ዝውውር

የመስመር እና የፊት አጥቂው ሀብታሙ ታደሠ ወደ ሀድያ ሆሳዕና አምርቷል፡፡ በአሠልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት መሪነት እስከ አሁን አራት አዳዲስ ተጫዋቾችን ያስፈረመው ሀድያ ሆሳዕና ሀብታሙ ታደሠን አምስተኛ ፈራሚውን አድርጓል። በወልቂጤ ከተማ በከፍተኛ ሊጉ ሲጫወት ባሳየው መልካም እንቅስቃሴ መነሻነት በ2012 ወደ ኢትዮጵያ ቡና አምርቶ የተጫወተው ሀብታሙ ሁለት ጥሩ የውድድር ዘመናትን በቡና ካሳለፈ በኋላዝርዝር

በዛሬው ዕለት ወደ ዝውውር ከገባ በኃላ ሦስት አዳዲስ ፈራሚዎችን በእጁ ያስገባው ጅማ አባጅፋር የመስመር አጥቂ ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል፡፡ የመስመር ተጫዋቹ እዮብ ዓለማየሁ በሁለት ዓመት ውል ጅማን የተቀላቀለው ተጫዋች ሆኗል። በወላይታ ድቻ ከ17 እና ከ20 አመት በታች ቡድን ውስጥ አንፀባራቂ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴን በማድረጉ በ2008 ወደ ዋናው ካደገ በኋላ ጥሩ ጊዜያትንዝርዝር

በአሠልጣኝ ካሣዬ አራጌ የሚመራው ኢትዮጵያ ቡና ልምድ ያለውን የመስመር ተከላካይ ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል። በዘንድሮ የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በ13 ነጥቦች ተበልጦ ዋንጫውን በፋሲል ከነማ ያጣው ኢትዮጵያ ቡና ክፍተቶቼ ባላቸው ቦታዎች ላይ ዝውውሮችን ማድረግ ጀምሯል። ከሁለት ቀናት በፊት የግብ ዘቡ በረከት አማረን ዝውውር ያጠናቀቀው ክለቡ ከሌሎች ተጫዋቾች ጋርም ድርድር ላይ መሆኑዝርዝር

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን ተወዳዳሪው ሀዋሳ ከተማ ትናንት ወደ ዝውውሩ በመግባት አምስት ተጫዋቾችን ያስፈረመ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ ተጨማሪ አምስት ፈራሚዎችን ቀላቅሏል፡፡ ግብ ጠባቂዋ መስከረም መንግሥቱ የዓባይነሽ ኤርቄሎን ቦታ ለመተካት ወደ ክለቡ ተቀላቅላለች፡፡ የቀድሞዋ የአዳማ ከተማ ግብ ጠባቂ በጌዲኦ ዲላ ያለፉትን ሁለት የውድድር ዓመታት አሳልፋለች።  ቱሪስት ለማ የክለቡዝርዝር

ወደ ፋሲል ከነማ ለማምራት ተቃርቦ የነበረው አስቻለው ታመነ ከደቂቃዎች በፊት ፊርማውን አኑሯል።  የቀድሞው የዲላ ከተማ እና ደደቢት ተከላካይ ከ2007 ጀምሮ በቅዱስ ጊዮርጊስ በወጥነት ብቃቱን ሲያሳይ የቆየ ሲሆን በተከታታይ ሁለት ጊዜም የፕሪምየር ሊጉ ኮከብ ተጫዋችነት ክብርን ማግኘት ችሎ ነበር። አስቻለው ከሁለት ወራት በፊት በቅዱስ ጊዮርጊስ እገዳ ተላልፎበት የቆየ ሲሆን ለረጅም ጊዜዝርዝር

ኪሩቤል ኃይሉ በፋሲል ከነማ ቆይታውን አራዝሟል። እስካሁን ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ የተቀላቀሉት ፋሲሎች ረፋድ ላይ የተከላካዩ ዳንኤል ዘመዴን ውል ለተጨማሪ ኣመት እንዳራዘሙ ይታወቃል፡ አሁን ደግሞ የኪሩቤል ኃይሉን ውል አራዝመዋል፡፡ የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ፍሬ የሆነው የተከላካይ አማካይ ሥፍራ ተጫዋቹ ዘንድሮ በክለቡ ብዙም የመሰለፍ ዕድል እያገኘ ባይሆንም ክለቡ ለተጨማሪ ዓመትዝርዝር

በዝውውር ገበያው ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት ቡናማዎቹ የአንድ ዓመት ኮንትራት ካለው ተከላካያቸው ጋር በስምምነት ተለያይተዋል። በአሠልጣኝ ካሳዬ አራጌ የሚመራው ኢትዮጵያ ቡና በ2014 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እና በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎች ተጠናክሮ ለመቅረብ ከሰባት ቀናት በፊት በተከፈተው የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ላይ እየተሳተፈ ይገኛል። ቡድኑ አዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ ለመቀላቀል እንቅስቃሴዝርዝር

እስካሁን ስድስት ተጫዋቾችን ያስፈረመው ሲዳማ ቡና የሁለት ተከላካዮቹን ውል አድሷል፡፡ ጊት ጋትኮች ውሉን ያራዘመው ተጫዋች ነው፡፡ አዲስ አበባ ከተማን በመልቀቅ ሲዳማ ቡናን በ2012 በመቀላቀል ሁለት የውድድር ዓመታትን ያሳለፈው ቁመተ ረጅሙ ተከላካይ አሁንም ለተጨማሪ ዓመት በክለቡ መቆየቱ ተረጋግጧል፡፡ ሌላኛው ውሉን ያራዘመው የመስመር ተከላካዩ አማኑኤል እንዳለ ነው፡፡ የሲዳማ ቡና የታዳጊ ቡድን ፍሬዝርዝር

አዳዲስ ተጫዋቾች እያስፈረመ የሚገኘው ፋሲል ከነማ የተከላካዩ ዳንኤል ዘመዴን ውል አራዝሟል፡፡ ከፋሲል ከነማ የታችኛው ቡድን የተገኘው ይህ ተከላካይ ዘንድሮ በአብዛኛው ጨዋታዎች ላይ በተጠባባቂነት ያሳለፈ ሲሆን ፋሲል ከነማ የ2013 ቻምፒዮን መሆን ከቻለ በኃላ የመጨረሻ ሦስት ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ መጫወቱ ይታወሳል፡፡ ዳንኤል በዐፄዎቹ ቤት ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት ለመቆየት ነው ውሉን ያደሰው።ዝርዝር

በዝውውሩ ላይ በፍጥነት እየሠሩ የሚገኙት ሲዳማ ቡናዎች የአጥቂ አማካይ አስፈርመዋል፡፡ የአሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌን ውል ለማራዘም የተቃረበውና ወደ ተጫዋቾች ዝውውር ጎራ ያለው ሲዳማ ቡና ተክለማርያም ሻንቆ፣ ብሩክ ሙሉጌታ፣ አንዋር ዱላ፣ ተስፋዬ በቀለ እና ሙሉዓለም መስፍንን በያዝነው ሳምንት ወደ ቡድኑ የቀላቀለ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ ፍሬው ሰለሞንን በሁለት ዓመት ውል ወደ ቡድኑዝርዝር