ዜና (Page 2)

በዝውውር ገበያው ላይ በንቃት እየተሳተፉ የሚገኙት ሰበታ ከተማዎች በዛሬው ዕለት የመስመር ተከላካይ ማስፈረማቸው ታውቋል። አሠልጣኝ ዘላለም ሽፈራውን ዋና አሠልጣኝ አድርገው የሾሙት ሰበታ ከተማዎች ከሰሞኑን በዝውውር ገበያው ላይ የነቃ ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ። አሁን በተገኘ መረጃ ደግሞ በአዳማ ከተማ የውድድር ዓመቱን ያሳለፈው ታፈሠ ሰርካ ስብስባቸውን መቀላቀሉ ታውቋል። የቀድሞ የመከላከያ እና መቐለ 70ዝርዝር

አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለን በቅርቡ የሾመው ጅማ አባ ጅፋር አሁን ደግሞ የምክትል አሰልጣኙን እና የግብጠባቂዎች አሰልጣኙን ውል አራዝመዋል። ጅማ አባ ጅፋር በ2014 የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ እራሱን በማጠናከር የተሻለ ቡድን ለመሆን ወደ እንቅስቃሴ የገባው አሠልጣኝ አሸናፊ በቀለን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ በመሾም ነበር። አሁን ደግሞ ያለፉትን አራት ዓመታት ከተለያዮዝርዝር

ወላይታ ድቻ አመሻሹን የክረምቱ አራተኛ ፈራሚ ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል። በአሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም መሪነት ሦስት አዳዲስ እና አምስት ነባር ተጫዋቾችን ያስፈረመው ወላይታ ድቻ በዛሬው ዕለት አማካዩ ሀብታሙ ንጉሤን አስፈርሟል፡፡ በጅማ አባጅፋር ጥሩ የውድድር ጊዜን በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ያሳለፈው ባለ ተሰጥኦው አማካይ በክለቡ ለሁለት የውድድር ዘመናት የቆየ ሲሆን አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያምን ተከትሎዝርዝር

ግብ ጠባቂው ሰለሞን ደምሴ በሰበታ ከተማ ውሉን አድሷል፡፡ በአሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው መሪነት አዳዲስ እና ነባር ተጫዋቾችን እያስፈረመ የሚገኘው ሰበታ ከተማ በዛሬው ዕለት የግብ ጠባቂው ሰለሞን ደምሴን ውል አራዝሟል፡፡ ከከፍተኛ ሊግ ጀምሮ ሰበታ ከተማን እያገለገለ የሚገኘው ሰለሞን አሁንም ለተጨማሪ ሦስት ዓመታት በሰበታ ለመቆየት ውሉን አድሷል፡፡ዝርዝር

በአሠልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ የሚመራው ድሬዳዋ ከተማ ግዙፉን የመስመር ተጫዋች ለማስፈረም ከስምምነት ላይ ደርሷል። በተጠናቀቀው የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር አስረኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ድሬዳዋ ከተማ የአሠልጣኙን ውል ካራዘመ በኋላ በዝውውር ገበያው ላይ በንቃት በመሳተፍ ተጫዋቾችን እያስፈረመ ይገኛል። ለከርሞው ተጠናክሮ ለመቅረብ እንቅስቃሴ ላይ የሚገኘው ክለቡም በዛሬው ዕለት ጋናዊውን የመስመር ተጫዋች አብዱለጢፍ መሐመድ የግሉዝርዝር

በሲዳማ ቡና የውድድር ዓመቱን ያሳለፈው አማካይ ወደ ሀገሩ የተመለሰበትን ዝውውር አጠናቋል። ዩጋንዳዊው አይደክሜ የአማካይ መስመር ተጫዋች ያስር ሙገርዋ 2009 ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ የመጣበትን ዝውውር በቅዱስ ጊዮርጊስ በኩል ማደረጉ አይዘነጋም። ተጫዋቹ አንድ ዓመት ለፈረሰኞቹ ግልጋሎግ ከሰጠ በኋላ ደግሞ ወደ ዐፄዎቹ ቤት አምርቶ ተጫውቷል። ከዛም ስሑል ሽረን ተቀላቅሎ ሲጫወት የነበረዝርዝር

የዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን የኤርትራ አቻውን ሁለት ለአንድ በመርታት አምስተኛ ደረጃን ይዞ ውድድሩን ጨርሷል። የወቅቱ የሴካፋ ውድድር አሸናፊ ዩጋንዳ ጨዋታውን በጥሩ አቀራረብ የቀረበ ይመስላል። ኤርትራዎች ደግሞ ከኳስ ጀርባ በመሆን ሲጫወቱ ታይቷል። ይህ ቢሆንም ግን የጨዋታውን የመጀመሪያ ሙከራ ያደረገችው ኤርትራ ነች። ቡድኑም በ9ኛው ደቂቃ በዓሊ ሱሌማን አማካኝነት ጥሩ ጥቃት ፈፅሟል። ከስምንት ደቂቃዎችዝርዝር

የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ታደለ መንገሻ የአዳማ ከተማ አምስተኛ ፈራሚ ተጫዋች ሆኗል። በዝውውር ገበያው የነቃ ተሳትፎ እያደረገ የሚገኘው አዳማ ከተማ ታደለ መንገሻን አምስተኛ ፈራሚው አድርጓል፡፡ በቴክኒክ ችሎታቸው ከሚጠቀሱት መሀል አንዱ የሆነው የቀድሞው የደደቢት፣ ኢትዮጵያ መድን፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና አርባምንጭ ከተማ አማካይ ታደለ ከሁለት ዓመት በፊት ዳግም ወደ ቀድሞ ክለቡ ቅዱስ ጊዮርጊስዝርዝር

በዝውውር ገበያው እየተሳተፈ የሚገኘው ሀዋሳ ከተማ ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ማስፈረም ችሏል፡፡ ሀዋሳ ከተማን በድምሩ ለአራት ዓመታት በግብ ጠባቂነት ያገለገለው ቶጓዊው ሶሆሆ ሜንሳ ከክለቡ ጋር በመለያየቱ ጋናዊው ግብ ጠባቂ መሐመድ ሙንታሪ በአንድ ዓመት ውል በቦታው ተተክቷል፡፡ ከዚህ ቀደም ለሀገሩ ክለቦች ሚዴአማ፣ አሻንቲ ኮቶኮ እንዲሁም ለዛምቢያው ሉሳካ ዳይናሞስ የተጫወተው እና ለጋና ከ23ዝርዝር

በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ መሪነት ወደ ዝውውሩ የገባው አዳማ ከተማ አዲሱ ተስፋዬ እና ዮናስ ገረመውን አስፈርሟል፡፡ ሦስተኛ አዲስ የክለቡ ፈራሚ በመሆን አዳማ የደረሰው ተከላካዩ አዲሱ ተስፋዬ ነው፡፡ የቀድሞው የስልጤ ወራቤ፣ ወላይታ ድቻ እና መከላከያ ተጫዋች ጦሩን ከለቀቀ በኃላ ያለፉትን ሁለት የውድድር ዓመታት በሰበታ ከተማ ቆይታን ያደረገ ሲሆን ውሉም በክለቡ መጠናቀቁን ተከትሎዝርዝር