Soccer Ethiopia

ወላይታ ድቻ

የወላይታ ድቻ ቡድን አባላት ድጋፍ ሲያደርጉ አሰልጣኞች እና የቀድሞ ተጫዋቾች ድጋፍ የማሰባሰብ ስራ አከነውነዋል

የኮሮናን ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል የሚደረገው ድጋፍ የቀጠለ ሲሆን የወላይታ ድቻ የቡድን አባላት የገንዘብ ድጋፍ አበርክተዋል። አሰልጣኞች እና የቀድሞ ተጫዋቾችም የግንዛቤ ማስጨበጫ እና ድጋፍ የማሰባሰብ ስራ አከናውነዋል። ወላይታ ድቻዎች ከተጫዋቾች፣ የክለቡ አመራሮች እና አሰልጣኞች እንዲሁም በቡድኑ ውስጥ የሚገኙ ሠራተኞች የተሰበሰበ አንድ መቶ ሺህ ብር ለዞኑ የኮሮና ቫይረሰ መከላከል ግብር ኃይል አስረክበዋል። ቡድኑም በቀጣይ በርካታ የገንዘብና ቁሳቁስ […]

ወላይታ ድቻ የመስመር ተጫዋች አስፈርሟል

ወላይታ ድቻዎች ትናንት የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ ቀደም ብለው በረከት ወንድሙን ዝውውርን ፈፅመዋል፡፡ በ2008 በወላይታ ድቻ ከ17 ዓመት በታች የክለብ እግር ኳስን የጀመረው እና በ2010 ደግሞ ከ20 ዓመት የድቻ ቡድን ውስጥ ቆይታን ያደረገው ይህ ተጫዋች ዐምና የተስፋ ቡድን ቆይታው በመጠናቀቁ ምክንያት ወደ ከፍተኛ ሊጉ ሶዶ ከተማ አምርቶ ለአንድ ዓመት ከግማሽ ያህል ቆይታን ካደረገ በኃላ ዳግም ወደአሳዳጊ […]

ወላይታ ድቻ ከአጥቂ መስመር ተጫዋቹ ጋር ተለያየ

የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ ዳንኤል ዳዊት ከወላይታ ድቻ ጋር ተለያይቷል፡፡ ዓምና በከፍተኛ ሊጉ በነቀምቴ ከተማ ድንቅ ጊዜ ማሳለፉን ተከትሎ በአሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ አማካኝነት በዓመቱ ጅማሮ ለወላይታ ድቻ ፈርሞ የነበረው ፈጣኑ አጥቂ ዳንኤል ዳዊት በፕሪምየር ሊጉ የመጀመሪያ ሳምንታት ላይ የመጫወት እድል ቢያገኝም አብዛኛዎቹን ጨዋታዎች ላይ ተሳትፎ ማድረግ ሳይችል ቀርቶ በመጨረሻም ከክለቡ ጋር የወራት ኮንትራት እየቀረው ተለያይቷል፡፡ ወላይታ […]

ወላይታ ድቻ ከመስመር ተከላካዩ ጋር ተለያየ

የግራ መስመር ተከላካዩ ይግረማቸው ተስፋዬ ከወላይታ ድቻ ጋር ተለያይቷል፡፡ በአሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ አማካኝነት በክረምቱ የዝውውር መስኮት በመስከረም ወር አጋማሽ ነበር ወላይታ ድቻን የተቀላቀለው የቀድሞው የሀዲያ ሆሳዕና እና ወልዲያ ተጫዋች ወደ ወላይታ ድቻ ካመራ በኋላ ጥቂት ጨዋታዎችን ያደረገ ሲሆን ቀሪ የ18 ውል እየቀረው መለያየቱን ለማወቅ ተችሏል። ቡድኑ በዝውውር መስኮቱ በግራ ተከላካይ ስፍራ ላይ አበባው ቡጣቆን ማስፈረሙ […]

የአሰልጣኞች አስተያየት | ወላይታ ድቻ 0-0 ወልዋሎ

ሶዶ ላይ የተደረገው የወላይታ ድቻ እና ወልዋሎ ጨዋታ ያለ ጎል ከተጠናቀቀ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። “ጨዋታ ላይ ጥሩ መንቀሳቀስ ብቻ ውጤት አያስገኝም” ደለለኝ ደቻሳ (ወላይታ ድቻ) ጨዋታ ላይ ጥሩ መንቀሳቀስ ብቻ ውጤት አያስገኝም። ጨዋታውን ተቆጣጥረን ነበር የተጫወትነው፤ ቢሆንም ያገኘነውን አጋጣሚ መጠቀም ባለመቻላችን ማሸነፍ አልቻልንም። ጎል የማግባት ችግር እንዳለብን ነው ያየነው። ይህንን ችግራችንን ቀርፈን […]

