ብሔራዊ ቡድን (Page 92)

  አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜ ካፈራቻቸው ድንቅ አሰልጣኞች አንዱ ናቸው፡፡ አሰልጣኙ ስላሳለፉት የእግርኳስ ህይወት እና ስለወደፊቱ አላማቸው ለሶከር ኢትዮጵያው ኦምና ታደለ ነግረውታል፡፡ እኛም እናንተ በሚመች መልኩ እንዲህ አቅርበነዋል፡፡ የውበቱ አባተ የእግርኳስ ህይወት በሰዎች ጭንቅላት ውስጥ መታተም የጀመረው ከአዲሱ ሚሌንየም ወዲህ ቢሆንም ግማሽ ደርዘን በሚሆኑ ክለቦች ውስጥ በተጫዋችነት አሳልፈዋል፡፡ዝርዝር

በ2015 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከሜዳው ውጪ ያልታጠበቀ ድል አስመዝግቦ የጨለመ የማለፍ ተስፋውን አለምልሟል፡፡ ማሊዎች ግብ በማስቆጠር ቅድሚያ የያዙት በ32ኛው ደቂቃ በባካሪ ሳኮ አማካኝነት ነበር፡፡ ብዙም ሳይቆይ በ36ኛው ደቂቃ ኡመድ ኡኩሪ ከጌታነህ ከበደ የተሸገረለትን ኳስ አስቆጥሮ ኢትዮጵያን አቻ አደረገ፡፡ የመጀመርያው ግማሽ የተጠናቀቀውም ጌታነህ ከበደ ኢትዮጵያን መሪ የምታደርግ ግብዝርዝር