ሁለተኛ ዲቪዝዮን

የስታዲየሞች ግምገማ ዛሬ ተጠናቀቀ

በተዋቀረ ሦስት ኮሚቴዎች አማካኝነት በየሀገሪቱ በተመረጡ ስታዲየሞች እና መሠረተ ልማቶች ዙሪያ ሲደረግ የነበረው ግምገማ ዛሬ ተጠናቋል፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ሌሎች አካላትንም በአባልነት አካቶ በተዋቀሩ ሦስት ኮሚቴዎች አማካኝነት ውድድሮች በድጋሚ እንዲጀምሩ እና በተመረጡ ሜዳዎች ውድድሮች እንዲደረጉ ቅድመ ግምገማ ላለፉት ስምንት ቀናት ሲደረግ ቆይቶ ዛሬ ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡ ኮሚቴዎቹ ተዟዙረው አስራ ሰባት ሜዳዎች […]

የሴቶች ውድድሮች የሚጀመሩበትን መንገድ አስመልክቶ መነሻ ሰነድ ቀረበ

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ እና ሁለተኛ ዲቪዚዮን ውድድሮች የሚጀመሩበትን ሂደት አስመልክቶ በዛሬው ዕለት የመነሻ ሰነድ ቀርቧል። ሰነዱ ከቀረበ በኋላም ውይይት ተደርጓል። የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከጤና ሚኒስቴር ጋር በጋራ ያዘጋጀውን የውድድር ማስጀመሪያ የመነሻ ሰነድ ለክለቦች እያቀረበ ይገኛል። የዛሬ ሁለት ሳምንትም ፌደሬሽኑ የወንዶች ፕሪምየር ሊግ፣ ከፍተኛ እና አንደኛ ሊግ ክለቦችን በሁለቱ የሊግ እርከን ከሚገኙ የሴቶች ክለብ ተወካዮች […]

የሴቶች የሊግ ውድድሮች የሚጀመሩበትን መንገድ አስመልክቶ ውይይት ተጠርቷል

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ እና የ2 ዲቪዚዮን ውድድር የሚጀመርበትን መንገድ አስመልክቶ የመነሻ ሰነድ ለክለብ ተወካዮች ሊቀርብ ነው። የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን ከሳምንታት በፊት በስሩ የሚገኙ የሊግ እርከናት ላይ የሚሳተፉ የወንዶች እና የሴቶች ቡድን አመራሮችን በካፍ የልህቀት ማኅከል ሰብስቦ ውድድሮች ሊጀመሩ የሚችሉባቸውን መንገዶች አስመልክቶ መነሻ ሰነድ ካቀረበ በኋላ ውይይቶችን ሲያወያይ እንደነበር ይታወሳል። በወቅቱም በውይይቱ ላይ የሴት ቡድን […]

በዛሬው ውይይት ስለሴቶች ውድድር ምንም አለመባሉ አስገራሚ ሆኗል

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ውድድሮች የሚጀመሩበትን መነሻ ሰነድ ለክለብ ተወካዮች አቅርቦ ውይይት መደረጉ ይታወቃል። ነገር ግን በውይይቱ ላይ ስለሴቶች ውድድር ሃሳቦች አለመነሳታቸው አግራሞትን ፈጥሯል። በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን የወንዶች እንዲሁም የሴቶች 1ኛ እና 2ኛ የሊግ እርከን ላይ የሚወዳደሩ ክለቦችን በካፍ የልህቀት ማዕከል ሰብስቦ ውድድሮች የሚጀመሩበትን የመነሻ ሰነድ ማቅረቡ ይታወቃል። ሰነዱ ከቀረበ በኋላም በጉዳዩ ዙርያ ገንቢ […]

የሴት ተጫዋቾች የደሞዝ ክፍያ በወቅቱ አለመከፈል እየተቸገሩ ነው

ክለቦች ለሴት ተጫዋቾች መክፈል የነበረባቸውን የወር ደመወዝ በአግባቡ እየፈፀሙ ባለመሆኑ በተጫዋቾቹ ዘንድ ቅሬታን አስነስቷል፡፡ በ2012 በኢትዮጵያ በሁለቱም ፆታ ሲደረጉ የነበሩ የእግር ኳስ የሊግ ውድድሮች ከወራት በፊት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ ከቆሙ በኃላ በቅርቡ ደግሞ በይፋ ሙሉ ለሙሉ መሰረዛቸው ይታወሳል፡፡ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ውድድሮቹ ቢሰረዙም ክለቦች ከተጫዋቾች ጋር በገቡት ውል መሠረት ወርሀዊ ክፍያቸውን እንዲከፍሉ ማሰሰቡ የሚታወቅ […]

