Soccer Ethiopia

የጨዋታ ሪፖርት

ሪፖርት | ዋልያዎቹ ዳግም በአቋም መለኪያ ጨዋታ ተረተዋል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአዲስ አበባ ስታዲየም ከዛምቢያ አቻው ጋር ያደረገውን የአቋም መፈተሻ ጨዋታ 3-1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል። በኮቪድ-19 ምክንያት ወደ 2022 ለተሸጋገረው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የማጣሪያ ጨዋታዎች እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በህዳር ወር የመጀመሪያ ቀናት ከኒጀር ጋር ላለበት የምድቡ 3ኛ እና 4ኛ ጨዋታ ይረዳው ዘንድ በዛሬው ዕለት ሁለተኛ የአቋም መለኪያ ጨዋታውን ከዛምቢያ ጋር በአዲስ […]

ሪፖርት | ዋልያዎቹ በአቋም መለኪያ ጨዋታ ተረተዋል

ከዛምቢያ ጋር የአቋም መለኪያ ጨዋታ ያደረጉት ዋልያዎቹ በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች በተቆጠረባቸው ሁለት ጎሎች 3-2 ተሸንፈዋል። በኮቪድ-19 ምክንያት ለተራዘመው የ2021 (ወደ 2022 የተሸጋገረው) የካሜሩን የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የማጣሪያ ጨዋታዎች እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከኒጀር ጋር ላለበት የምድቡ 3ኛ እና 4ኛ ጨዋታ በዛሬው ዕለት የአቋም መለኪያ ጨዋታ ከዛምቢያ አቻው ጋር አከናውኗል። ከሳምንታት በፊት ብሔራዊ ቡድኑን ለቀጣይ ሁለት […]

ሪፖርት | ስሑል ሽረ በድል ወደ ሜዳው ተመልሷል

በ17ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሜዳቸው ጥገና ላይ መቆየቱን ተከትሎ ለ6 ወራት በትግራይ ኢንተርናሽናል ስታድየም ሲጫወቱ የቆዩት ስሑል ሽረዎች ወደ ከተማቸው ተመልሰው ባደረጉት የመጀመርያ ጨዋታ ሲዳማ ቡናን በጠባብ ውጤት አሸንፈዋል። ባሳለፍነው ሳምንት በኢትዮጵያ ቡና የግማሽ ደርዘን ጎሎች አሰቃቂ ሽንፈት የተከናነቡት ባለሜዳዎቹ በአዲሱ ሜዳቸው ድል ቀንቷቸዋል። ስሑል ሽረዎች ሳምንት ከተሸነፉበት ስብስብ ዉስጥ ያልተካተቱትን ግብ ጠባቂው ወንድወሰን […]

ሪፖርት | ባህር ዳሮች በግብ ጠባቂው አስደናቂ ብቃት ታግዘው ከመቐለ ጋር ነጥብ ተጋርተዋል

ሀሪስተን ሄሱ ድንቅ ብቃት ባሳየበት ጨዋታ ምዓም እናብስት እና የጣና ሞገዶቹ ነጥብ ተጋርተዋል። መቐለዎች ባለፈው ሳምንት ሀዲያ ሆሳዕናን ካሸነፈው ስብስብ ቢያድግልኝ ኤልያስን በአስናቀ ሞገስ ተክተው ሲገቡ ባህር ዳር ከተማዎችም ጅማን ከረታው ስብስብ ስንታየሁ መንግሥቱን በማማዱ ሲዲቤ ተክተው ገብተዋል። የመቐለዎች ሙሉ ብልጫ የታየበት እና ቤኒናዊ ግብ ጠባቂ ሀሪሰን ሄሱ የጣና ሞገዶቹን የቁርጥ ቀን ልጅ መሆኑ ባስመሰከረበት […]

ሪፖርት | ሀዋሳ ከተማ እና ሀዲያ ሆሳዕና ነጥብ ተጋርተዋል

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 17ኛው ሳምንት ሀዋሳ ላይ ሀዋሳ ከተማ እና ሀዲያ ሆሳዕና እጅግ ቀዝቃዛ በነበረው ጨዋታ 1-1 በሆነ ውጤት ተለያይተዋል። ሀዋሳ ከተማዎች ባለፈው ሳምንት በድሬዳዋ ሽንፈት ካስተናገደው ቡድን ውስጥ በአራት ተጫዋች ላይ ለውጥ አድርገዋል። በዚህም ሀብቴ ከድር በቢሊንጋ ኢኖህ ፣ ላውረንስ ላርቴን በወንድማገኝ ማዕረግ ፣ ተስፋዬ መላኩን በአክሊሉ ተፈራ ፣ ሄኖክ አየለን በብርሀኑ በቀለ ለውጠዋል፡፡ […]

