ቅድመ ውድድር (Page 2)

የ2013 የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ቻምፒዮኑ ፋሲል ከነማ በጳጉሜ ወር ላለበት የካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ እና ለ2014 የሀገር ውስጥ ውድድር በቀጣዩ ሳምንት ወደ ዝግጅት ይገባል፡፡ በአሰልጣኝ ሥዩም ከበደ እየተመራ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የ2013 ቻምፒዮን መሆን የቻለው ፋሲል ከነማ ለሦስተኛ ጊዜ በአፍሪካ መድረክ ውድድር ያደርጋል፡፡ በተከታታይ ለሁለት ዓመታትዝርዝር

በተጠናቀቀው የ2013 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተካፋይ መሆኑን ያረጋገጠው ኢትዮጵያ ቡና ለውድድሩ ይረዳው ዘንድ ከመጪው ማክሰኞ አንስቶ በቢሾፍቱ ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን የሚያደርግ ይሆናል። በአሰልጣኝ ካሣዬ አራጌ የሚመሩት ኢትዮጵያ ቡናዎች በመጪው የውድድር ዘመን ላሉባቸው አህጉራዊ እና ሀገራዊ ውድድሮች ስብስባቸውን አጠናክሮ ለማቅረብ ከወዲሁ በዝውውርዝርዝር

ድሬዳዋ ከተማዎች የ2013 ቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን የሚጀምሩበት ጊዜ ታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተወዳዳሪው ድሬዳዋ ከተማ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ከከፍተኛ ሊጉ እስከ ፕሪምየር ሊግ ያሉ ተጫዋቾችን ተመልክቶ ያስፈረመ ሲሆን ረዳት አሰልጣኞችንም በመሾም ለአዲሱ ዓመት ራሳቸውን ሲያጠናክሩ ቆይተዋል። ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ደግሞ ቅድመ ውድድር ዝግጅትን ለማድረግ ለተጫዋቾቹ ጥሪ አስተላልፏል፡፡ ሁሉም ተጫዋቾች ነገዝርዝር

ባለፉት ሁለት ሳምንታት በዝውውሩ ንቁ ተሳትፎ አድርገው ስድስት ተጫዋቾች ያስፈረሙት ወልዋሎዎች ለተጫዋቾቻቸው ጥሪ አድርገዋል። ክለቡ ተጫዋቾቹ እንዲሰበሰቡ ጥሪ ያደረገ ሲሆን የኮቪድ 19 ምርመራ ከተደረገላው በኋላ ጥቅምት 17 ዝግጅት እንደሚጀምሩ ታውቋል። ባለፉት ሁለት የውድድር ዓመታት በወልዋሎ ስታዲየም እድሳት ምክንያት በመቐለ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ያካሄዱት ቢጫዎቹ ዘንድሮ ግን በከተማቸው ዓዲግራት ዝግጅት የሚጀምሩዝርዝር

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከዕለተ ዕሁድ ጀምሮ ተጫዋቾቹ ለዝግጅት እንዲሰበሰቡ ጥሪ አድርጓል፡፡ ባለፉት ሁለት ዓመታት ያጣውን ዋንጫ ዳግም በእጁ ለማስገባት በማለም ጀርመናዊው የቀድሞ ካይዘር ቺፍስ አሰልጣኝ ኤርነስት ሜደንዶርፕን ትናንት በጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ በይፋ ያስተዋወቀው ክለቡ አሰልጣኙ ወደ አዲስ አበባ ከመጡ ጀምሮ ስለ ክለቡ አጠቃላይ ገለፃ እና ማብራሪያ እንዲሁም አብረዋቸው የሚዘልቁትን ተጫዋቾች ሲያስተዋውቅዝርዝር

ዛሬ በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል በተዘጋጀው ፕሮግራም በውድድሩ በኮከብነት ለተመረጡ እና ለተሳታፊ ክለቦች የሽልማት ስነ-ሥርዓት ተከናውኗል። ይጀመራል ተብሎ ከተነገረው አንድ ሰዓት ከአስራ አምስት ደቂቃ አርፍዶ በተጀመረው ሥነ ስርዓት ሀብታሙ ሲሳይ (የኢፌዴሪ ባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ዴኤታ)፣ ኤሊያስ ሽኩር (የኢፌዴሪ ስፓርት ኮሚሽን ኮሚሽነር)፣ ዮናስ አረጋዊ (የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር)፣ዝርዝር

በደማቅ ሁኔታ ባሳለፍነው ወር የተጠናቀቀው የ14ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የመዝጊያ ሥነ ስርዓት በቀጣይ ሳምንት በኢንተርኮንትኔታል ሆቴል ይካሄዳል። ከጥቅምት 29 – ኅዳር 14 ቀን በአዲስ አበባ ስታዲየም ሲካሄድ የቆየው 14ኛው የአአ ከተማ ዋንጫ የማጠቃል ለያ መርሐግብር ማክሰኞ ታኀሳስ 14 ቀን ከቀኑ 08:00 በኢንተርኮንትኔታል ሆቴል በልዮ ሁኔታ ይካሄዳል። በዕለቱ የሚካሄዱ ዋናዝርዝር

ለቀናት በቢሾፍቱ ከተማ በአምስት ቡድኖች መካከል ሲካሄድ የቆየው የኦሮሚያ ዋንጫ ዛሬ ፍፃሜውን ሲያገኝ ገላን ከተማ የውድድሩ አሸናፊ ሆኗል። የኦሮሚያ ዳኞችና ኮሚሽነሮች ማኅበር ከኦሮሚያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር በተዘጋጀው በዚህ ውድድር አምስት ቡድኖች ተሳትፈዋል። ዛሬ ፍፃሜውን አግኝቶ የተሻለ ነጥብ በመሰብሰብ ገላን ከተማ የውድድሩ አጠቃላይ አሸናፊ ሆኖ አጠናቋል። ረቡዕ ኀዳር 24 ቀንዝርዝር

የከፍተኛ ሊግ እና የአንደኛ ሊግ አምስት ቡድኖችን አሳትፎ እየተካሄደ በሚገኘው የኦሮሚያ ዋንጫ ትናንት የተካሄዱ ሁለት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል። የፊታችን እሁድ ፍፃሜውን የሚያደገኘው ውድድሩ የትናንት ጨዋታዎች ውጤት ገላን ከተማ 1–1 ባቱ ከተማ ሞጆ ከተማ 0–0 ዱከም ከተማ ረቡዕ ኀዳር 24 ቀን 2012 08:00 | ሞጆ ከተማ ከ ገላን ከተማ 10:00ዝርዝር

ለአስር ቀናት ያህል ወደ ውድድሩ ዘግይቶ የገባው ዲላ ከተማን ጨምሮ በአምስት ክለቦች መካከል ሲደረግ የነበረው የደቡብ ሰላም የከፍተኛ ሊግ ክለቦች ዋንጫ ሀምበሪቾ ዱራሜን በነጥብ ብልጫ አሸናፊ በማድረግ ተፈፅሟል፡፡ ለሦስተኛ ጊዜ በደቡብ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን እየተመራ ሲደረግ የቆየው ይህ ውድድር ቡታጅራ ከተማ፣ ጌዴኦ ዲላ፣ ሀላባ ከተማ እና ሀምበሪቾ ዱራሜን ከከፍተኛዝርዝር