Soccer Ethiopia

ዜና

​የቅዱስ ጊዮርጊስ ጊዜያዊ አሰልጣኝ…

የኤርነስት ሚድንዶርፕን ስንብት ተከትሎ የፈረሰኞቹ ጊዜያዊ አሰልጣኝ ሆኖ የተሾመው ማሂር ዴቪድስ ማነው? በቅርቡ ረጅም ልምድ ያካበቱትን ጀርመናዊውን የቀድሞው ካይዘር ቺፍስ አሰልጣኝ ኤርነስት ሚድንዶርፕን በሦስት ዓመት ውል ካስፈረመ በኃላ በይድነቃቸው ተሰማ የማሰልጠኛ ማዕከል ልምምዱን አጠናክሮ ሲሰራ ሰንብቶ አሰልጣኙ በሀገሪቱ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት የመልቀቅ ጥያቄ በማቅረባቸው ከክለቡ ጋር መለያየታቸው በዛሬው ዕለት ይፋ መደረጉ ይታወቃል።  ጀርመናዊው አሰልጣኝ […]

​ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ| ፋሲል ከነማዎች ቱኒዚያ ደርሰዋል 

በኮንፌደሬሽን ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ የቱኒዚያው ዩኤስ ሞናስቲርን ከሜዳ ውጭ የሚገጥመው ፋሲል ከነማ ቱኒዝያ ገብቷል ። ዐፄዎቹ ጨዋታቸውን የሚያደርጉት በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት ቢሆንም ከኢትዮጵያ ቀጥታ ወደ ቱኒዚያ የአየር በረራ ባለመኖሩ ቀደም ብለው በማመቻቸት ሊገሸዙ ችለዋል። ትናንት ምሽት ወደ ቱኒዚያ ጉዞ የጀመሩት የቡድኑ አባላትም ከምሽቱ 4 ሰዓት ከቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተነስተው ወደ ግብፅ ያመሩ ሲሆን […]

​መቐለ 70 እንደርታ ጉዳይ ወደ ካፍ አምርቷል

በካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ ተሳታፊ ለሆነው መቐለ 70 እንደርታ ጉዳይ መፍትሄ ያስገኛል የተባለ ደብዳቤ ወደ ካፍ ተልኳል። የ2011 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊው ክለብ መቐለ 70 እንደርታ በካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ ከሊቢያው አህሊ ቤንጋዚ ጋር የመጀመርያ ዙር ጨዋታውን መደልደሉ ይታወቃል። በዚህ ሳምንት መጨረሻ ላይ ከኅዳር 18 – 20 ባሉት ቀናት ከሜዳው ውጭ ግብፅ አልያም ቱኒዚያ ላይ የሚጫወት መሆኑ […]

የከፍተኛ ሊግ ውድድር የዕጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓት ዛሬ ተከናውኗል

በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ስር የሚተዳደረው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር የ2013 ዓመት የዕጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓት ዛሬ ሲያከናውን የደንብ ውይይትም ተደርጓል። ከረፋዱ አራት ሰዓት ጀምሮ በጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል በተካሄደው በዚህ መርሐ-ግብር ላይ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ ጂራ፣ የስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ዓሊሚራህ መሐመድ፣ የጽሕፈት ቤት ኃላፊው አቶ ባህሩ ጥላሁን እንዲሁም በውድድሩ የሚሳተፉ ክለቦች ተገኝተዋል። በቅድሚያም […]

​የቅዱስ ጊዮርጊሱ አሰልጣኝ ከክለቡ ተሰናበቱ

ቅዱስ ጊዮርጊስ የጀርመናዊውን አሰልጣኝ የልቀቁኝ ጥያቅ ተቀብሎ ማሰናበቱን አስታወቀ። ክለቡ በፌስቡክ ገፁ የሰፈረው መረጃ ይህን ይመስላል:- ” ቅዱስ ጊዮርጊስን ለሦስት ዓመታት ለማሰልጠን በቅርቡ ፊርማቸውን ያኖሩት ጀርመናዊው አሰልጣኝ ኧርነስት ሚድንድሮፕ በሀገሪቱ ውስጥ ያለው ሁኔታ ስላሳሰበኝና ቤተሰቦቼም በሁኔታው ግራ ስለተጋቡ በሚል ሰበብ ውሌን አፍርሼ እንድሄድ ይፈቀድልኝ ሲሉ ለቦርዱ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ የስራ አመራር ቦርድ ምንም እንኳን […]

