ዋልያዎቹ (Page 3)

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የፊት፣ የመሐል እና የኋላ መስመር ሦስት ተጫዋቾች ቀለል ያለ ጉዳት ማስተናገዳቸው ተሰምቷል። ለኳታሩ የዓለም ዋንጫ ለማለፍ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የምድብ የማጣሪያ ጨዋታዎችን ካለንበት ወር መጨረሻ ጀምሮ እንደሚያደርግ ይታወቃል። ለምድቡ ሁለት የመክፈቻ ጨዋታዎች ዝግጅቱን በአዳማ ከተማ እያደረገ የሚገኘው ብሔራዊ ቡድኑም በአሠልጣኙ እንደወጣው የዝግጅት መርሐ-ግብር በቀን አንድ እና ሁለትዝርዝር

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫው ተሳትፎ እና በቀጣይ ስለሚገጥማቸው የምድብ ቡድኖች ዕውነታ ተከታዩን ጥንክር አዘጋጅተናል። 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በቀጣይ ዓመት በካሜሩን አስተናጋጅነት እንደሚከናወን ይታወቃል። የውድድሩ የምድብ ድልድልም ከደቂቃዎች በፊት በካሜሩን ያውንዴ በደማቅ ሥነ-ስርዓት ወጥቷል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም በምድብ አንድ ከአስተናጋጇ ካሜሩን፣ ቡርኪና ፋሶ እና ኬፕ ቬርድ ጋር መደልደሉ እርግጥ ሆኗል።ዝርዝር

በካሜሩን አስተናጋጅነት በሚካሄደው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር የሚሳተፉ ሀገራት የምድብ ድልድላቸውን አውቀዋል። ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ጀምሮ በካሜሩን በተከናወነው የእጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓት ላይ የካፍ ፕሬዝዳንት ፓትሪክ ሙሴፔን (ዶ/ር) ጨምሮ የፌዴሬሽን አመራሮች፣ የቀድሞ ተጫዋቾች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። የካፍ የውድድር ዳይሬክተር ሳምሶን አዳሙ የቀድሞ ተጫዋቾቹን ሳሙኤል ኢቶ፣ ጋዬል ኢንጋናሙቲ፣ ራባህ ማጄር፣ዝርዝር

ከስምንት ዓመታት በኋላ ወደ ትልቁ አህጉራዊ ውድድር የተመለሰው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የምድብ ተጋጣሚዎቹን አውቋል። በቀጣይ ዓመት በካሜሩን አስተናጋጅነት ለሚካሄደው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ማለፉ ይታወቃል። 24 ተሳታፊዎች ያሉበት ትልቁ የአህጉሩ ሀገራት ውድድር ከጥር 1 – 29 (ጃኑዋሪ 9 – ፌብሩዋሪ 6) ድረስ የሚደረግ ሲሆን ከደቂቃዎች በፊትዝርዝር

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ነገ ማለዳ ከሀገር ውጪ ጉዞ እንደሚያደርጉ ታውቋል። ለኳታሩ የዓለም ዋንጫ ለመብቃት ከፊቱ የምድብ የማጣሪያ ጨዋታዎች የሚጠብቁት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአዳማ መቀመጫውን በማድረግ ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ ይታወቃል። የብሔራዊ ቡድኑ አሠልጣኝ ውበቱ አባተም ቡድኑን በቀን ሁለት ጊዜ እያዘጋጁት የሚገኝ ቢሆንም ነገ ማለዳ ግን ወደ ካሜሩንዝርዝር

በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጋና ኢትዮጵያን የምታስተናግድበት ጨዋታ በሞሮኮ ዳኞች ይመራል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለ2022 የካታር ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከዚምባብዌ ፣ ጋና እና ደቡብ አፍሪካ ጋር መደልደሏ ይታወሳል፡፡ በያዝነው ወር መጨረሻ የማጣሪያ ጨዋታዎቹ የሚጀመሩ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያም ከጋና ጋር ለምታደርገው መርሀግብር በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ መሪነት በአዳማ ከተማ ዝግጅት በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡የመጀመሪያውንዝርዝር

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት እና ዋና ፀሐፊው ወደ ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር አቅንተዋል። በካሜሩን አስተናጋጅነት በቀጣይ ዓመት በሚዘጋጀው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ተሳታፊ የሆነችው ኢትዮጵያ በየትኛው ምድብ ትደለደላለች የሚለውን ነገ አመሻሻሽ ላይ በካሜሩን ያውንዴ ከተማ የሚታወቅ ይሆናል። በዚህ ሥነ ሥርዓት ላይ ለመታደምም የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ ጅራ እና ዋና ፀሐፊውዝርዝር

ከሦስት ቀናት በፊት በልምምድ ላይ ጉዳት ያጋጠመው የአማካይ መስመር ተጫዋች ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ስብስብ ውጪ ሆኗል። በአሠልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለኳታሩ የዓለም ዋንጫ ለማለፍ ከጋና እና ዚምባቡዌ ጋር ከያዝነው ወር መጨረሻ ጀምሮ ጨዋታ ያደርጋል። ከሳምንት በፊት ለ28 ተጫዋቾች ጥሪ በማድረግ ልምምድ የጀመረው ቡድኑም ማክሰኞ ወደ አዳማ በማቅናትዝርዝር

በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ ተጋጣሚ የሆነችው ጋና በዛሬው ዕለት ስብስቧን ይፋ አድርጋለች። በኳታር አስተናጋጅነት በሚካሄደው የ2022 ዓለም ዋንጫ ውድድር ላይ ለመሳተፍ የአፍሪካ ሀገራት ከያዝነው ወር መጨረሻ ጀምሮ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ለዚሁ ውድድር ለመብቃት በምድብ ሰባት ከጋና፣ ደቡብ አፍሪካ እና ዚምባቡዌ ጋር የተደለደለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም የምድብዝርዝር

የፊፋ ወርሀዊ የሀገራት ደረጃ ዛሬ ይፋ ሲሆን የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን የተቀመጠበት ደረጃም ታውቋል። በዚህ ወር በፊፋ እውቅና እንደተሰጠው በተነገረው የሴካፋ ከ23 ዓመት በታች ውድድር ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ137ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ይህም ባለፈው ወር ከነበረበት ደረጃ ጋር ተመሳሳይ ነው። ቡድኑ ከአፍሪካ ሀገራት ደግሞ በ39ኙ ተበልጦ 40ኛ ደረጃዝርዝር