ዋልያዎቹ (Page 69)

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለኢኳቶርያል ጊኒው የ2015 የአፍሪካ ዋንጫ 4ኛ ምድብ ማጣርያ ጨዋታ ትላንት ምሽት ወደ አልጄርያ ተጉዟል፡፡ ቡድኑ ማሊን ከሜዳው ውጪ አሸንፎ የማለፍ ተስፋውን ነፍስ የዘራበት ሲሆን ተጋጣሚው አልጄርያ ደግሞ ያደረገቻቸውን ጨዋታዎች በሙሉ አሸንፋ ከወዲሁ ለአፍሪካ ዋንጫው ማለፏን አረጋግጣለች፡፡ አሰልጣኝ ማርያኖ ባሬቶ 21 ተጫዋቾችን ለአልጄርያው ጨዋታ የመረጡ ሲሆን ጌታነህ ከበደዝርዝር

የሃገራችን የህትመት ውጤቶች ዛሬ ማለዳ ለህትመት ያበቋቸው የኢትዮጵያ እግርኳስን የሚመለከቱ ጉዳዮችን እንዲህ አጠናቅረናቸዋል፡፡ ሪፖርተር ሪፖርተር በዛሬው እትሙ የጀርባ ገፅ ቅዱስ ጊዮርጊስ በብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ማርያኖ ባሬቶ ላይ ክስ ሊመሰርት እንደሚችል የሚያትት ዘገባ ይዞ ወጥቷል፡፡ አሰልጣኙ በሁለተኛው ሳምንት ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀዋሳ ከነማን ያስተናገደበትን ጨዋታ በስታድየም ተገኝነተው የተከታተሉ ሲሆን አይዛክ ኢሴንዴ በታፈሰዝርዝር

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በካምፓላ ከዩጋንዳ ብሄራዊ ቡድን ጋር ባደረገው የወዳጅነት ጨዋታ 3-0 ተሸንፏል፡፡ የዩጋንዳው ካዎዎ ስፖርት ያዘጋጀው የጨዋታ ሪፖርት ይህንን ይመስላል፡፡ UGANDA WHIPS ETHIOPIA IN INTERNATIONAL FRIENDLY by David Isabirye – Kawowo Sports Uganda Cranes has warmed up for the upcoming AFCON 2015 Group E qualifier against Ghana with aዝርዝር

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን 27 አባላትን ይዞ ወደ ካምፓላ አምርቷል፡፡ በነገው እለትም በናምቡሊ ስታድየም ከዩጋንዳ ብሄራዊ ቡድን ጋር የወዳጅነት ጨዋታውን ያደርጋል፡፡ ዋና አሰልጣኝ ማርያኖ ባሬቶ ኢንቴቤ አየር ማረፍያ ሲደርሱ ከካዎዎ ስፖርት ድረ-ገፅ በሰጡት አስተያየት ‹‹ ዩጋንዳ በምስራቅ አፍሪካ ከሚገኙ ጠንካራ ሃገራት አንዷ ናት፡፡ ብሄራዊ ቡድኑን አከብራለሁ ፤ ነገር ግን እዚህ የመጣነውዝርዝር

  አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜ ካፈራቻቸው ድንቅ አሰልጣኞች አንዱ ናቸው፡፡ አሰልጣኙ ስላሳለፉት የእግርኳስ ህይወት እና ስለወደፊቱ አላማቸው ለሶከር ኢትዮጵያው ኦምና ታደለ ነግረውታል፡፡ እኛም እናንተ በሚመች መልኩ እንዲህ አቅርበነዋል፡፡ የውበቱ አባተ የእግርኳስ ህይወት በሰዎች ጭንቅላት ውስጥ መታተም የጀመረው ከአዲሱ ሚሌንየም ወዲህ ቢሆንም ግማሽ ደርዘን በሚሆኑ ክለቦች ውስጥ በተጫዋችነት አሳልፈዋል፡፡ዝርዝር

በ2015 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከሜዳው ውጪ ያልታጠበቀ ድል አስመዝግቦ የጨለመ የማለፍ ተስፋውን አለምልሟል፡፡ ማሊዎች ግብ በማስቆጠር ቅድሚያ የያዙት በ32ኛው ደቂቃ በባካሪ ሳኮ አማካኝነት ነበር፡፡ ብዙም ሳይቆይ በ36ኛው ደቂቃ ኡመድ ኡኩሪ ከጌታነህ ከበደ የተሸገረለትን ኳስ አስቆጥሮ ኢትዮጵያን አቻ አደረገ፡፡ የመጀመርያው ግማሽ የተጠናቀቀውም ጌታነህ ከበደ ኢትዮጵያን መሪ የምታደርግ ግብዝርዝር