Soccer Ethiopia

ወላይታ ድቻ

ወላይታ ድቻ በሦስት ተጫዋቾቹ ክስ ሲቀርብበት ተጫዋቾቹ ለሁለተኛ ጊዜ ልምምድ አቁመዋል

ወላይታ ድቻ በሦስት የክለቡ ተጫዋቾችን አቤቱታ የቀረበበት ሲሆን ለሁለተኛ ጊዜ የአምስት ወር ደመወዛችን በተባለው ቀን አልተከፈለንም በሚል የክለቡ አባላት ልምምድ አቁመዋል፡፡ ክለቡ ለዘንድሮው የ2013 የውድድር አመት ለፕሪምየር ሊጉ ዝግጅት ማድረግ ከጀመረ ወራት ሊቆጠሩ ጥቂት ቀናት ቀርተውታል፡፡ ይሁንና የክለቡ ተጫዋቾች ከሀምሌ ወር ጀምሮ እስከ ያዝነው ወር ድረስ ደመወዝ አልተከፈለንም በማለት ኅዳር ወር አጋማሽ ላይ ልምምድ ማቆማቸውን […]

​የወላይታ ድቻ ተጫዋቾች ልምምድ ማቆም እና የክለቡ ምላሽ…

የወላይታ ድቻ ተጫዋቾች እና አሰልጣኞች ከደመወዝ ጥያቄ ጋር በተገናኘ በተደጋጋሚ ክለቡን ጠይቀው ምላሽ እንዳላገኙ በመግለፅ የዛሬ ልምምዳቸውን ማድረግ ሳይችሉ ወደየመጡበት ተመልሰዋል፡፡ የጦና ንቦቹ ለ2013 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የቅድመ ውድድር ዝግጅት በሶዶ ከተማ ከጀመሩ ሁለት ሳምንታት አልፏቸዋል፡፡ ቡድኑ የመጀመሪያዎቹን አንድ ሳምንታት በቀን ሁለቴ ልምምድ ሲሰሩ ከሰነበቱ በኃላ ያለፉትን አምስት ቀናት በቀን አንድ ጊዜ በአሰልጣኝ ደለለኝ ደቻሳ […]

ወላይታ ድቻ ሁለት ተጫዋቾችን አስፈረመ

የቅድመ ውድድር ዝግጀታቸውን ከጀመሩ ሁለት ሳምንታት ያለፋቸው የጦና ንቦቹ ሁለት ተጫዋቾችን የግላቸው አድርገዋል፡፡ የመሐል ተከላካዩ አዩብ በቀታ ለወላይታ ድቻ የፈረመ ተጫዋች ነው፡፡ በሀዲያ ሆሳዕና በተሰረዘው የውድድር ዓመት በግሉ መልካም ጊዜ የነበረው ይህ ተጫዋች ባለፈው ወር ለከፍተኛ ሊጉ ክለብ አርባምንጭ ከተማ ለመጫወት ስምምነት ፈፅሞ የነበረ ቢሆንም ምርጫውን ወላይታ ድቻ በማድረግ የሁለት ዓመት ውል ፈርሟል፡፡ ሌላኛው ክለቡን […]

ወላይታ ድቻ አጥቂ አስፈረመ

የጦና ንቦቹ ወጣቱ አጥቂ ያሬድ ዳርዛን አስፈረሙ፡፡ ከወላይታ ድቻ ወጣት ቡድን ከተገኘ በኃላ ለክለቡ ዋናው ቡድን ሳይጫወት ያለፉትን ሁለት የውድድር ዓመታት በከፍተኛ ሊጉ ለርባምንጭ ከተማ እና ኢኮሥኮ አምርቶ በመጫወት ያሳለፈው የአጥቂ መስመር ተሰላፊው ያሬድ የዝውውር መስኮቱ ከመከፈቱ በፊት ቅድመ ስምምነት ከፈፀሙ ተጫዋቾች አንዱ የነበረ ሲሆን ወደ ልጅነት ቡድኑ የሚመልሰውን የሁለት ዓመት ኮንትራት በመፈራረም በዛሬው ዕለት […]

የዘመናችን ከዋክብት ገፅ | ቆይታ ከኤልያስ አሕመድ ጋር…

በቅርብ ዓመታት በሊጉ እየታዩ ከሚገኙ ጥሩ የአማካይ መስመር ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ኤልያስ አህመድ በዛሬው የዘመናችን ከዋክብት ገፅ ላይ እንግዳ ሆኗል። ብዙዎች ‘ኳስ እግሩ ላይ ታምራለች’ የሚሉለት የዛሬው እንግዳችን ኤልያስ በመዲናችን አዲስ አበባ ተወልዶ አድጓል። በታዳጊነቱም ተወለዶ ባደገበት ልደታ አካባቢ ኳስን መጫወት ጀምሯል። የአስራዎቹን ዕድሜ ሲጀምርም ለአጭር ጊዜ በፕሮጀክት ደረጃ ታቅፎ መሰልጠን የሚችልበትን እድል አግኝቶ […]