የ2011 ኮከቦች የገንዘብ ሽልማት በዚህ ሳምንት ተግባራዊ ይሆናል ተባለ

ተደጋጋሚ ቅሬታ በተሸላሚዎቹ ዘንድ ሲነሳበት የቆየው የ2011 የሊጎቹ ኮከቦች ሽልማት ከወራቶች መጓተት በኃላ ከዚህ ሳምንት ጀምሮ የገንዘብ ሽልማቱ መከፈል ይጀምራል፡፡ በ2011 በወንዶች ከአንደኛ ሊግ እስከ ፕሪምየር ሊግ በሴቶች ደግሞ የፕሪምየር ሊግ እና ሁለተኛ ዲቪዚዮን፣ በተጨማሪም ከ20 ዓመት በታች ወንዶች ፕሪምየር ሊግ ላይ በከፍተኛ ግብ አግቢነት፣ ኮከብ ተጫዋችነት፣ ኮከብ ግብ ጠባቂነት፣ ኮከብ አሰልጣኝነት፣ ምስጉን ዋና እና […]

የሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዙር ግምገማ በቀጣዩ ሳምንት ይደረጋል

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛው ዙር ግምገማ በቀጣዩ ሳምንት ቅዳሜ የሚደረግ ሲሆን መጋቢት 23 ደግሞ ሁለተኛው ዙር ይጀመራል፡፡ አስራ አንድ ክለቦችን ተካፋይ የሚያደርገው የ2012 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን ውድድር የፊታችን ዕሁድ በሚደረግ አንድ ቀሪ ጨዋታ የመጀመሪያውን ዙር ያጠናቀቃል፡፡ ይህንንም ተከትሎ በአንደኛው ዙር የነበሩት አጠቃላይ ደካማ እና ጠንካራ ጎን ጨምሮ የውድድሩ ሙሉ ሒደት የሚገመግም […]

ሴቶች 2ኛ ዲቪዚዮን | በዛሬ ጨዋታዎች ለገጣፎ፣ አካዳሚ እና ጥሩነሽ አሸንፈዋል

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ዲቪዝዮን ስምንተኛ ሳምንት ቀሪ ሦስት ጨዋታዎች ዛሬ ተከናውነው ለገጣፎ፣ አካዳሚ እና ጥሩነሽ አሸናፊ ሆነዋል። ለገጣፎ ከተማ ላይ ለገጣፎ ለገዳዲን ከልደታ ክ/ከተማ ያገናኘው ጨዋታ በባለሜዳዎቹ 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል። በመጀመርያው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ብዙም ያልተጠና፣ ሳቢ ያልሆነ የማጥቃት እንቅስቃሴ ብንመለከትበትም በተሻለ ሁኔታ ልደታ ክፍለ ከተማዎች ኳሱን መስርተው እስከ ለገጣፎ የሜዳ ክፍል […]

ሴቶች 2ኛ ዲቪዝዮን | ባህር ዳር ከተማ ሲያሸንፍ መሪው ሻሸመኔ ነጥብ ጥሏል

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር 2ኛ ዲቪዚዮን ስድስተኛ ሳምንት ዛሬ ሦስት ጨዋታዎች ሲደረጉ ባህር ዳር ፋሲልን አሸንፏፍ። ሁለቱ ጨዋታዎች ደግሞ በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል። ባህር ዳር ላይ ፋሲልን የገጠመው ባህር ዳር ከተማ 2-1 አሸንፏል። በርከት ያሉ ደጋፊዎች በታደመበት የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ባህር ዳሮች በመጀመሪያው አጋማሽ ፋሲሎች ደግሞ በሁለተኛው አጋማሽ ተሽለው ተንቀሳቅሰውበታል። ባለሜዳዎቹ ባህር ዳር ከተማዎች በመጀመሪያዎቹ ደቂቃዎች በተሻለ […]

ሴቶች 2ኛ ዲቪዝዮን | ሻሸመኔ ወደ መሪነቱ ሲመለስ ፋሲል ተከታታይ ድሉን አስመዝግቧል

የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ዲቪዚዮን አምስተኛ ሳምንት ዛሬ በተደረጉ ሦስት ጨዋታዎች ሲቀጥል ሻሸመኔ ከተማ፣ ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ እና ፋሲል ከነማ አሸንፈዋል። ጎንደር ፋሲለደስ ስታድየም ልደታ ክፍለ ከተማን ያስተናገዱት ፋሲል ከነማዎች 3 – 0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፈዋል። በመጀመሪያው አጋማሽ ጥሩ የተንቀሳቀሱት ምንትዋቦቹ ግብ ለማስቆጠርም ብዙ ደቂቃዎች አልጠበቁም። 10ኛው ደቂቃ ረደኤት ዳንኤል ሳጥን ውስጥ ያገኘችውን ኳስ […]

ሶከር ኢትዮጵያ

ሶከር ኢትዮጵያ በ ‘አብርሀም ገ/ማርያም የማስታወቂያ ድርጅት’ ስር የሚሰራ ድረገፅ ሲሆን በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በሚያተኩሩ ዜናዎች፣ ቁጥራዊ መረጃዎች፣ ታሪኮች፣ ጥልቅ ዘገባዎች፣ አስተያየቶች እና ትንታኔዎች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

ዘርፍ

ማኅደር

top