ዝውውር (Page 2)

ካሜሩናዊው የፊት መስመር ተጫዋች ወደ ሀዋሳ ከተማ አምርቷል። በአሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ እየተመሩ አዳዲስ ተጫዋቾች እያስፈረሙ እንዲሁም ደግሞ የነባሮችን ውል በማደስ ያለፉትን ጊዜያት የሰነበቱት ሀዋሳ ከተማዎች አሁን ደግሞ ካሜሩናዊው የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች ኤሚ ጄይካ ጋሲሶውን ማስፈረማቸውን ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡ 1 ሜትር ከ85 ሴንቲ ሜትር የሚረዝመው ኤሚ ሌስ አስተርስ ለተባለዝርዝር

የተጠናቀቀው የውድድር ዘመንን በድሬዳዋ ከተማ ያሳለፈው አጥቂ ወደ ሰበታ ከተማ እንደሚያመራ ተረጋግጧል። በአሠልጣኝ ዘላለም ሽፈራው እየተመሩ ስብስባቸውን እያጠናከሩ የሚገኙት ሰበታ ከተማዎች ከደቂቃዎች በፊት ጁኒያስ ናንጄቦን የግላቸው ማድረጋቸው ታውቋል። በኮቪድ-19 ምክንያት በተሰረዘው የ2012 የውድድር ዘመን ወልዋሎ ዓ/ዩን በመቀላቀል ወደ ኢትዮጵያ የመጣው ናንጄቦ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ደግሞ ወደ ድሬዳዋ ከተማ በማምራት ተጫውቶዝርዝር

አቡበከር ናስር ወደ ውጪ ሀገር ክለብ ሊያመራ ስለመሆኑ እየተነገረ ይገኛል። ዘንድሮ በኢትዮጵያ እግርኳስ ደምቆ የታየው አበቡበከር ናስርን የተለያዩ የውጭ ሀገር ክለቦች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ ለተጫዋቹ ባለቤት ኢትዮጵያ ቡና ጥያቄዎች እየቀረቡ መሆናቸውን ከዚህ ቀደም መዘገባችን ይታወቃል። ሀገራዊ ጥሪ ቀርቦለት በግል ጉዳይ ምክንያት ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር የማይገኘው አቡበከር ዛሬ ከቡድኑ ጋርዝርዝር

በአንደኛ ዲቪዝዮን የሚሳተፈው አርባምንጭ ከተማ የአራት አዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር ሲያጠናቅቅ የስድስት ነባር ተጫዋቾችን ውልም አራዝሟል፡፡ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን የ2013 የውድድር ዘመን ተወዳዳሪ የነበረውና በዓመቱ መጨረሻ ለመውረድ ተገዶ የነበረው አርባምንጭ ከተማ በቅርቡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የወረዱ ክለቦች በድጋሚ በአንደኛ ዲቪዚዮኑ ይቀጥሉ የሚል መመሪያን በማውጣቱ መነሻነት በፕሪምየር ሊጉዝርዝር

ወላይታ ድቻ ከአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ጋር በስምምነት መለያየቱ ታውቋል። ተመስገን ታምራት ከክለቡ ጋር የተለያየ ተጫዋች ነው። ከሀዋሳ ወጣት ቡድን የተገኘውና በተሰረዘው የውድድር ዓመት ወደ ወላይታ ድቻ አምርቶ የነበረው ተመስገን ቀሪ የአንድ ዓመት ውል እየቀረው በስምምነት ከክለቡ ጋር መለያየቱን ለማረጋገጥ ችለናል፡፡ ተጫዋቹ በቀጣይ ወደ አንድ የፕሪምየር ሊግ ክለብ ለማምራት ከጫፍ መድረሱንምዝርዝር

በድሬዳዋ ከተማ የሚያቆየው ቀሪ ኮንትራት አለው በማለት ወደ ወላይታ ድቻ የሚያደርገው ዝውውር ዕንከን ገጥሞት የቆየው ጉዳይ መፍትሔ አግኝቷል። በቅርቡ በአሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም ስብሰብ ለሁለት ዓመት ውል የተቀላቀለው ግብጠባቂው ወንደሰን አሸናፊ ወደ ቀድሞ ክለቡ ለመመለስ ያገኘው አጋጣሚ ላይ ጥያቄ ተነስቶ ነበር። ምክንያቱ ደግሞ ከዘንድሮ ከግማሽ ዓመት ጀምሮ የተጫወተበት ድሬዳዋ ከተማ ”ዝርዝር

የአማካይ እና የግራ መስመር ተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ ለሲዳማ ቡና ለመጫወት ተስማምቷል፡፡ የአሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌን ውል ካራዘመ በኃላ በርከት ያሉ አዳዲስ ተጫዋቾች ያስፈረመውና የነባሮችን ውልም ያደሰው ሲዳማ ቡና የግራ መስመር ተከላካዩ እና የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ሰለሞን ሀብቴን ለማስፈረም ተስማምተዋል፡፡ ከዚህ ቀደም በደደቢት፣ ወላይታ ድቻ እና ፋሲል ከነማ የተጫወተው ሰለሞን በተጠናቀቀው የውድድርዝርዝር

በኢትዮጵያ ቡና የውድድር ዓመቱን ያገባደደው የአማካይ መስመር ተጫዋች ቀጣይ ማረፊያው መከላከያ መሆኑ እርግጥ ሆኗል። በአሠልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ እየተመሩ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ማደጋቸውን ያረጋገጡት መከላከያዎች በቀጣይ ዓመት የሊጉ ውድድር ተጠናክረው ለመቅረብ በዝውውር ገበያው ላይ እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ። ከዚህ ቀደም የመሐል ተከላካዩ ልደቱ ጌታቸውን እና የግብ ዘቡ ሙሴዝርዝር

የነባር ተጫዋቾችን ውል እያደሰ አዳዲስ ተጫዋቾችንም ወደ ስብስቡ እየቀላቀለ የሚገኘው ሰበታ ከተማ ከደቂቃዎች በፊት የመስመር ተጫዋቹን ቆይታ ማራዘሙ ታውቋል። አሠልጣኝ ዘላለም ሽፈራውን ከቀጠሩ በኋላ በዝውውር ገበያው ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት ሰበታ ከተማዎች በርካታ ነባር ተጫዋቾቻቸውን ቢያጡም የጥቂቶቹን ውል በማደስ ላይ ይገኛሉ። ከዚህ ቀደም የፍፁም ገብረማርያም፣ ዱሬሳ ሹቢሳ እና ናትናኤል ጋንቹላን ውልዝርዝር

ወጣቱ አማካይ ከውሰት ቆይታ ተመልሶ በኢትዮጵያ ቡና አዲስ የሦስት ዓመት ውል ተፈራርሟል፡፡ በቢሾፍቱ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን ማድረግ የጀመረው ኢትዮጵያ ቡና አዳዲስ እና ነባር ተጫዋቾችን በመያዝ የቀጠለ ሲሆን ከቡድኑ ጋር የሚገኘው ተስፈኛው ወጣት በየነ ባንጃውም የሦስት ዓመት ውል መፈረሙ ታውቋል፡፡ ጎዶሎሊያስ ከተባለ የሰፈሩ ቡድን ባሳየው ተስፋ ሲጪ እንቅስቃሴ ወደ አፍሮ ፅዮንዝርዝር