በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ27ኛ ሳምንት መገባደጃ ሁለት ጨዋታዎች የተመለከቱ መረጃዎች እንደሚከተለው ቀርቧል። ሀድያ ሆሳዕና ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሀድያ ሆሳዕና እና መውረዱን ያረጋገጠው እና የአሰልጣኝ ለውጥ ያደረገው ኢትዮ ኤሌክትሪክ የሚያደርጉት ጨዋታ 7:00 ላይ ይጀመራል። ባለፉት አምስት ጨዋታዎች ሁለት አቻ ፤ ሁለት ሽንፈትና አንድ ድል አስመዝግበው ሠላሳ ስድስት ነጥቦች የሰበሰቡት ሀድያዎችRead More →

“ወራጁን እንኳን አሁን ሳይሆን በመጨረሻው ቀን ነው የሚለየው ብዬ አስባለሁ” አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ “ከታች የመጣ ነው ፣ ስሜቱን እረዳዋለሁ ፣ ግን ምንም እስካልሰራ ድረስ ከቡድኑ ማንም አይበልጥም” አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ወልቂጤ ከተማ እና ፋሲል ከነማ የሀዋሳ የመጨረሻ ጨዋታቸውን ያለ ጎል ከፈፀሙ በኋላ አሰልጣኞች ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ ነበራቸው። አሰልጣኝ ገብረክርስቶስRead More →

የወልቂጤ እና ፋሲል የዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ 0ለ0 በሆነ ውጤት ፍፃሜን አግኝቷል። ወልቂጤ ከተማ ድል ካደረጉበት የመድኑ ጨዋታቸው ቅያሪ ሳያደርጉ ሲገቡ በአንፃሩ ከድሬዳዋው ሽንፈታቸው ፋሲሎች የሁለት ተጫዋቾች ለውጥ አድርገዋል። በለውጡም አስቻለው ታመነን በዓለምብርሀን ይግዛው ፣ ሀብታሙ ገዛኸኝን በዱላ ሙላቱ ተክተዋል። ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት የዕለቱ ዋና ዳኛ ተካልኝ ለማ ፋሲሎች ያደረጉት መለያRead More →

“ቡድናችን ዛሬ ድክመት ነበረበት።” – አሰልጣኝ ዮሴፍ ተስፋዬ “ያለንን አቅም አውጥተን ነው የተጫወትነው።” – ምክትል አሰልጣኝ ለይኩን ታደሰ ኢትዮጵያ መድን የሀዋሳ ቆይታውን ኢትዮጵያ ቡና ላይ የ 2-1 ድል በመቀዳጀት ከቋጨ በኋላ የሁለቱም ቡድኖች አሰልጣኞች ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል። አሰልጣኝ ዮሴፍ ተስፋዬ – ኢትዮጵያ ቡና ስለ ጨዋታው… “በመጀመሪያው አጋማሽ በጣምRead More →

ኢትዮጵያ መድን ኢትዮጵያ ቡናን 2-1 በመርታት የሀዋሳ ቆይታውን በድል ዘግቷል። ኢትዮጵያ መድን ከወልቂጤው ሽንፈት በሦስት ተጫዋች ላይ ቅያሪ አስፈልጎታል። ሐቢብ መሐመድ ፣ ዮናስ ገረመው እና ሀብታሙ ሸዋለምን በፀጋሰው ድማሙ ፣ አሚር ሙደሲር እና ወገኔ ገዛኸኝ ሲተኩ ሀድያ ላይ ኢትዮጵያ ቡና ድል ካደረገው ስብስቡ ጉዳት በገጠመው ሬድዋን ናስር ምትክ ጫላ ተሺታንRead More →

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 27ኛ ሳምንት ሦስተኛ ቀን የሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎችን የተመለከቱ መረጃዎች እነሆ! ኢትዮጵያ መድን ከ ኢትዮጵያ ቡና ቀን 7 ሰዓት ላይ ተቃራኒ የጨዋታ ሳምንት ባሳለፉ ቡድኖች መካከል የሚደረገው ጨዋታ ብርቱ ፉክክር ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል። በወልቂጤ ከተማ የውድድሩን ሰባተኛ ሽንፈት ያስተናገዱት መድኖች ሁሉ ነገራቸውን ባጡበት ጨዋታ ካለፉት 14 ጨዋታዎችRead More →

“ማሸነፍ አስበን ብቻ ነው የገባነው” አሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ “እንደጠበቅነው ጨዋታው ጠንካራ ነበር” አሰልጣኝ አስራት አባተ አዳማ ከተማ ከመመራት ተነስቶ ድሬዳዋ ከተማን ካሸነፈበት ጨዋታ በኋላ የሁለቱም ቡድን አሰልጣኞች ለሶከር ኢትዮጵያ የሰጡት አስተያየት እንደሚከተለው ቀርቧል። አሰልጣኝ አስራት አባተ ስለ ጨዋታው… እንደጠበቅነው ጨዋታው ጠንካራ ነበር። በሁለታችን መካከል የነበረው የነጥብ ልዩነት ተቀራራቢ ስለነበር በአግባቡRead More →

አዳማ ከተማ በሁለተኛው አጋማሽ ከጥሩ እንቅስቃሴ ጋር ታግዞ ከመመራት ተነስቶ ባስቆጠራቸው ሁለት ግቦች ድሬዳዋ ከተማን አሸንፏል። ድሬዳዋ በፋሲሉ ድል ላይ ይዞት የገባውን አሰላለፍ ሳይለውጥ ለጨዋታው ሲቀርብ በአንፃሩ በለገጣፎ ሽንፈት ያስተናገዱት አዳማዎች የአምስት ተጫዋቾችን ቅያሪ አድርገዋል። እዮብ ማቲዮስ ፣ ዳንኤል ደምሱ ፣ አማኑኤል ጎበና ፣ ቦና ዓሊ እና ቢኒያም አይተንን በአዲሱRead More →

“ተጫዋቾቹ ነጥብ እያሰሉ ስለሚጫወቱ ከዛ ጫና መውጣት አለብን ብዬ ነው የማስበው።” – አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም “ዛሬ ቡድናችን እጅግ በጣም ጥሩ ነበር።” – አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም – ወላይታ ድቻ ስለ ጨዋታው… “የቡድናችን አጨዋወት በተለይም በመጀመሪያው አጋማሽ በጣም ጥሩ ነበር። የመጀመሪያው አጋማሽ መጠናቀቂያ ላይ የተቆጠረብን የሙጅብ ጎል ብዙ ነገርRead More →

ሀዋሳ ከተማ በሜዳው እና በደጋፊው ፊት የመጀመሪያ ሦስት ነጥቡን ወላይታ ድቻን 3ለ1 በመርታት አስመዝግቧል። ሀዋሳ ከተማ በመጨረሻ ደቂቃ ግብ ተቆጥሮበት ነጥብ ከተጋራው የመቻሉ ጨዋታ የአንድ ተጫዋች ለውጥ አድርጎ ጀምሯል። በለውጡም በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቶ በነበረው ግብ ጠባቂው መሐመድ ሙንታሪ ምትክ አላዛር ማርቆስን በብቸኝነት ሲለውጡ ከሲዳማ ቡና ጋር ያለ ጎል አጠናቀውRead More →