“ለፋሲል ከነማ ደጋፊ ትልቅ ክብር አለኝ” ሽመክት ጉግሳ

አስቀድሞ ከፋሲል ከነማ ጋር ውሉን ለማደስ ከስምምነት ደርሶ በዛሬው ዕለት ደግሞ ለቀድሞ ክለቡ ወላይታ ድቻ የመስማማቱን ምክንያት ሽመክት ጉግሳ ይናገራል። በሊጉ ከሚጠቀሱ ምርጥ የመስመር አጥቂዎች መካከል አንዱ የሆነው ሽመክት ለተጨማሪ ዓመት ከዐፄዎቹ ጋር ለመቆየት አስቀድሞ ተስማምቶ እንደነበረ ይታወቃል። ነገር ግን በዛሬ ዕለት ለቀድሞው ክለቡ ወላይታ ድቻ ለሁለት ዓመት ለመጫወት ቅድመ ስምምነት ፈፅሟል፡፡ ይህን ተከትሎ ለፋሲል […]

ወላይታ ድቻ የአምስተኛ ተጫዋቹን ውል አራዘመ

ፀጋዬ አበራ ለተጨማሪ ዓመት በክለቡ ለመቆየት ቅድመ ስምምነት ፈፅሟል፡፡ ከአርባምንጭ ከተማ የታዳጊ ቡድን እስከ ዋናው ድረስ በአዞዎቹ ቤት የፕሪምየር ሊግ ቆይታን ካደረገ በኃላ 2011 መስከረም ወር ላይ ወደ ጦና ንቦቹ አምርቶ ሁለት የውድድር ዓመታትን በክለቡ አሳልፏል፡፡ በክለቡ ቆይታው ከሚታወቅበት የመስመር አጥቂነቱ ባሻገር በቀኝ መስመር ተከላካይነት ያገለገለ ሲሆን ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ ለሁለት ተጨማሪ ዓመት በክለቡ ለመቆየት […]

ሽመክት ጉግሳ ወደ ቀድሞ ክለቡ ለማምራት ተስማማ

ወላይታ ድቻ የቀድሞው ተጫዋቹ ሽመክት ጉግሳን ለማስፈረም ተስማምቷል፡፡ በመስመር አጥቂነት በፕሪምየር ሊጉ ከሚጫወቱ ተጫዋቾች መካከል ከግንባር ቀደሞቹ የሚጠቀሰው ሽመክት ከዚህ ቀደም ለትውልድ ከተማው ክለብ ወላይታ ድቻ በቀድሞው ብሔራዊ ሊግ (በአሁኑ አንደኛ ሊግ) የተጫወተ ሲሆን ከዛም በመቀጠል በአየር ኃይል፣ ሀዋሳ ከተማ፣ ደደቢት እንዲሁም ከ2011 ጀምሮ ደግሞ ያለፉትን ሁለት ዓመታት በፋሲል ከነማ መለያ ምርጥ የውድድር ጊዜን ካሳለፈ […]

ወላይታ ድቻ የሦስት ተጫዋቾችን ውል አራዘመ

በቀድሞው የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት መምህር የሚመሩት ወላይታ ድቻዎች እስከ አሁን ስምንት አዳዲስ ተጫዋቾችን ያስፈረሙ ሲሆን የወሳኝ አጥቂው ባዬ ገዛኸኝንም ውል ማራዘማቸው ይታወሳል፡፡ ዛሬ አመሻሽ ደግሞ የሦስት ነባር ተጫዋቾችን ውል ለማራዘም ተስማምተዋል፡፡ ውል ካራዘሙት ተጫዋቾች መካከል አንተነህ ጉግሳ አንዱ ነው፡፡ በመሀል እና በመስመር ተከላካይነት የከፍተኛ ሊጉን ክለብ ሶዶ ከተማን ለቆ ወላይታ ድቻን በ2011 የውድድር ዓመት […]

ወላይታ ድቻ አማካይ ለማስፈረም ተስማማ

የጦና ንቦቹ ኤልያስ አሕመድን ስምንተኛ ፈራሚ ለማድረግ ተስማምተዋል፡፡ የቀድሞው የሰበታ ከተማ እና ባህር ዳር ከተማ ተጫዋች የሆነው ኤልያስ ዘንድሮ ሊጉ እስከተሰረዘበት ጊዜ ድረስ በጅማ አባጅፋር በግሉ መልካም እንቅስቃሴን ሲያደርግ ቆይቷል። ውሉ በመጠናቀቁም ወደ የአሰልጣኝ ደለለኝ ደቻሳውን ወላይታ ድቻ በሁለት ዓመት ውል ለመቀላቀል ዛሬ አመሻሽ ስምምነት ፈፅሟል፡፡ ወላይታ ድቻዎች እስከ አሁን ኤልያስ አሕመድን ጨምሮ ስምንት አዳዲስ […]

ሶከር ኢትዮጵያ

ሶከር ኢትዮጵያ በ ‘አብርሀም ገ/ማርያም የማስታወቂያ ድርጅት’ ስር የሚሰራ ድረገፅ ሲሆን በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በሚያተኩሩ ዜናዎች፣ ቁጥራዊ መረጃዎች፣ ታሪኮች፣ ጥልቅ ዘገባዎች፣ አስተያየቶች እና ትንታኔዎች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

ዘርፍ

ማኅደር

top