ኢትዮጵያውያን በውጪ (Page 2)

በገጠመው ከበድ ያለ ጉዳት ለስምንት ወራት ያህል በጉዳት ከሜዳ ርቆ በቅርቡ የተመተለሰው የግብፁ አስዋን ክለብ አጥቂ ዑመድ ኡኩሪ ከጉዳት ስለመመለሱ እና ስለወቅታዊ አቋሙ ለሶከር ኢትዮጵያ ይናገራል፡፡ የ2006 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኮከብ ተጫዋች እና ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪው ዑመድ በመከላከያ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ዋልያዎቹ ጥሩ የውድድር ዘመናት ካሳለፈ በኃላ ነበር በ2007 ወደዝርዝር

ከኮሮና ቫይረስ መቋረጥ በኃላ በተጀመረው የግብፅ ፕሪምየር ሊግ ጥሩ ብቃቱን በማሳየት ለቡድኑ መሻሻል ጥሩ አስተዋፅኦ እያደርገ የሚገኘው ሽመልስ በቀለ ተቀይሮ በመግባት ግብ አስቆጥሯል። በግብፅ ፕሪምየር ሊግ 27ኛ ሳምንት ምስር ለል ማቃሳ ካይሮ ላይ ማስርን አስተናግዶ 3-0 ማሸነፍ ችሏል። ምስሮች በ16ኛው ደቂቃ በአሚር ማሬ አማካኝነት ግብ አስቆጥረው እስከ ዘጠናኛው ደቂቃ አንድዝርዝር

ወደ ጥሩ ወቅታዊ ብቃት የተመለሰው ሽመልስ በቀለ ከደቂቃዎች በፊት በተጠናቀቀው ጨዋታ ግብ አስቆጥሯል። በተከታታይ ጨዋታ በተጠባባቂ ወንበር ላይ ከቆየ በኃላ ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ወደ ቋሚነት የተመለሰው ኢትዮጵያዊው የምስር አልመቃሳ አማካይ ሽመልስ በቀለ ቡድኑ ከኢስማዒልያ ባደረገው ጨዋታ በሀምሳ አራተኛው ደቂቃ ግብ አስቆጥሯል። እንግዶቹ ኢስማዒልያዎች በመግዲ አማካኝነት ግብ አስቆጥረው መምራት በጀመሩበት ጨዋታዝርዝር

መልካሙ በመጀመርያው ጨዋታ ግብ ሲያስቆጥር ኢዮብ ዛምባታሮ እና ቢንያም በላይም በትናንትናው ዕለት ጨዋታ አድርገዋል። ከእረፍት መልስ የመሰለፍ ዕድሉን መልሶ ያገኘው ሽመልስ በቀለም ዛሬ ይጫወታል። 👉 ትውልደ ኢትዮጵያዊው በሊቨርፑል የመጀመርያ ጨዋታው ግብ አስቆጥሯል መልካሙ ፍራውንዶርፍ በቀዩ ማልያ የመጀመርያው ግብ አስቆጥሯል። ባለፈው ሳምንት ከሆፈንሄይም ወደ ሊቨርፑል የተዘዋወረው ትውልደ ኢትዮጵያዊው የቀጣይ ኮከብ መልካሙዝርዝር

አዲስ አበባ የተወለደው የመስመር ተከላካይ ኢዮብ ዛምባታሮ የሴሪ ሲ ክለብ የሆነው ሞንፓሊን ተቀላቅሏል፡፡ በሴሪ ሲ (ሦስተኛ የሊግ እርከን እየተወዳደረ የሚገኘው ሞኖፖሊ1966 ይፋ እንዳደረገው ከሆነ ተጫዋቹ ክለቡን የተቀላቀለው በውሰት ውል ሲሆን ከዛሬ ጅምሮ ከቡድኑ ጋር ልምምድ ጀምሯል። የ22 ዓመቱ ኢዮብ ለሁለት ዓመታት በአታላንታ ወጣት ቡድን (ፕሪማቬራ) ቆይቶ በ2018 ወደ ፓዶቫ በውሰትዝርዝር

