ዜና (Page 1,090)

  የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ዛሬ በኢንተር ኮንትኔንታል አዲስ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ በመጪው ቅዳሜ ከኬንያ ጋር የሚያደርጉትን የቻን ማጣርያ የመልስ ጨዋታ በተመለከተ ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡ የአሰልጣኙን ንግግሮች ለድረ-ገፃችን አንባብያን በሚሆን መልኩ እንዲህ አሰናድተነዋል፡፡   ስላልተመረጡ ተጫዋቾች ‹‹ ቡድኑ በሀዋሳ ልምምድ ሲያደርግ የነበረው ከረቡእ እለት ጀምሮ ቢሆንም እኔዝርዝር

በመጪው እሁድ ከኬንያ አቻው ጋር ለቻን ቅድመ ማጣርያ የመልስ ጨዋታ በናይሮቢ የሚያደርገው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በሀዋሳ ዝግጅቱን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ወደ ሀዋሳ ያቀኑ ዋልያዎቹ ሳውዝ ስታር ሆቴል የተቀመጡ ሲሆን ትላንት ብቻ(ሰኞ) በቀን 2 ጊዜ ልምምድ አድርገዋል፡፡ የግንባታው 2/3 ኛ ላይ የደረሰው አዲሱ የሀዋሳ ስታድየምም የልምምድ ፕሮግራሙ እየተካሄደበት ይገኛል፡፡ዝርዝር

ኢትዮጵያ የሴካፋ ሲኒየር ቻሌንጅ ዋንጫን በህዳር ወር እኝደምታዘጋጅ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን ፕሬዝደንት ጁነዲ ባሻ በግል የትዊተር ገፃቸው አስተውቀዋል፡፡ የሴካፋ ዋንጫን በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የክልል ከተሞች ለማዘጋጀት መታሰቡን ጁነዲ ጨምረው አስታውቀዋል፡፡ ኢትዮጵያ የሴካፋ ዋንጫን ስታዘጋጅ ይህ ለአራተኛ ግዜ ነው፡፡ ከዚህ በፊት በታህሳስ 1980፣ በህዳር 1997 እና 1999 ውድድሩን አዘጋጅታለች፡፡ የቻንዝርዝር

ኢትዮጵያዊው አጥቂ ፍቅሩ ተፈራ ለህንዱ ሂሮ ሱፐር ሊግ ለሚወዳደረው ቺኔይን ፈርሟል፡፡ ያለፉትን 4 ወራት በዊትስ ቆይታ አድርጎ 1 ግብ ማስቆጠር የቻለው ፍቅሩ የውል ማረዘሚያ ስላልቀረበለት ቤድቬስት ዊትስን ለቋል፡፡ የቀድሞ የአዳማ ከነማ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኦርላንዶ ፓይሬትስ እና ሱፐር ስፓርት ዮናይትድ አጥቂ ቀጣይ ማረፉያው የህንዱ ቺኔይን ሆኗል፡፡ የህንድ ሂሮ ሱፐር ሊግን የመጀመሪያዝርዝር

ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ጌታነህ ከበደ ከደቡብ አፍሪካው ክለብ ቤድቬስት ዊትስ ጋር መለያየቱ ታውቋል፡፡ ያላፈውን የውድድር ዘመን በተቀማጭ ወንበር ላይ ያሳለፈው የቀድሞ የደቡብ ፓሊስ እና ደደቢት አጥቂ ከዊትስ ጋር እንደሚለያይ ቀደም ብሎ ይታወቀ ነበር፡፡ ዊትስ ጌታነህን በውሰት ለሌላ ክለብ ለመስጠት ወይም ለመሸጥ እንደሚፈልግ ከዚህ በፊት መዘገቡ የሚታወስ ነው፡፡ የአንድ ዓመት ቀሪ ውልዝርዝር

