ዜና

ሀይቆቹ የሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር ማጠናቀቃቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች፡፡ በአሠልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ እየተመሩ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በመቀመጫ ከተማቸው እየሰሩ የሚገኙት ሀዋሳ ከተማዎች የሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር እንዳጠናቀቁ ታውቋል፡፡ የመጀመሪያው ወደ አሳዳጊ ክለቡ የተመለሰው ተጫዋች ተስፉ ኤልያስ ነው፡፡ የግራ መስመር ተከላካይ የሆነው ይህ ተጫዋች ከሀዋሳ ከተማ የታዳጊ ቡድን ከተገኘ በኋላ ለዋናው ቡድንም ጭምርዝርዝር

በአሠልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ የሚመሩት መከላከያዎች ከ17 ዓመት በታች ቡድናቸው ጀምሮ ሲያገለግላቸው የነበረውን አማካይ ውል አራዝመዋል። ዛሬ በሚጀመረው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ውድድር ላይ የሚሳተፉት መከላከያዎች የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ቢሾፍቱ ላይ ካከናወኑ በኋላ ለመዲናው ውድድር በትናንትናው ዕለት አዲስ አበባ ገብተዋል። ቡድኑ ትናንት አዲስ አበባ እንደገባም የአማካይ ተጫዋቹ አቤል ነጋሽን ውል በአንድዝርዝር

የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ላይ እየተካፈለ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከደቡብ አፍሪካ ጋር ላለበት ጨዋታ የሊቢያ ዜግነት ያላቸው ዳኞች ተመድበዋል፡፡ በኳታር አስተናጋጅነት ለሚደረገው የ2022 የዓለም ዋንጫ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎችን እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከምድቡ ከተደለደሉት ጋና እና ዚምባብዌ ጋር ከሜዳው ውጪ እና በሜዳው ያከናወነ ሲሆን በሦስተኛው የማጣርያ መርሀግብር መስከረምዝርዝር

ከሳምንታት በፊት ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሚያደርገው ዝውውር የከሸፈው ወጣቱ አጥቂ ጅማ አባጅፋርን ለመቀላቀል በቃል ደረጃ የተስማማበትን ስምምነት ህጋዊ አድርጓል። ከኢትዮጵያ መድህን የወጣት ቡድን ተገኝቶ ዋናውን ቡድን ያገለገለው ወጣቱ አጥቂ መሐመድ ኑር ባለንበት የዝውውር መስኮት ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ይዘዋወራል ተብሎ በስፋት ሲነገር መቆየቱ አይዘነጋም። ነገርግን ተጫዋቹ ከክለቡ ጋር ስምምነት ላይ ሳይደርስዝርዝር

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የትጥቅ አጋር የሆነው ኡምብሮ ለቡድኖቹ ያመረተውን አዲስ ትጥቅ ፌዴሬሽኑ ይፋ አድርጓል። 2019 ላይ በተለያየ እርከን ለሚገኙ የወንድ እና ሴት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድኖች የመጫወቻ እንዲሁም የመለማመጃ ትጥቅ ለማቅረብ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር የተስማማው አምብሮ በቅርቡ ለአራት ዓመታት ከብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ጋር አብሮ ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሱ ይታወቃል። እንግሊዝዝርዝር

ኪጋሊ ላይ ለዓለም ዋንጫ አንደኛ ዙር ማጣሪያ ሩዋንዳን የገጠመው የኢትዮጵያ የሴቶች ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን 4-0 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችሏል። በጨዋታው ሙሉ ብልጫ የነበረው የብሔራዊ ቡድኑ ሙከራዎች በ3ኛው ደቂቃ ቤተልሄም በቀለ ከማዕዘን ምት በግንባሯ ባደረገችው ሙከራ የጀመረ ነበር። በቡድን ፍጥትነትም ሆነ በአካላዊ ቅልጥፍና ከተጋጣሚያቸው እጅግ የተሻሉ የነበሩት ኢትዮጵያዊያኑዝርዝር

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከሩዋንዳ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ የሚጠቀምበት አሰላለፍ ይፋ ሆኗል። በአሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል የሚመራው ከ20 ዓመት ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በዓለም ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ዋንጫ ማጣርያ ሩዋንዳን ለመግጠም ኪጋሊ የሚገኝ ሲሆን በ10፡00 ለሚያደርጉት ጨዋታ የሚጠቀሙበትን አሰላለፍ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል። ግብ ጠባቂ እየሩሳሌም ሎራቶ  ተከላካዮች  ብዙዓየሁ ታደሰዝርዝር

ወላይታ ድቻ የአሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም ረዳትን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል፡፡ አዳዲስ እና ነባር ተጫዋቾችን በማጣመር የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን በመቀመጫ ከተማው ሶዶ እየሰራ የሚገኘው ወላይታ ድቻ በየትኛውም የቅድመ ውድድር ዋንጫ ላይ በበጀት እጥረት የተነሳ እንደማይሳተፍ ሶከር ኢትዮጵያ ያረጋገጠች ሲሆን በቀጣዩ ቀናት በሚገኙ የአቋም መፈተሻ የወዳጅነት ጨዋታዎች ግን ራሱን ለመፈተሽ እቅድ ይዟል፡፡ዝርዝር

አምስት የፕሪምየር ሊግ ክለቦችን ተሳታፊ የሚያደርገው የሲዳማ ጎፈሬ ዋንጫ የዕጣ ማውጣት ስነ ስርአት በዛሬው ዕለት በሀዋሳ ሌዊ ሪዞርት ተካሂዷል፡፡ በሲዳማ ክልል እግርኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት በጎፈሬ የትጥቅ አምራች ተቋም ስፖንሰር አድራጊነት የ2014 የሲዳማ ጎፈሬ ዋንጫ በሚል ስያሜ በአምስት የፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች መካከል በሀዋሳ ከተማ ቀደም ተብሎ ከተያዘለት ቀን በአንድ ወደፊትዝርዝር

ሀድያ ሆሳዕና የመስመር አጥቂውን በአንድ ዓመት ውል ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል፡፡ በአዲሱ አሰልጣኙ ሙሉጌታ ምህረት እና ረዳቶቹ መሪነት ከሳምንታቶች በፊት በመቀመጫው ሆሳዕና ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን የጀመረው ሀድያ ሆሳዕና በሲዳማ ጎፈሬ ዋንጫ ላይ ለመካፈል ከአንድ ቀን በፊት ወደ ሀዋሳ በመምጣት በሴንትራል ሆቴል ማረፊያውን በማድረግ በርከት ያሉ አዳዲስ ፈራሚዎችን ከነባሮቹ ጋር በማቀናጀትዝርዝር