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ታዳጊ መልካሙ ፍራውንዶርፍ ወደ ሊቨርፑል የሚያደርገው ዝውውር ስለ መጠናቀቁ ፍንጭ ሰጥቷል። በኢትዮጵያ ከምባታ ጠምባሮ ዞን ተወልዶ የእግርኳስ ሕይወቱን በጀርመኑ ክለብ በሆፈንሄም የጀመረው የ16 ዓመቱ ትውልደ ኢትዮጵያዊ የአጥቂ አማካይ በጀርመን ከፍተኛ ግምት ከተሰጣቸው ታዳጊዎች አንዱ ሲሆን ሊቨርፑልም የግሉ ለማድረግ ለወራት ሲከታተለው እንደቆየ ተገልጿል። ተጫዋቹ በኢንስታግራም ገፁ ፕሮፋይል ላይ የሊቨርፑልንዝርዝር

ባለክህሎቱ የመስመር ተጫዋች አንዋር ሜዴይሮ የባርሴሎና ወጣት ቡድንን ለቆ ወደ ጣልያኑ አታላንታ አምርቷል። ላለፉት ዓመታት በባርሰሎና ሁለተኛ ቡድን ቆይታ የነበረው የ18 ዓመቱ ትውልደ ኢትዮጵያዊ አንዋር መዴይሮ ወደ ጣልያኑ አታላንታ መፈረሙ ታማኙ ጣልያናዊ ጋዜጠኛ ፋብሪዝዮ ሮማኖ ገልጿል። በመስመር እና በአጥቂነት መጫወት የሚችለው አንዋር በአታላንታ በቅርቡ ከሁለተኛው ቡድን ያድጋል ተብሎ ከሚጠበቀው ሌላውዝርዝር

ሎዛ አበራ የምትገኝበት የማልታው ክለብ ቢርኪርካራ በሴቶች እግርኳስ ትልቁ መድረክ ላይ መሳተፉ ተረጋግጧል። የማልታ እግር ኳስ ፌደሬሽን በስሩ የሚያካሂዳቸው ውድድሮች መሰረዙን ተከትሎ የዓምናው የሊጉ አሸናፊ እና ውድድሩ እስከተቋረጠበት ድረስ ሊጉን ከተከታዩ ምጋር በ6 ነጥቦች በመራቅ ሲመራ የቆየው ቢርኪርካራ በቀጣይ ዓመት በቻምፒየንስ ሊግ እንዲሳተፍ የፌደሬሽኑ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ወስኗል። በመጀመርያ ዓመትዝርዝር

በስፖርቲንግ ካንሳስ ሲቲ አካዳሚ ውስጥ የሚገኘው ናቲ ክላርክ ወደ ትውልድ ሀገሩ ኢትዮጵያ ለጉብኝት የመጣበትን አጋጣሚ በመንተራስ ስለታዳጊው ጥቂት ልንላችሁ ወደናል።                                              ከአስር ዓመት በፊት የተከሰተውን የሀይቲ መሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ በማደጎ ልጅዝርዝር

ምንተስኖት አሎ በቀጣይ ቀናት በአንታልያ ስፖር ያለውን ቆይታ አጠናቆ ወደ ደሚርስፖር ያመራል። ከሳምንታት በፊት በቱርክ ክለቦች አንታልያ ስፖር እና ደሚር ስፖር የሙከራ አድል አግኝቶ ወደ ስፍራው ያቀናው የስሑል ሽረው ምንተስኖት አሎ ጥሩ የሙከራ ግዜ እያሳለፈ እንደሚገኝ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ባደረገው አጭር ቆይታ ገልጿል። ላለፉት ሳምንታት በቱርክ ዋናው ሊግ በሚሳተፈው አንታልያስፖርዝርዝር