ዝውውር (Page 129)

ኢትዮጵያ ቡና የአብዱልከሪም መሃመድን ዝውውር ዛሬ አጠናቋል፡፡ የመስመር ተከላካዩ ለቡና የ2 አመት ውልም ፈርሟል፡፡ ተጫዋቹ ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ ተገኝቶ ከክለቡ ኃላፊዎች ጋር በፊርማ ገንዘቡ ጉዳይ ላይ ድርድር ሲያደርግ የነበረ ሲሆን ከጠየቀው 1.5 ሚልዮን ብር በ100ሺህ ብር ቀንሶ በ1.4 ሚልዮን ብር ከስምምነት ላይ መድረሱ ታውቋል፡፡ ቡናም ለተጫዋቹ በ2 አመት ውስጥዝርዝር

ኤሌክትሪክ ዛሬ ውል ለማደስ የተስማማቸውን እና አዳዲስ ተጫዋቾቹን ፌዴሬሽን ወስዶ አስፈርሟቸዋል፡፡ ክለቡ ያስፈረማቸው ተጫዋቾች ከዚህ በፊት በክለቡ ለመቀጠል የተስማሙት እና አዲስ ለመቀላቀል ከስምምነት የደረሱትን ነው፡፡ አዲስ ነጋሽ ፣ አወት ገ/ሚካኤል ፣ አሳልፈው መኮንን እና በረከት ተሰማ ከክለቡ ጋር ያላቸውን ውል ማደሳቸውን ዛሬ በፊርማቸው ሲያረጋግጡ ብሩክ አየለ ፣ ሃብታሙ መንገሻ እናዝርዝር

በዝውውር መስኮቱ እስካሁን አዲስ ተጫዋች ያላስፈረመው ደደቢት ዛሬ የ5 ተጫዋቾቹን ኮንትራት አድሷል፡፡ ደደቢት ዛሬ ያስፈረማቸው ተጫዋቾች ሳምሶን ጥላሁን ፣ ሽመክት ጉግሳ ፣ ዳዊት ፍቃዱ ፣ አክሊሉ አየነው እና ብርሃኑ ቦጋለ ናቸው፡፡ ደደቢት ለተጫዋቾቹ ውል ማደሻ ምን ያህል ገንዘብ እንደከፈለ ማወቅ ባይቻልም ከክለቡ ባገኘነው መረጃ መሰረት ክለቡ ለተጫዋቾቹ ያወጣው ገንዘብ በወቅታዊውዝርዝር

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቡናው ቢንያም አሰፋ እና የኤሌክትሪኩ አማካይ ፍቅረየሱስ ተክለብርንን አስፈርሟል፡፡ ባንክ ለተጫዋቾቹ ፊርማ ምንያህል ወጪ እንዳወጣ ከክለቡ ማረጋገጫ አልተሰጠም፡፡ ቢንያም አሰፋ አምና ከኢትዮጵያውያን አጥቂዎች በሊጉ ከፍተኛ ግብ ያስቆጠረ አጥቂ ሲሆን ለቡና ውሉን ለማደስ የጠየቀው ገንዘብ በክለቡ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ቡናን ለቆ በሳምንቱ መጨረሻ ለሃምራዊዎቹ መፈረሙ ተነግሯል፡፡ ቢንያም ከዚህ ቀደምዝርዝር

የሲዳማ ቡናው የመስመር ተከላካይ አብዱልከሪም መሃመድ ሲዳማ ቡናን ለቆ ወደ ኢትዮጵያ ቡና ለመቀላቀል ከጫፍ መድረሱን ከምንጮቻችን የደረሱን መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ ወጣቱ የመስመር ተከላካይ ኢትዮጵያ ቡናን ለመቀላቀል ፍላጎቱን ያሳየ ሲሆን በሚከፈለው ዙርያ ለመስማማት እየተነጋገሩ መሆኑ ታውቋል፡፡ ተጫዋቹ እና ክለቡ ከስምምነት ላይ ከደረሱም በመጪዎቹ ቀናት ሊፈርም እንደሚችል ተነግሯል፡፡ ክለቡ ከተጫዋቹ የተጠየቀው ገንዘብ እስከዝርዝር

