Soccer Ethiopia

ቅድመ ውድድር

ድሬዳዋ ከተማ ተጫዋቾቹን ጠርቷል

ድሬዳዋ ከተማዎች የ2013 ቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን የሚጀምሩበት ጊዜ ታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተወዳዳሪው ድሬዳዋ ከተማ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ከከፍተኛ ሊጉ እስከ ፕሪምየር ሊግ ያሉ ተጫዋቾችን ተመልክቶ ያስፈረመ ሲሆን ረዳት አሰልጣኞችንም በመሾም ለአዲሱ ዓመት ራሳቸውን ሲያጠናክሩ ቆይተዋል። ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ደግሞ ቅድመ ውድድር ዝግጅትን ለማድረግ ለተጫዋቾቹ ጥሪ አስተላልፏል፡፡ ሁሉም ተጫዋቾች ነገ ወደ ድሬዳዋ አምርተው ክሊኦፓትራ በተባለ […]

ወልዋሎዎች ዝግጅት የሚጀምሩበት ቀን ታውቋል

ባለፉት ሁለት ሳምንታት በዝውውሩ ንቁ ተሳትፎ አድርገው ስድስት ተጫዋቾች ያስፈረሙት ወልዋሎዎች ለተጫዋቾቻቸው ጥሪ አድርገዋል። ክለቡ ተጫዋቾቹ እንዲሰበሰቡ ጥሪ ያደረገ ሲሆን የኮቪድ 19 ምርመራ ከተደረገላው በኋላ ጥቅምት 17 ዝግጅት እንደሚጀምሩ ታውቋል። ባለፉት ሁለት የውድድር ዓመታት በወልዋሎ ስታዲየም እድሳት ምክንያት በመቐለ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ያካሄዱት ቢጫዎቹ ዘንድሮ ግን በከተማቸው ዓዲግራት ዝግጅት የሚጀምሩ ይሆናል። እስካሁን ድረስ ዓወት ገብረሚካኤል፣ […]

ቅዱስ ጊዮርጊስ ለተጫዋቾቹ ጥሪ አቅርቧል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከዕለተ ዕሁድ ጀምሮ ተጫዋቾቹ ለዝግጅት እንዲሰበሰቡ ጥሪ አድርጓል፡፡ ባለፉት ሁለት ዓመታት ያጣውን ዋንጫ ዳግም በእጁ ለማስገባት በማለም ጀርመናዊው የቀድሞ ካይዘር ቺፍስ አሰልጣኝ ኤርነስት ሜደንዶርፕን ትናንት በጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ በይፋ ያስተዋወቀው ክለቡ አሰልጣኙ ወደ አዲስ አበባ ከመጡ ጀምሮ ስለ ክለቡ አጠቃላይ ገለፃ እና ማብራሪያ እንዲሁም አብረዋቸው የሚዘልቁትን ተጫዋቾች ሲያስተዋውቅ ሰንብቷል። ነገ ደግሞ የቡድኑ አባላት […]

የ14ኛው የአአ ከተማ ዋንጫ ኮከቦች ሽልማት ዛሬ ተከናውኗል

ዛሬ በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል በተዘጋጀው ፕሮግራም በውድድሩ በኮከብነት ለተመረጡ እና ለተሳታፊ ክለቦች የሽልማት ስነ-ሥርዓት ተከናውኗል። ይጀመራል ተብሎ ከተነገረው አንድ ሰዓት ከአስራ አምስት ደቂቃ አርፍዶ በተጀመረው ሥነ ስርዓት ሀብታሙ ሲሳይ (የኢፌዴሪ ባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ዴኤታ)፣ ኤሊያስ ሽኩር (የኢፌዴሪ ስፓርት ኮሚሽን ኮሚሽነር)፣ ዮናስ አረጋዊ (የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር)፣ ኢሳይያስ ጂራ (የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን […]

የ14ኛው የአአ ከተማ ዋንጫ የኮከቦች ምርጫ በቀጣይ ሳምንት ይካሄዳል

በደማቅ ሁኔታ ባሳለፍነው ወር የተጠናቀቀው የ14ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የመዝጊያ ሥነ ስርዓት በቀጣይ ሳምንት በኢንተርኮንትኔታል ሆቴል ይካሄዳል። ከጥቅምት 29 – ኅዳር 14 ቀን በአዲስ አበባ ስታዲየም ሲካሄድ የቆየው 14ኛው የአአ ከተማ ዋንጫ የማጠቃል ለያ መርሐግብር ማክሰኞ ታኀሳስ 14 ቀን ከቀኑ 08:00 በኢንተርኮንትኔታል ሆቴል በልዮ ሁኔታ ይካሄዳል። በዕለቱ የሚካሄዱ ዋና ዋና ኩነቶች፡- – የውድድሩ ኮከብ […]

