ዜና (Page 1,097)

በቅዱስ ጊዮርጊስ የውድድር ዘመኑ የቻምፒዮንነት ጉዞ ቁልፍ ሚና የነበረው በኃይሉ አሰፋ በግሉ ለ3ኛ ተከታታይ የውድድር ዘመን የሊጉን ዋንጫ አንስቷል፡፡ ፈጣኑ የመስመር አማካይ ከዛሬው ጨዋታ በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጠው አስተያየት የድላቸውን ምስጢር ያብራራል፡፡ ‹‹ በ2007 ብዙ ፈተናዎችን አሳልፈናል፡፡ ጥሩ አጀማመር ማድረግ አልቻልንም ነበር፡፡ በሁለተኛው ዙር ክለቡ በድክመቶቹ ላይ ሰርቷል፡፡ እኛም ድክመቶቻችንን እያረምንዝርዝር

  የቀድሞው የደቡብ ፖሊስ እና ደደቢት የአጥቂ መስመር ተጫዋች ጌታነህ ከበደ ከቢድቭስት ዊትስ ጋር የመቀጠሉ ነገር አጠራጣሪ መሆኑን ከደቡብ አፍሪካ የሚወጡ ዘገባዎች ጠቁመዋል። ጌታነህ በብሉምፎንቴይኑ ክለብ ለተጨማሪ አንድ አመት የሚያቆየው ኮንትራት ቢኖረውም ክለቡ ተጫዋቹን ለማቆየት ፍላጎት እንደሌለው ነው የተነገረው። ጌታነህ በ2005 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በደደቢት ባሳየው ድንቅ አቋም እናዝርዝር

በኢትዮጵያ ፕሪሚር ሊግ 24ኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ አርባምንጭ ከነማን 3-1 አሸንፎ የ2007 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቻምፒዮንነቱን አረጋግጧል፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስን የአሸናፊነት ግቦች በድንቅ አቋም ላይ የሚገኘው አዳነ ግርማ በጨዋታ እና በፍፁም ቅጣት ምንት እንዲሁም አማካዩ ምንተስኖት አዳነ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡ የአርባምንጭን ብቸኛ ግብ ፀጋዬ አበራ ከመረብ ሲያሳርፍ ተሸመ ታደሰዝርዝር

  በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 24ኛ ሳምንት አስቀድሞ ከሊጉ መውረዱን ያረጋገጠው ወልድያ መልካ ቆሌ ላይ ሲዳማ ቡናን አስተናግዶ 3-2 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ በመልሶ ማጥቃት አጨዋወት ወደ ሜዳ የገቡት ወልድያዎች ግብ ለማግኘት የፈጀባቸው 1 ደቂቃ ብቻ ነበር፡፡ በውድድር ዘመኑ አጋማሽ ቡድኑን የተቀላቀለው ፍፁም ደስይበለው ወልድን ቀዳሚ ያደረገች ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡ የመጀመርያው አጋማሽዝርዝር

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ደደቢት አቻ ተለያይቶ የቻምፒዮንነት ተስፋውን ሲያጨልም ሙገር ሲሚንቶ ላለመውረድ በሚያደርገው ትግል ላይ ነፍስ ዘርቶበታል፡፡ አዲስ አበባ ላይ በ9 ሰአት ዳሽን ቢራን ያስተናገደው ደደቢት 2-2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል፡፡ ዳሽን ቢራ የተሸ ግዛው በ9ኛው እና14ኛው ደቂቃ ባስቆጠራቸው ግቦች 2-0 ቢመራም ሳሙኤል ሳኑሚ በ44ኛው ደቂ በፍፁም ቅጣት ምት እንዲሁምዝርዝር

በመውረድ ስጋት ውስጥ የሚገኘው ኤሌክትሪክ አሰልጣኙ አጥናፉ አለሙን ማሰናበቱን ተወዳጁ ጨዋታ ዘግቧል፡፡ የቡልጋሪያዊውን ዮርዳን ስቶይኮቭ ስንብት ተከትሎ ከዋና ከረዳት አሰልጣኝነት ወደ ዋና አሰልጣኝነት ያደጉት አሰልጣኝ አጥናፉ አለሙ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ያስመዘገቡት ደካማ ውጤት ለስንብታቸው መንስኤ ነው ተብሏል፡፡ የአሰልጣኙን ስንብት ተከትሎ የኤሌትሪክ ተስፋ ቡድን አሰልጣኝ የሆነው ኤርሚያስ በቀሪዎቹ 3 የሊግ ጨዋታዎችዝርዝር

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ወልድያ ከፕሪሚየር ሊጉ መውረዱን ሲያረጋግጥ ሙገር ሲሚንቶም የወልድያን እግር ሊከተል ተቃርቧል፡፡ መልካ ቆሌ ላይ አርባምንጭ ከነማን ያስተናገደው ወልድያ 1-0 ተሸንፏል፡፡ ሽንፈቱን ተከትሎም 3 ጨዋታ እየቀረው 12ኛ ደረጃ ላይ ካለው ኤሌክትሪክ ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት 12 በመድረሱ ባለፈው አመት ወደነበረበት ብሄራዊ ሊግ መውረዱን አረጋግጧል፡፡ አሰላ ላይ አዳማ ከነማንዝርዝር

  በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሳምንት ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ጎንደር ተጉዞ በድል ተመልሷል፡፡ ዳሽን ቢራዎች ቶጓዊው አጥቂ ኤዶም ሆሶሮቪ ባስቆጠረው ግብ የመጀመርያውን አጋማሽ በ1-0 መሪነት ቢጨርሱም በጥሩ አቋም ላይ የሚገኘው አዳነ ግርማ አከታትሎ ባስቆጠራቸው ግቦች 2-1 አሸንፎ ከደደቢት ጋር ያለውን የ8 ነጥብ ልዩነት ልዩነት ማስጠበቅ ችሏል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ48ዝርዝር

  የኢትዮጵያ ንግድ ባንኩ አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪ/ማርያም ባለፈው እሁድ በአዳማ ከነማ 4-2 በተሸነፉበት ጨዋታ ከፍተኛ የዳኝነት በደል እንደደረሰባቸውና ለፌዴሬሽኑ ክስ እንዳስገቡ ተናግረዋል፡፡ አሰልጣኝ ፀጋዬ በአዳማው ጨዋታ የዳኝነት ውሳኔዎች ለሽንፈታቸው ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል ‹‹ በጨዋታው የፍፁም ቅጣት ምት አላግባብ ተሰጥቶብናል፡፡ አዳማዎች ካስቆጠሯቸው ግቦች አንዷ የተቆጠረችው ከጨዋታ ውጪ በሆነ እንቅስቃሴ ነበር፡፡ የጨዋታውንዝርዝር

  ዛሬ በተካሄደ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ደደቢት ኤሌክትሪክን 4-0 በማሸነፍ 2ኛ ደረጃን ከሲዳማ ተረክቧል፡፡ ደደቢት 4-0 ባሸነፈበት የእለቱ ግጥሚያ ሳሙኤል ሳኑሚ በቀድሞ ክለቡ ላይ 3 ግቦች አስቆጥሮ ሐት-ትሪክ ሲሰራ ታደለ መንገሻ ቀሪዋን አንድ ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡ ሳኑሚ ዛሬ ያቆጠራቸውን 3 ግቦች ጨምሮ በሊጉ 18 ግቦች በማስቆጠር ከፊሊፕ ዳውዚ በ3 ግቦችዝርዝር