ከፍተኛ ሊግ | ደቡብ ፖሊስ አዲስ አሰልጣኝ ሾሟል

ላለፉት ሁለት ዓመታት በረዳት አሰልጣኝነት ሲሰራ የነበረው አላዛር መለሰ ደቡብ ፖሊስን በዋና አሰልጣኝነት ተረክቧል፡፡ ከአሰልጣኝ ተመስገን ዳና ጋር የአንድ አመት ቀሪ ውል ቢኖረውም ለኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አሳልፎ የሰጠው ክለቡ አዲስ የሾመው አላዛር መለሰን ከዚህ ቀደም በተለያዩ ጊዜያት በረዳት አሰልጣኝነት የሰራ ሲሆን ከ2009 በፊት ባሉት ዓመታት ክለቡን ለቆ ታዳጊ ተጫዋቾች ላይ አሰልጣኙ ሲሰራ […]

​የከፍተኛ ሊግ ውድድሮች የሚደረጉባቸው ሜዳዎች ታውቀዋል

ከፍተኛ ጭቅጭቅ ያስነሳው የሜዳ መረጣ ጉዳይ በመጨረሻም በዕጣ ተለይቷል። የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የ2013 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድርን የዕጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓት እና የደንብ ውይይት ከደቂቃዎች በፊት አከናውኗል። የውድድሩ ደንብ ቀርቦ ውይይት እየተደረገ ባለበት ሰዓትም የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ውድድሮቹ የት እንደሚካሄዱ ተናግረዋል። በዚህ ሰዓት አንዳንድ ተሳታፊ ክለቦች የሜዳ መረጣው ላይ ከፍተኛ ቅሬታ በማስነሳታቸው ሜዳዎቹ በዕጣ እንዲለዩ ሆኗል። ነገርግን […]

​በከፍተኛ ሊጉ ሦስት ምድቦች የተደለደሉ ክለቦች ታውቀዋል

የከፍተኛ ሊግ ዓመታዊ ስብሰባ እና የዕጣ ማውጣት ሥነስርዓት እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን በሦስቱ ምድቦች የሚገኙ ክለቦችም ታውቀዋል። በተሰረዘው የውድድር ዓመት ከነበረው የምድብ ድልድል አንድ ለውጥ የተደረገ ሲሆን ምድብ ለ ላይ የነበረው መከላከያ ወደ ምድብ ሀ፣ በምድብ ሀ የነበረው አቃቂ ቃሊቲ ደግሞ በምድብ ለ ተደልድለዋል። ይህን ተከትሎ በአቃቂ ቃሊቲ በኩል ተቃውሞ የቀረበ ሲሆን ከፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት እና ከፍተማ […]

​ሎዛ አበራ የቢቢሲ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ዝርዝር ውስጥ ተካታለች

ኢትዮጵያዊቷ የፊት መስመር ተሰላፊ ሎዛ አበራ በተፅዕኖ ፈጣሪነቷ ዓለምአቀፍ ትኩረት አግኝታለች። የእንግሊዙ የሚዲያ ተቋም ቢቢሲ እንደአውሮፓዊያኑ የዘመን አቆጣጠር ከ 2013 ጀምሮ ዓለም ላይ ተፅዕኖ ፈጣሪ የሚላቸውን 100 እንስቶች በየዓመቱ ይፋ ያደርጋል። እንስቶቹ በተለያዩ የስራ መስኮች ላይ ተሰማርተው በማህበረሰባቸው ውስጥ ቢፈጥሩት ከፍ ያለ ተፅዕኖ መነሻነት ነው በተቋሙ ዝርዝር ውስጥ የሚካተቱት። በዚህ መሰረት ቢቢሲ የ2020 ተፅዕኖ ፈጣሪ […]

​ከፍተኛ ሊግ | አዲስ አበባ ከተማ አዲስ ዋና አሰልጣኝ ሾሟል

ከከፍተኛ ሊጉ ምድብ ለ ክለቦች አንዱ የሆነው አዲስ አበባ ከተማ ረዳት አሰልጣኝ በመሆን ከ2010 ጀምሮ ሲሰራ የነበረው እስማኤል አቡበከርን ቀጥሯል፡፡  በተጫዋችነት ዘመኑ ኢትዮጵያ ቡና፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሀዋሳ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ ክለቦች በአጥቂ እና አማካይ ስፍራ ላይ ድንቅ ጊዜያት ካሳለፈ በኋላ በሚሌንየሙ መግቢያ ከተጫዋችነት ተገልሎ የሀረር ሲቲን ክለብ በረዳት አሰልጣኝነት በመያዝ የአሰልጣኝኘት ጅማሮ ያደረገው እስማኤል […]

ሶከር ኢትዮጵያ

ሶከር ኢትዮጵያ በ ‘አብርሀም ገ/ማርያም የማስታወቂያ ድርጅት’ ስር የሚሰራ ድረገፅ ሲሆን በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በሚያተኩሩ ዜናዎች፣ ቁጥራዊ መረጃዎች፣ ታሪኮች፣ ጥልቅ ዘገባዎች፣ አስተያየቶች እና ትንታኔዎች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

ዘርፍ

ማኅደር

top