የኦሮሚያ ዋንጫ በገላን ከተማ አሸናፊነት ተጠናቋል

ለቀናት በቢሾፍቱ ከተማ በአምስት ቡድኖች መካከል ሲካሄድ የቆየው የኦሮሚያ ዋንጫ ዛሬ ፍፃሜውን ሲያገኝ ገላን ከተማ የውድድሩ አሸናፊ ሆኗል። የኦሮሚያ ዳኞችና ኮሚሽነሮች ማኅበር ከኦሮሚያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር በተዘጋጀው በዚህ ውድድር አምስት ቡድኖች ተሳትፈዋል። ዛሬ ፍፃሜውን አግኝቶ የተሻለ ነጥብ በመሰብሰብ ገላን ከተማ የውድድሩ አጠቃላይ አሸናፊ ሆኖ አጠናቋል። ረቡዕ ኀዳር 24 ቀን 2012 ሞጆ ከተማ 0–2 ገላን […]

የኦሮሚያ ዋንጫ መካሄዱን ቀጥሏል

የከፍተኛ ሊግ እና የአንደኛ ሊግ አምስት ቡድኖችን አሳትፎ እየተካሄደ በሚገኘው የኦሮሚያ ዋንጫ ትናንት የተካሄዱ ሁለት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል። የፊታችን እሁድ ፍፃሜውን የሚያደገኘው ውድድሩ የትናንት ጨዋታዎች ውጤት ገላን ከተማ 1–1 ባቱ ከተማ ሞጆ ከተማ 0–0 ዱከም ከተማ ረቡዕ ኀዳር 24 ቀን 2012 08:00 | ሞጆ ከተማ ከ ገላን ከተማ 10:00 | ቢሾፍቱ ከተማ ከ ባቱ […]

የደቡብ ሠላም የከፍተኛ ሊግ ዋንጫ በሀምበሪቾ አሸናፊነት ተጠናቀቀ

ለአስር ቀናት ያህል ወደ ውድድሩ ዘግይቶ የገባው ዲላ ከተማን ጨምሮ በአምስት ክለቦች መካከል ሲደረግ የነበረው የደቡብ ሰላም የከፍተኛ ሊግ ክለቦች ዋንጫ ሀምበሪቾ ዱራሜን በነጥብ ብልጫ አሸናፊ በማድረግ ተፈፅሟል፡፡ ለሦስተኛ ጊዜ በደቡብ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን እየተመራ ሲደረግ የቆየው ይህ ውድድር ቡታጅራ ከተማ፣ ጌዴኦ ዲላ፣ ሀላባ ከተማ እና ሀምበሪቾ ዱራሜን ከከፍተኛ ሊጉ፤ ጂንካ ከተማን ከአንደኛ ሊግ […]

ኦሮሚያ ዋንጫ ዛሬ ተጀመረ

በአምስት ቡድኖች መካከል በቢሾፍቱ ከተማ የሚካሄደው የኦሮሚያ ከፍተኛ ሊግ እና አንደኛ ሊግ ቡድኖች የሚካፈሉበት ውድደር ዛሬ ተጀምሯል። የኦሮሚያ ዳኞችና ኮሚሽነሮች ማኀበር ከኦሮሚያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር በተዘጋጀው በዚህ ውድድር አምስት ቡድኖች የሚካፈሉ ይሆናል። ገላን ከተማ፣ ቢሾፍቱ ከተማ፣ ባቱ ከተማ፣ ዱከም ከተማ እና ሞጆ ከተማ ተሳታፊ ቡድኖች ናቸው። የዛሬ ጨዋታ ውጤት ቢሾፍቱ ከተማ 1–0 ሞጆ ከተማ […]

የአአ ከተማ ዋንጫ መጠናቀቅ ዙርያ መግለጫ ተሰጠ

የ14ኛውን የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ መጠናቀቅ አስመልክቶ የአአ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከአአ ስፖርት ኮሚሽን በጋራ በመሆን በጊዮን ሆቴል ዛሬ ቀትር ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። በመግለጫው ላይ የአአ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዮናስ አረጋይ፣ የአአ ግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት ኃይለየሱስ ፍስሐ እና የሥራ አስፈፃሚ አባል የኔነህ በቀለ የተገኙ ሲሆን የ14ኛው የአአ ከተማ ዋንጫ በስኬት መጠናቀቁን የፌዴሬሽኑ ፕሬዝደን ዝርዝር መግለጫ […]

ሶከር ኢትዮጵያ

ሶከር ኢትዮጵያ በ ‘አብርሀም ገ/ማርያም የማስታወቂያ ድርጅት’ ስር የሚሰራ ድረገፅ ሲሆን በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በሚያተኩሩ ዜናዎች፣ ቁጥራዊ መረጃዎች፣ ታሪኮች፣ ጥልቅ ዘገባዎች፣ አስተያየቶች እና ትንታኔዎች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

ዘርፍ

ማኅደር

top