ዜና (Page 1,088)

ኤሌክትሪክ በተጫዋቾች ዝውውር ተጠምዷል፡፡ እስካሁን ከ5 ተጫዋቾች ጋር ሲስማማ የ7 ተጫዋቾችንም ውል አድሷል፡፡ ኤሌክትሪክ ለማስፈረም ከተስማማቸው ተጫዋቾች መካከል የንግድ ባንኩ የግራ መስመር ተከላካይ አለምነህ ግርማ የመጀመርያው ተጫዋች ሲሆን 1.1 ሚልዮን ብር ለ2 አመት ሊከፈለው መስማማመቱ ተነግሯል፡፡ የወላይታ ድቻዎቹ ተስፋዬ መላኩ እና አማካዩ አሸናፊ ሽብሩ ሌሎች ለኤሌክትሪክ ለመፈረም የተስማሙ ተጫዋቾች ሲሆኑዝርዝር

የግብፁ ክለብ ኢ.ኤን.ፒ.ፒ.አይ የኢትዮጵያዊው አጥቂ ኡመድ ኡኩሪ ፈላጊ ክለብ መሆኑ ተነግሯል፡፡ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የነበረው ውል ሰኔ 30 ላይ የተጠናቀቀው ኡመድ ወደ ኢ.ኤን.ፒ.ፒ.አይ ሊያመራ ይችላል፡፡ በግብፅ ፕሪሚየር ሊግ በሶስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ኢ.ኤን.ፒ.ፒ.አይ በ2016 በአፍሪካ ኮንፌድሬሽን ካፕ ተሳታፊ መሆኑ እና በገንዘብ አቅሙ ጠንካራ መሆኑ ኡመድን ወደ ክለቡ እንዲዛወር ምክንያት ሊሆንዝርዝር

ጋቶች ፓኖም በቤልጂየም እና ቱርክ ክለቦች ዕይታ ውስጥ ገብቷል፡፡ ስማቸው ያልተጠቀሰው ክለቦቹ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እና የኢትዮጵያ ቡና የተከላካይ አማካይ ጋቶችን ለመውሰድ ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው ተብሏል፡፡ በቤልጂየም ሊግ የሚወዳደር አንድ ክለብ ፣ በቱርክ ሱፐር ሊግ እና የቱርክ ቲ.ኤፍ.ኤፍ አንደኛ ሊግ (አንደኛ ዲቪዚዮን) የሚወዳደሩ ሁለት ክለቦች ጋቶች ከሌሴቶ እና ኬንያ ጋርዝርዝር

  በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን የመጀመርያ አጋማሽ አስገራሚ አቋም ያሳየው ሲዳማ ቡና ቡድኑን ከወዲሁ እያጠናከረ ይገኛል፡፡ እንደ ስፖርት ፋና ዘገባ ከሆነ ሲዳማ ቡና የደቡብ ፖሊሱን አማካይ ሚካኤል ለማን አስፈርሟል፡፡ ተጫዋቹ ከሁሉም ክለቦች ቀድሞ ወደ ብሄራዊ ሊጉ ማጠቃለያ ውድድር ማለፉን ባረጋገጠው ደቡብ ፖሊስ ውስጥ ድንቅ አመት አሳልፏል፡፡ ቡድኑ ከአርባምንጭ ከነማ 2 ተጫዋችዝርዝር

በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ላለመውረድ ሲታገል የነበረው ሀዋሳ ከነማ የወሳኝ ተጫዋቾቹን ኮንትራት አድሷል፡፡ አምበሉ ሙሉጌታን ጨምሮ 5 ተጫዋቾቹን ውል ማደሱም ተነግሯል፡፡ አጥቂው ተመስገን ተክሌ በቡድኑ ከፍተኛው ተከፋይ ያደረገውን ኮንትራት ያደሰ ሲሆን በ2 አመት ውስጥ 1.3 ሚልዮን ብር ሊከፈለው ተስማምቷል፡፡ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ድንቅ ብቃታቸውን ያሳዩት ጋዲሳ መብራቴ እና ታፈሰ ሰለሞንን ኮንትራትዝርዝር

