኮከቦቹ በስካይ ላይት ሆቴል የዕውቅና አሰጣጥ መርሐግብር አካሄዷል። ከምሽቱ አስራ አንድ ሰዓት ጀምሮ በተካሄደው በዚህ የዕውቅና ፕሮግራም ላይ የመዲናችን ምክትል ከንቲባ አዳነች አበቤ፣ የቀድሞ ርዕሰ ብሔር እና የኢትዮጵያ ቡና የበላይ ጠባቂ ዶ/ርዝርዝር

የቡና ኃላፊዎች የውድድር ዓመቱን ሪፖርት እና ክለቡ ከ ‘ከ ሀ እስከ ፐ ‘ ጋር ስላደረገው አዲስ የሥራ ስምምነት አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል። ዛሬ ከሰዓት በስካይ ላይት ሆቴል የተሰጠው የኢትዮጵያ ቡና ጋዜጣዊ መግለጫ ሦስት ክፍሎች ነበሩት። በቀዳሚነት አስተዳደራዊ እና ቴክኒካዊ ሪፖርቶች በሥራ አስኪያጁ አቶ ገዛሀኝ ወልዴ እና በአሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ አማካይነት ቀርበዋል።ዝርዝር

በዘንድሮ የውድድር ዘመን እጅግ ድንቅ ጊዜ ያሳለፈው አቡበከር ናስር ከጆርጂያ ክለብ የእናስፈርም ጥያቄ እንደቀረበለት ተሰምቷል። በሦስት ዘርፎች የዘንድሮ የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ኮከብ ተብሎ ሽልማት የተበረከተለት አቡበከር ናስር የበርካታ የውጪ ክለቦች እይታ ውስጥ መግባቱ እየተሰማ ይገኛል። አሁን በወጣ መረጃ መሠረት ደግሞ የጆርጂያው ክለብ ዲላ ጎሪ ተጫዋቹን የግሉ ለማድረግ የተጫዋቹ ባለቤት ኢትዮጵያዝርዝር

የዘንድሮ የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ተጫዋች የሆነው አቡበከር ናስር የዋንጫ እና የገንዘብ ሽልማቱን ተረክቧል። 29 ግቦችን ያስቆጠረው አቡበከር ናስር የውድድሩ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆኑ የዋንጫ እና የ2 መቶ ሺ ብር ሽልማቱን ከክብር እንግዳው ዮርዳኖስ ዓባይ ተቀብሏል። ተጫዋቹም ሽልማቱን ከተረከበ በኋላ ተከታዩን ሀሳብ በመድረኩ ተናግሯል። “በቅድሚያ ፈጣሪዬን አመሠግናለሁ። ዓመቱዝርዝር

የሁለተኛ ደረጃን ለመያዝ ከፍተኛ ፉክክር ይደረግበታል ተብሎ የሚጠበቀው የ25ኛ ሳምንት የመዝጊያ ጨዋታ እንደሚከተለው ቃኝተነዋል። ሁለቱ የሸገር ክለቦችን በተከታታይ ያስተናገዱት ሀዲያ ሆሳዕናዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ያገኙትን ድል በሌላኛው የመዲናችን ክለብ ለመድገም እና የሁለተኛ ደረጃን ይዘው የሚያጠናቅቁበትን ዕድል በራሳቸው ለመወሰን ጠንክረው ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ይገመታል። ሦስት ነጥብ ካገኙ አምስት የጨዋታ ሳምንታት ያለፋቸውዝርዝር