ኢትዮጵያ ቡና (Page 2)

የኢትዮጵያ ቡና ተጫዋቾች ለዝግጅት ቢሾፍቱ ቢደርሱም ዋና እና ረዳት አሠልጣኙ እስከ አሁን ድረስ ወደ ስፍራው አላቀኑም። በዘንድሮ የውድድር ዘመን ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ የቀጣይ ዓመት የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ውድድር ተሳታፊ መሆኑን ያረጋገጠው ኢትዮጵያ ቡና በጳጉሜ ወር የሚጀመረውን የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎች ላይ ተጠናክሮ ለመቅረብ በትናንትናው ዕለት ዝግጅቱን ለመጀመር ወደ ቢሾፍቱ አምርቷል። ሶከርዝርዝር

በካፍ ኮፌዴሬሽን ዋንጫ ተካፋይ የሆነው ኢትዮጵያ ቡና ለቅድመ ውድድር ዝግጅት ወደ ቢሸፍቱ ሲያመሩ የቡድኑ አሰልጣኞች አብረው አልተጓዙም። በአሰልጣኝ ካሣዬ አራጌ የሚመሩት ኢትዮጵያ ቡናዎች በመጪው የውድድር ዘመን ላሉባቸው አህጉራዊ እና ሀገራዊ ውድድሮች ቅድመ ዝግጅታቸውን ለማድረግ ዛሬ ከሰዓት ለቡ ከሚገኘው የክለቡ የተጫዋቾች መኖርያ በመነሳት ወደ ቢሸፍቱ ከተማ አቅንተዋል። ከ17 እና ከ20 ዓመትዝርዝር

በተጠናቀቀው የ2013 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተካፋይ መሆኑን ያረጋገጠው ኢትዮጵያ ቡና ለውድድሩ ይረዳው ዘንድ ከመጪው ማክሰኞ አንስቶ በቢሾፍቱ ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን የሚያደርግ ይሆናል። በአሰልጣኝ ካሣዬ አራጌ የሚመሩት ኢትዮጵያ ቡናዎች በመጪው የውድድር ዘመን ላሉባቸው አህጉራዊ እና ሀገራዊ ውድድሮች ስብስባቸውን አጠናክሮ ለማቅረብ ከወዲሁ በዝውውርዝርዝር

የወሳኝ ተጫዋቻቸውን ውል ለማደስ ረዘም ያለ ድርድር ላይ የነበሩት ኢትዮጵያ ቡናዎች በመጨረሻም ውጥናቸው ፍሬ አፍርቶ ተጫዋቹ ውሉን አራዝሟል። ለተጨማሪ ዓመት ውሉን ያደሰው የቡድኑ ተጫዋች አሥራት ቱንጆ ነው። የ2010 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከመጀመሩ በፊት ከጅማ አባጅፋር የመዲናውን ክለብ ኢትዮጵያ ቡናን የተቀላቀለው አሥራት ቱንጆ ከዓመት ዓመት እየጎለበተ የቡድኑ ወሳኝ ተጫዋች እየሆነ መጥቷል።ዝርዝር

በአሠልጣኝ ካሣዬ አራጌ የሚመራው ኢትዮጵያ ቡና ልምድ ያለውን የመስመር ተከላካይ ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል። በዘንድሮ የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በ13 ነጥቦች ተበልጦ ዋንጫውን በፋሲል ከነማ ያጣው ኢትዮጵያ ቡና ክፍተቶቼ ባላቸው ቦታዎች ላይ ዝውውሮችን ማድረግ ጀምሯል። ከሁለት ቀናት በፊት የግብ ዘቡ በረከት አማረን ዝውውር ያጠናቀቀው ክለቡ ከሌሎች ተጫዋቾች ጋርም ድርድር ላይ መሆኑዝርዝር

በዝውውር ገበያው ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት ቡናማዎቹ የአንድ ዓመት ኮንትራት ካለው ተከላካያቸው ጋር በስምምነት ተለያይተዋል። በአሠልጣኝ ካሳዬ አራጌ የሚመራው ኢትዮጵያ ቡና በ2014 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እና በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎች ተጠናክሮ ለመቅረብ ከሰባት ቀናት በፊት በተከፈተው የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ላይ እየተሳተፈ ይገኛል። ቡድኑ አዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ ለመቀላቀል እንቅስቃሴዝርዝር

ተክለማርያም ሻንቆን ያጣው ኢትዮጵያ ቡና በምትኩ ተጫዋች በይፋ አስፈርሟል። ክለቡን የተቀላቀለው ተጫዋች የግብ ዘቡ በረከት አማረ ነው። በ2012 የውድድር ዘመን ከቡናማዎቹ ጋር ቆይቶ የነበረው በረከት ዓምና ወደ መቐለ 70 እንደርታ አምርቶ እንደነበር አይዘነጋም። በኮቪድ-19 ሊጉ እስከተቋረጠበት ጊዜ ድረስም በመቐለ ቆይቶ ዘንድሮ ግማሽ ዓመት ላይ ወደ ጅማ አባጅፋር አምርቶ መጨወት ቀጥሎዝርዝር

በዘንድሮ የውድድር ዓመት ጥሩ ብቃት ያሳየው አሥራት ቱንጆ ከቡናማዎቹ ጋር የመቀጠል እና አለመቀጠሉ ጉዳይ እየለየ መጥቷል። በ2009 ክረምት ጅማ አባ ጅፋርን ለቆ ኢትዮጵያ ቡናን የተቀላቀለው አሥራት ቱንጆ በቡናማው መለያ ራሱን እያጎለበት ለቡድኑ ወሳኝ ተጫዋች ሆኗል። በተለይ ለአሠልጣኝ ካሣዬ አራጌ አጨዋወት አመቺ የሆነው የመስመር ተከላካዩ ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ ስሙ ከተለያዩ ክለቦችዝርዝር

በስካይ ላይት ሆቴል ምሸቱን በተካሄደው የዕውቅና ፕሮግራም ላይ ልዩ ሽልማት የተበረከተለት ኮከቡ አቡበከር ናስር በቀጣይ ዓመት በኢትዮጵያ ቡና እንደሚቆይ ፍንጭ ሰጥቷል። በ2013 የውድድር ዘመን አብዛኛዎችን የክብር ሽልማት ጠቅልሎ የወሰደው አቡበከር ናስር በዛሬው ዕለት በስካይ ላይት ሆቴል በተካሄደው የዕውቅና ሥነ ስርዓት ላይ ኮከብ ተጫዋች ልዩ ዋንጫ እና አንድ ነጥብ አራት ሚሊዮንዝርዝር

የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ዋናው የወንዶች ቡድኑ ወደ ኮፌዴሬሽን ዋንጫ ማለፉን በመንተራስ እንዲሁም በሌሎች ቡድኖቹ የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ኮከቦቹ በስካይ ላይት ሆቴል የዕውቅና አሰጣጥ መርሐግብር አካሄዷል። ከምሽቱ አስራ አንድ ሰዓት ጀምሮ በተካሄደው በዚህ የዕውቅና ፕሮግራም ላይ የመዲናችን ምክትል ከንቲባ አዳነች አበቤ፣ የቀድሞ ርዕሰ ብሔር እና የኢትዮጵያ ቡና የበላይ ጠባቂ ዶ/ርዝርዝር