የሲዳማ ቡናው የመስመር አማካይ እንዳለ ከበደ ወደ ቀድሞ ክለቡ አርባምንጭ ከነማ ሊዘዋወር እንደሚችል ተነግሯል፡፡ በ2004 አርባምንጭ ከነማን ለቆ ወደ ሲዳማ ቡና ያቀናው እንዳለ ከበደ በይርጋለሙ ክለብ ዘንድሮ ያሳየው ድንቅ እንቅስቃሴ ለብሄራዊ ቡድን እስከመመረጥም አድርሶታል፡፡ ተጫዋቹ በአርባምንጭ ከነማ በነበረበት ወቅት ከአሰልጣኙ ጋር በነበረው አለመግባባበት ምክንያት ወደ ሲዳማ እንዳመራና አሁን አሰልጣኝ አለማየሁዝርዝር

  ደደቢት የውጭ ዜጋ አሰልጣኝ ለመቅጠር እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡ ክለቡ የፖላንድ እና የፔሩ ዜግነት ያላቸው አሰልጣኞችን ሲቪ እየተመለከተ ሲሆን ከሁለቱ አንዱ የክለቡን ፍላጎት የሚያሟሉ ከሆነ ለሰማያዊው ጦር ይፈርማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ክለቡ ከአሰልጣኝ ቅጥር ጋር በተያያዘ ሃገር ውስጥ ያሉ አሰልጣኞችን ሊቀጥር የሚችለው ከውጭ ሊያመጣቸው ያቀዷቸው አሰልጣኞች ካልተሳኩ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ እ4ስካሁን የ2 የሃገርዝርዝር

  ኢትዮጵያ ቡና የግብ ጠባቂ ችግሩን ለመቅረፍ ከውጭ ግብ ጠባቂ ለማምጣት እንቅስቃሴ መጀመሩ ታውቋል፡፡ ቡና በዲስፕሊን ግድፈት ምክንያት ሙሴ ገብረኪዳንን ማገዱ የሚታወስ ሲሆን ተጫዋቹ ክለቡን የመሰናበት እድሉ ከፍተኛ በመሆኑ በቡድኑ ውስጥ ልምድ ያለው ግብ ጠባቂ የ1 አመት ቀሪ ኮንትራት የሚቀረው ጌቱ ተስፋዬ ብቻ ነው፡፡ የክለቡ ቴክኒክ ዳይሬክተር እና አዲሱ አሰልጣኝዝርዝር

  በ2015 የካጋሜ ካፕ ላይ የሚሳተፈው አዳማ ከነማ ተጫዋቾችን እያስፈረመ ነው፡፡ ቡድኑ የ3 ተጫዋቾችን ፊርማ ማግኘቱንም አረጋግጧል፡፡ የወላይታ ድቻው አማካይ ብሩክ ቃልቦሬ በ1.1 ሚልዮን ብር ለ2 አመት የተስማማ ሲሆን ተጫዋቹ ክለቡን እንዲቀላቀል አሰልጣኙ አሸናፊ በቀለ ከፍተኛውን ሚና እንደተጫወቱ ተነግሯል፡፡ ብሩክ ከብሄራዊ ቡድኑ ጋር በቻን አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የነበረ ሲሆን ከኬንያዝርዝር

ወላይታ ድቻ በሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ ያደረጉት ተጫዋቾቹን ማጣቱን ቀጥሏል፡፡ የብሄራዊ ቡድኑ አጥቂ ባዬ ገዛኸኝ ወደ መከላከያ ያመራ ሲሆን ለ2 አመት ውስጥ 1.2 ሚልዮን ሊከፈለው ተስማምቷል፡፡ ሌላው የቡድኑ ወሳኝ አማካይ የሆነው ብሩክ ቃልቦሬም ማረፊያውን አዳማ ከነማ አድርጓል፡፡ በመከላከያ እና ባንክ ሲፈለግ የነበረው ብሩክን ለማግኘት አዳማ ከነማ 1.1 ሚልዮን ብር ለ2 አመትዝርዝር