ሪፖርት | አሰልቺው ጨዋታ ያለ ግብ ተጠናቋል

ከዛሬ የ17ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች መካከል ወላይታ ሶዶ ላይ የተደረገው የወላይታ ድቻ እና የወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጨዋታ ያለምንም ግብ ተጠናቋል። ወላይታ ድቻ በ16ኛው ሳምንት በሲዳማ ቡና ከተሸነፈበት አሰላለፍ ላይ የሦስት ተጫዋቾች ለውጥ በማድረግ አዲስ ፈራሚዎቹ አበባው ቡታቆ እና አማኑኤል ተሾመን እንዲሁም ጉዳት ላይ የነበረው ደጉ ደበበን በማሰለፍ ወደ ሜዳ የገባ ሲሆን እንግዳው ቡድን […]

ቅድመ ዳሰሳ | ወላይታ ድቻ ከ ወልዋሎ

የጦና ንቦች በሜዳቸው ቢጫ ለባሾቹን የሚያስተናግዱበት ጨዋታን እንደሚከተለው ዳሰነዋል። ከደካማው ጉዞ ወጥተው ተከታታይ ጨዋታዎች በማሸነፍ ደረጃቸውን ያሻሻሉት የጦና ንቦች በተከታታይ ጨዋታዎች ነጥብ ጥለው ከደረጃቸው ላለመውረድ ከዚህ ጨዋታ ሦስት ነጥብ ይዞ መውጣት ይጠበቅባቸዋል። የወላይታ ድቻ ያለፉት 5 ጨዋታዎች አቋም (ከቅርብ ወደ ሩቅ) ተሸነፈ ተሸነፈ አሸነፈ አሸነፈ አሸነፈ በሜዳቸው ጥሩ ክብረ ወሰን ያላቸው የጦና ንቦች በሜዳቸው በብዛት […]

የአሰልጣኞች አስተያየት | ሲዳማ ቡና 5-3 ወላይታ ድቻ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አስራ ስድስተኛው ሳምንት ጨዋታ ሲዳማ ቡና በሜዳው ሀዋሳ ሰው ሰራሽ ሜዳ ላይ ወላይታ ድቻን 5ለ3 ካሸነፈበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የሁለቱ ክለብ ዋና አሰልጣኞች አስተያየታቸውን ሰጥተውናል፡፡ ” ሜዳችን ላይ አጥቅተን ነው የምንጫወተው” ዘርዓይ ሙሉ (ሲዳማ ቡና) ስለጨዋታው እና ስለተቆጠሩት ግቦች የመከላከል ችግራችን ዛሬ ላይ የለም። ለምሳሌ የመጀመሪያው ግብ ሲቆጠር የመሳይ በረኛው አቋቋም ነው፤ […]

ሪፖርት | የዓመቱ ፈጣን ጎል በተቆጠረበት ጨዋታ ሲዳማ ቡና ወላይታ ድቻን ረቷል

ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 16ኛው ሳምንት ጨዋታዎች ስምንት ግቦችን ባስተናገደው የሲዳማ ቡና እና ወላይታ ድቻ ጨዋታ ባለሜዳዎቹ በሀብታሙ ገዛኸኝ ሐት-ትሪክ ታግዘው 5-3 በማሸነፍ ተከታታይ የድል ጉዟቸውን ቀጥለዋል። ሲዳማ ቡናዎች በመጀመሪያው ዙር የመጨረሻ ጨዋታ ሰበታን በሜዳቸው ሲያሸንፉ ከተጠቀሙት ቡድን ውስጥ ፍቅሩ ወዴሳ ፣ ግርማ በቀለ እና ብርሀኑ አሻሞን በመሳይ አያኖ ፣ ሰንደይ ሙቱክ እና ዳዊት ተፈራ በመተካት […]

ሲዳማ ቡና ከ ወላይታ ድቻ – ቀጥታ የውጤት መግለጫ

እሁድ የካቲት 29 ቀን 2012 FT ሲዳማ ቡና 5-3 ወላይታ ድቻ 1′ አዲስ ግደይ 25′ ዳዊት ተፈራ 48′ ሀብታሙ ገዛኸኝ 66′ ሀብታሙ ገዛኸኝ 83′ ሀብታሙ ገዛኸኝ 19′ እድሪስ ሰዒድ 77′ እድሪስ ሰዒድ 90′ ባዬ ገዛኸኝ (ፍ) ቅያሪዎች 78′ ዳዊት / ትርታዬ 53′ ተመስገን / ነጋሽ  – 64′ እዮብ / ፀጋዬ – – ካርዶች – – […]

ሶከር ኢትዮጵያ

ሶከር ኢትዮጵያ በ ‘አብርሀም ገ/ማርያም የማስታወቂያ ድርጅት’ ስር የሚሰራ ድረገፅ ሲሆን በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በሚያተኩሩ ዜናዎች፣ ቁጥራዊ መረጃዎች፣ ታሪኮች፣ ጥልቅ ዘገባዎች፣ አስተያየቶች እና ትንታኔዎች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

ዘርፍ

ማኅደር

top