የኢትዮጵያ ዋንጫ (ጥሎ ማለፍ) ሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ዛሬ ሲቀጥሉ ሀዋሳ ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወደ ግማሽ ፍፃሜ አልፈዋል፡፡ በ9፡00 ኤሌክትሪክን የገጠመው ወላይታ ድቻ 1-0 አሸንፏል፡፡ የወላይታ ድቻን የድል ግብ አላዛር ፋሲካ በ68ኛው ደቂቃ በሚታወቅበበት የግንባር ኳስ ከመረብ አሳርፏል፡፡ በ11፡00 ኢትዮጵያ ቡናን የገጠመው ሀዋሳ ከነማ 2-1 አሸንፏል፡፡ ኢትዮጵያ ቡና ቢንያም አሰፋዝርዝር

በኢትዮጵያ ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ የአምናው የፍፃሜ ተፋላሚ ቅዱስ ጊዮርጊስ አርባንጭ ከነማን አሸነፎ ግማሽ ፍፃሜውን ሲቀላቀል መከላከያ ሲዳማን በቀላሉ አሸንፎ ግማሽ ፍፀሜውን የተቀላቀለ ሁለተኛው ቡድን ሆኗል፡፡ በ9፡00 አርባምንጭ ከነማን የገጠመው ቅዱ ጊዮርጊስ 1-0 አሸንፏል፡፡ ፈረሰኞቹ በጨዋታው ሙሉ የጠጨዋ ብልጫ የነበራቸው ሲሆን በርካታ የግብ ሙከራዎችን ማድረገግ ችለዋል፡፡ በአንፃሩ አርባምንጭ ከነማዎች ወደ መለያዝርዝር

ኢትዮጵያዊው አማካይ ሽመልስ በቀለ ማክሰኞ ምሽት በተደረገ የግብፅ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ክለቡ ፔትሮጀት በአል አሃሊ በተሸነፈበት ጨዋታ ግብ አስቆጥሯል፡፡ በስዊዝ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሽመልስ በቀለ በስምንተኛው ደቂቃ ግብ ማስቆጠር ችሏል፡፡ ሽመልስ ለፔትሮጀት ሁለተኛ ግብ ማስቆጠር የሚችልበትን አጋጣሚ አግኝቶ የነበረ ቢሆንም የአሃሊው ግብ ጠባቂ አህመድ አድል አምክኗታል፡፡ ጨዋታውን አል አሃሊ በዋሊድዝርዝር

ወደ ፕሪሚየር ሊግ ለማለፍ የሚደረገው የመጨረሻ ውድደር ከሐምሌ 14 ጀምሮ በድሬዳዋ ከተማ የሚካሄድ ሲሆን ከ24 ቡድኖች መካከል 1ኛ እና 2ኛ የሚወጡ ቡድኖች ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ይሸጋገራሉ፡፡ በ8 ዞኖች ተከፍሎ እየተካሄደ ያለው የ2007 የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሊግ ወደ መጠናቀቂያው እየተቃረበ ነው፡፡ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ባደረሰን መረጃ መሰረት ቡድኖቹ የሚገኙበት ወቅታዊ ሁኔታ የሚከተለውንዝርዝር

የኢትዮጵያዊው አጥቂ ሳላዲን ሰዒድ ወኪል የሆኑት ግብፃዊው አብዱልራህማን መግዲ ሳላዲን ወደ አልጄሪያው ክለብ ኤምሲ አልጀርስ ሊያቀና ነው የሚሉትን ዜናዎች ከእውነት የራቀ በማለት አጣጥለዋል፡፡ አብዱልራህማን መግዲ ስለተጫዋቹ ለሶከር ኢትዮጵያ በሰጡት አስተያየት “ሳላ ወደ አልጄሪያ እየሄደ አይደለም፡፡ በአሁን ሰዓት ስለዝውውሩ ማውራት አልችልም፡፡ ስለዝውውሩ የተነሳው ዘገባ ከእውነት የራቀ ነው፡፡” ብለዋል፡፡ በግብፁ አል አሃሊዝርዝር