ሪፖርት | አሰልቺው ጨዋታ ያለ ግብ ተጠናቋል

ከዛሬ የ17ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች መካከል ወላይታ ሶዶ ላይ የተደረገው የወላይታ ድቻ እና የወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጨዋታ ያለምንም ግብ ተጠናቋል። ወላይታ ድቻ በ16ኛው ሳምንት በሲዳማ ቡና ከተሸነፈበት አሰላለፍ ላይ የሦስት ተጫዋቾች ለውጥ በማድረግ አዲስ ፈራሚዎቹ አበባው ቡታቆ እና አማኑኤል ተሾመን እንዲሁም ጉዳት ላይ የነበረው ደጉ ደበበን በማሰለፍ ወደ ሜዳ የገባ ሲሆን እንግዳው ቡድን […]

ሪፖርት |  ጅማ አባ ጅፋር እና ኢትዮጵያ ቡና ድራማዊ በሆነ መልኩ በአቻ ውጤት ተለያይተዋል

በ17ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጅማ ላይ አባ ጅፋር ኢትዮጵያ ቡናን ያስተናገደበት ጨዋታ በመጨረሻ ደቂቃ በተቆጠሩ ግቦች 1-1 ተጠናቋል። ጅማ አባ ጅፋር ሳምንት በባህር ዳር ሽንፈት ከቀመሰው ስብስቡ ውስጥ ኤልያስ አታሮ ፣ ተመስገን ደረሰ እና ኤርሚያስ ኃይሉን በማሳረፍ ለመላኩ ወልዴ፣ አመረላ ደልታታ እና ሱራፌል ዐወል የመሰለፍ ዕድል ሰጥቷል። ኢትዮጵያ ቡናዎች ደግሞ በ16ኛው ሳምንት ስሑል ሽረን […]

ሪፖርት | ያለ አሰልጣኝ ጨዋታ ያደረገው ቅዱስ ጊዮርጊስ በሰበታ ሽንፈትን አስተናግዷል

በ17ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ የጨዋታ ቀን አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ ያለ አሰልጣኝ ሰበታ ከተማን የገጠመው ቅዱስ ጊዮርጊስ በአስቻለው ግርማ ብቸኛ ግብ ሽንፈት አስተናግዷል። ሰበታ ከተማዎች ከወልዋሎ ጋር ከመመራት ተነስቶ ሁለት አቻ ከተለያየው ስብስብ ላይ ሁለት ለውጦችን ሲያደርግ በዚህም ሳሙኤል ታዬ እና ባኑ ዲያዋራ ደግሞ ወደ መጀመሪያ አሰላለፍ የተመለሱበት ጨዋታ ነበር። ቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ […]

ሪፖርት | ድሬዳዋ እና ፋሲል ያለ ጎል ተያይተዋል

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 17ኛ ሳምንት ሁለተኛ የጨዋታ ቀን ድሬዳዋ ላይ ድሬዳዋ ከተማ ዐፄዎቹን ያስተናገደበት ጨዋታ ያለምንም ግብ ተጠናቋል። ድሬዳዋ ባለፈው ሳምንት ሀዋሳን ከረታበት ጨዋታ በቅጣት ባልተሰለፈው ፍሬድ ሙሸንዲ ምትክ ከድር አዩብን እንዲሁም በቢኒያም ጾመልሳን ምትክ አዲስ ፈራሚው እንዳለ ከበደን በማሰለፍ ጨዋታውን ጀምሯል። ዐፄዎቹ በበኩላቸው አዳማን ካሸነፈው ስብስብ በቅጣት ባልተሰለፈው ከድር ኩሊባሊ ምትክ ሰዒድ ሀሰንን በመሐል […]

ሪፖርት | አዳማ ከተማ ወልቂጤን አሸንፏል

17ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በቅጣት ምክንያት አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ አዳማ ከተማን ያስተናገዱት ወልቂጤ ከተማዎች እጅግ ደካማን እንቅስቃሴ ባሳዩበት ጨዋታ በአዳማ ከተማ የ2ለ0 ሽንፈት ደርሶባቸዋል። ባለሜዳዎቹ ወልቂጤዎች ባሳለፍነው የጨዋታ ሳምንት ቅዱስ ጊዮርጊስን ከረታው ስብስብ ውስጥ ሦስት ተጫዋቾች ለውጥ ሲያደርጉ በዚህም ዐወል ከድር፣ ፍፁም ተፈሪ እና እዩኤል ሳሙኤል በዛሬው ጨዋታ በመጀመሪያው አሰላለፍ ሲካተቱ በአዳማዎች በኩል […]

ሶከር ኢትዮጵያ

ሶከር ኢትዮጵያ በ ‘አብርሀም ገ/ማርያም የማስታወቂያ ድርጅት’ ስር የሚሰራ ድረገፅ ሲሆን በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በሚያተኩሩ ዜናዎች፣ ቁጥራዊ መረጃዎች፣ ታሪኮች፣ ጥልቅ ዘገባዎች፣ አስተያየቶች እና ትንታኔዎች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

ዘርፍ

ማኅደር

top