ኢትዮጵያ ቡና የተለያዩ ተጫዋቾችን ለማስፈረም ጥረቱን ቀጥሏል፡፡ ውል የጨረሱ እና የታገዱ ተጫዋቾችን እያሰናበተ የሚገኘው ክለቡ አዳዲስ ተጫዋቾችን ለማስፈረም እንዲሁም ውል የጨረሱ ተጫዋቾችን ውል የማደስ ስራን ዕየሰራ ነው፡፡ ክለቡ ከሃዋሳ ከነማው የመሃል ተከላካይ ግርማ በቀለ ጋር ስሙ ተያያዟል፡፡ ግርማ ከኢትዮጵያ ቡና የአሰልጣኞች ስታፍ ጋር የተገናኘ ሲሆን ቡናን ለመቀላቀል ድርድር ላይ መሆኑንዝርዝር

የወቅቱ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ውዱስ ጊዮርጊስ በዝውውር ላይ ዝምታን መርጦ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ወሳኝ ተጫዋቾችን ለማዘዋወር ከጫፍ መድረሱን ያገኘናቸው መረጃዎች ያሳያሉ፡፡   የደደቢቱ ተከላካይ አስቻለው ታመነ እና የኢትዮጵያ ቡናው የመስመር አጥቂ አስቻለው ግርማ ፈረሰኞቹን ይቀላቀላሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በቃል ደረጃም ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአስቻለው ታመነ ጋር መስማማቱ ተነግሯል፡፡ አስቻለው ታመነዝርዝር

  ሳላዲን ሰዒድ ለአልጄሪው ክለብ ኤምሲ አልጀር ለመጫወት የሁለት አመት ውል ፈርሟል፡፡ የዋሊያዎቹ አምበል ሳላዲን የምዕተ አመቱን የአፍሪካ ምርጥ ክለብ የግብፁን አል አሃሊን ለቆ ወደ ኤምሲ አልጀር ማምራቱ ተረጋግጧል፡፡ ከአል አሃሊ ጋር ያልተሳካ ግዜያትን ያሳለፈው ሳላዲን በካይሮው ክለብ ለአንድ ዓመት ብቻ ቆይታ አድርጓል፡፡ ሳላዲን በአል አሃሊ ቆይታው በ17 ጨዋታዎች 4ዝርዝር

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንደቀደመው የዝውውር መስኮት ሁሉ በዘንድሮውም ክረምት የዝውውር መስኮቱ ዋና ተዋናይ እየሆነ ነው፡፡ ቡድኑ በርካታ አዳዲስ ተጫዋቾችን ለማምጣት ከስምምነት ሲደርስ ኮንትራታቸው የተጠናቀቁ አብዛኛዎቹ ተጫዋቾቹን ኮንትራት ላለማደስ ወስኗል፡፡ ባንክ ለማስፈረም ከተስማማቸው ተጫዋቾች መካከል የቀድሞው የቡና ተከላካይ ቶክ ጄምስ በትልቅነቱ ቅድሚያውን ይይዛል፡፡ አምና 2ኛውን ግማሽ የውድድር ዘመን በወልድያ ያሳለፈው ቶክዝርዝር

ኤሌክትሪክ በተጫዋቾች ዝውውር ተጠምዷል፡፡ እስካሁን ከ5 ተጫዋቾች ጋር ሲስማማ የ7 ተጫዋቾችንም ውል አድሷል፡፡ ኤሌክትሪክ ለማስፈረም ከተስማማቸው ተጫዋቾች መካከል የንግድ ባንኩ የግራ መስመር ተከላካይ አለምነህ ግርማ የመጀመርያው ተጫዋች ሲሆን 1.1 ሚልዮን ብር ለ2 አመት ሊከፈለው መስማማመቱ ተነግሯል፡፡ የወላይታ ድቻዎቹ ተስፋዬ መላኩ እና አማካዩ አሸናፊ ሽብሩ ሌሎች ለኤሌክትሪክ ለመፈረም የተስማሙ ተጫዋቾች ሲሆኑዝርዝር