ሁለት የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎችን ለማድረግ ወደ እስራኤል የተጓዘው ብሔራዊ ቡድኑ በሠላም ስፍራው ላይ መድረሱ ተገልጿል። በኢትዮጵያ እና እስራኤል እግርኳስ ፌዴሬሽኖች ውይይት የተገኘው የሁለቱ ሀገራት ከ17 ዓመት ብሔራዊ ቡድኖች የአቋም መለኪያ ጨዋታ ነገ እና ሀሙስ አመሻሽ እንደሚከናወን መገለፁ ይታወቃል። እነዚህን ጨዋታዎች ለማድረግ ትላንት ለሊት ወደ እስራኤል የተጓዘው የኢትዮጵያ ልዑካንም ለአራት ሰዓትContinue Reading

የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዙር የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ከመቼ እስከ መቼ እንደሆነ ተገልጿል። በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን እና በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር ሥር የሚገኙ የዘንድሮ ዓመት ውድድሮች እየተገባደዱ (የተጠናቀቁም እንዳለ ልብ ይሏል) እንደሆነ ይታወቃል። በየእርከኑ የሚገኙ ውድድሮች ሲገባደዱም ይፋዊው የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ከመከፈቱ በፊት ክለቦች ተጫዋቾችን ለማስፈረም ቅድመ ስምምነት እየፈፀሙ እንደሆነContinue Reading

በአሠልጣኝ ስታንሊ ኦኩምቢ የሚመራው የኬንያ ብሔራዊ ቡድን በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው ለሴካፋ ውድድር የሚያገለግሉትን ተጫዋቾች ጠርቷል። በአስራ አንዱ የቀጠናው ብሔራዊ ቡድኖች እና በአንድ ተጋባዥ ቡድን (ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ) መካከል የሚደረገው የ2021 የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ሊጀመር ከሁለት ሳምንት ያነሰ ጊዜ ቀርቶታል። በውድድሩ ለመሳተፍ ማረጋገጫ የሰጡ ብሔራዊ ቡድኖችም ለተጫዋቾቻቸው ጥሪContinue Reading

አስራ ሁለት ሀገራት በሚወዳደሩበት የሴካፋ ውድድር ላይ በተጋባዥነት የምትሳተፈው ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ለተጫዋቾቿ ጥሪ ማድረጓ ተገልጿል። በሀገራችን ኢትዮጵያ ከሰኔ 26 – ሐምሌ 12 ድረስ በሚደረገው የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ (ሴካፋ) ውድድር ላይ የሚሳተፉ የቀጠናው ብሔራዊ ቡድኖች ስብስባቸውን እያሳወቁ ዝግጅት እያደረጉ እንደሆነ ይታወቃል። ከዚህ ቀደምም ኢትዮጵያ፣ ዩጋንዳ እና ቡሩንዲ ስብስባቸውንContinue Reading

በሻላ እግርኳስ ማኅበር አዘጋጅነት ለቀናት በስምንት ቡድኖች መካከል ሲካሄድ የቆየው የአሰግድ ተስፋዬ የመታሰቢያ ውድድር በኢትዮ አፍሪካ አሸናፊነት ተገባዷል። የቀድሞ ድንቅ አጥቂ አሰግድ ተስፋዬ በድንገት ህይወቱ ያለፈበትን አራተኛ ዓመት ለመዘከር በሁለት ምድብ ተከፍሎ ስምንት ቡድን በመያዝ ሃያ ሁለት በሚገኘው አስራ አንድ ቀበሌ ሜዳ በየጨዋታው ቁጥሩ በርካታ የሆነ ተመልካች እየታደመበት ሲዝናና የቆየበትContinue Reading

በዛሬው ዕለት ከ28 ተጫዋቾች ሰባቱን በወዳጅነት ጨዋታ የቀነሱት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ አምስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ጠርተዋል፡፡ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የሴካፋ ከ23 ዓመት በታች ዋንጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በካፍ የልህቀት ማዕከል ማረፊያውን አድርጎ በመዘጋጀት ላይ ይገኛል፡፡ ከዝግጅት ጊዜው አስቀድሞ ለ35 ተጫዋቾች ጥሪ የቀረበላቸው ሲሆን በተለያዩ ምክንያቶች ቁጥራቸው ወደ ሀያ ስምንት ዝቅ ብሎContinue Reading

በኢትዮጵያ ለሚደረገው የሴካፋ ውድድር ዝግጅቱን እያደረገ ከሚገኘው የዋልያው ስብስብ በዛሬው ዕለት ሰባት ተጫዋቾች መቀነሳቸው ታውቋል። ከቀናት በፊት ለምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ (ሴካፋ) ውድድር ለ35 ተጫዋቾች ጥሪ አድርጎ ዝግጅቱን እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዛሬው ዕለት የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ማድረጉን ቀደም ብለን መዘገባችን ይታወቃል። የቡድኑ አሠልጣኝ ውበቱContinue Reading

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የሴካፋ ዋንጫ እየተዘጋጀ የሚገኘው የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የአቋም መለኪያ ጨዋታ አድርጓል። በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመራው የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ቡድን ከሳምንት በፊት 28 ተጫዋቾችን በመያዝ አያት በሚገኘው የካፍ የልህቀት ማዕከል ሲዘጋጅ መቆየቱ ይታወቃል። በዛሬው ዕለትም የመጨረሻዎቹን ተጫዋቾችን ለመለየት በአዲስ አበባ ስታዲየም ረፋድ ላይ ከኢትዮContinue Reading

በስድስት ዘርፎች የስፖርት ዞን የዓመቱ የዕዉቅና ፕሮግራም አሰጣጥ አስመልክቶ ዛሬ በቤዝ ኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል። ያለፉትን ስድስት ዓመታት በሀገር ውስጥ እግርኳስ ላይ ትኩረቱን በማድረግ በፋና ኤፌም 98.1 ከሰኞ እስከ አርብ በጋዜጠኛ ሰዒድ ኪያር እና ጋዜጠኛ መኳንንት በርሄ ዋና አዘጋጅነት ተሰናድቶ የሚቀርበው ስፖርት ዞን በእግርኳሱ ዘርፍ ኮከቦችን ለመሸለም ከወራትContinue Reading

በተጠናቀቀው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ መሳተፍ ያልቻለው ስሑል ሽረ በቀጣይ ዓመት ወደ ውድድር ለመመለስ እንቅስቃሴ ጀምሯል። ከዓመት በፊት በትግራይ ክልል በተከሰተው የፀጥታ ችግር ምክንያት በ2013 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መሳተፍ ያልቻሉት መቐለ 70 እንደርታ፣ ስሑል ሽረ እና ወልዋሎ ዓ/ዩ በቀጣይ ዓመት በሊጉ የመመለሳቸው ነገር እስካሁን የለየለት መልስ አላገኘም። የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግContinue Reading