Soccer Ethiopia

ሁለተኛ ዲቪዝዮን

ሴቶች 2ኛ ዲቪዚዮን | ቦሌ መሪነቱን የያዘበትን ድል ሲያስመዘግብ ንፋስ ስልክ እና ቂርቆስ አቻ ተለያይተዋል

የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ዲቪዝዮን 5ኛ ሳምንት ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄዱ ሁለት ጨዋታዎች ሲጀምር ቦሌ ተከታታይ ድሉን በማሳካት በጊዜያዊነት የሰንጠረዡ አናት ላይ ተቀምጧል። የንፋስ ስልክ ላ/ክ/ከተማ እና ቂርቆስ ክ/ከተማ ጨዋታ ደግሞ ያለ ጎል በአቻ ውጤት ተጠናቋል። 09:00 በጀመረው የመጀመርያ ጨዋታ ቦሌዎች አካዳሚን 5-1 ማሸነፍ ችለዋል። ፍፁም በሚባል ደረጃ በኳስ ቁጥጥሩም ሆነ ለጎል የቀረበ ሙከራ […]

ሴቶች 2ኛ ዲቪዚዮን | ቦሌ እና ፋሲል ከሜዳቸው ውጪ፤ ባህር ዳር እና ልደታ በሜዳቸው አሸንፈዋል

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ዲቪዝዮን አራተኛ ሳምንት ዛሬ በአራት ጨዋታዎች ሲቀጥል መሪውን ሻሸመኔ በባህርዳር ሽንፈት ገጥሞታል። ቦሌ እና ፋሲል ከሜዳቸው ውጪ ሲያሸንፉ ልደታም ድል አስመዝግቧል። ለገጣፎ ለገዳዲ 0-4 ቦሌ ክ/ከተማ (ዳንኤል መስፍን) በእንቅስቃሴ ደረጃ ቀዝቀዝ ብሎ በጀመረው ጨዋታ እንግዶቹ ቦሌዎች በአንፃራዊነት በመጀመርያው አጋማሽ የተሻለ ሆነው ሲታዮ ገና በ8ኛው ደቂቃ ነበር ከመሐል ሜዳ አደራጅተው ወደ […]

የሴቶች ከፍተኛ ሊግ | ቦሌ ክ/ከተማ የመጀመርያ ድሉን አሳክቷል

የሴቶች ከፍተኛ ሊግ (ሁለተኛ ዲቪዚዮን) ሁለተኛ ሳምንት አንድ ቀሪ ጨዋታ በንግድ ባንክ ሜዳ የክፍለ ከተማ ደርቢ ልደታን ከቦሌ አገናኝቶ ቦሌዎች በህዳት ካሡ ሐት-ትሪክ 3–0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል። ኳሱን መስረተው እና ተቆጣጥረው በመጫወት ልደታዎች የተሻሉ በሆኑበት የመጀመርያው አጋማሽ በሁለት አጋጣሚ ግልፅ የማግባት አጋጣሚ አግኝተው ሳይጠቀሙ መቅረታቸው ዋጋ አስከፍሏቸዋል። 26ኛው ደቂቃ የቦሌዎች ተከላካይ ኳስ ከጨዋታ ውጪ ነው […]

የሴቶች ከፍተኛ ሊግ | ሻሸመኔ ከተማ ፋሲልን በመርታት ተከታታይ ድል አስመዝግቧል

በሁለተኛ ሳምንት በሴቶች ከፍተኛ ሊግ (ሁለተኛ ዲቪዚዮን) ቅዳሜ ፋሲል ከነማ ከ ሻሸመኔ ከተማ ጎንደር አፄ ፋሲደስ ስታድየም ባደረጉት ጨዋታ ሻሻመኔዎች 2-1 አሸንፈዋል ። ተመጣጣኝ በነበረው የሜዳላይ እንቅስቃሴ ግብ በማስቆጠር ረገድ ቀዳሚ የነበሩት ሻሸመኔ ከተማዎች ሲሆኑ 17ኛው ደቂቃ ላይ ትሁን ፌሎ ከሳጥን ውጭ ወደ ግብ አክርራ በመምታት ድንቅ ግብ አስቆጥራለች። በመጀመሪያው አጋማሽ ግቦች ቢቆጠሩም በሙከራ ረገድ […]

የ2012 ሴቶች ከፍተኛ ሊግ ዛሬ ተጀመረ

የ2012 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ ዛሬ ሲጀመር ሻሸመኔ ከተማ፣ ለገጣፎ ለገዳዲ፣ ልደታ ክ/ከተማ እና ፋሲል ከነማ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል። በአዲስ አበባ ስታዲየም 8 ሰዓት የተጀመረው የቦሌ ክ/ከተማ እና የፋሲል ከነማ ጨዋታ በተጋባዦቹ 3-2 አሸናፊነት ተጠናቋል። ገና በጅማሮ ግብ ማስተናገድ የጀመረው ጨዋታው በ13 ደቂቃዎች ውስጥ ሶስት ጎሎችን አስመልክቷል። በሶስተኛው ደቂቃ የቅጣት ምት ያገኙት ፋሲሎች አጋጣሚውን […]

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ኮከቦች ምርጫ ዛሬ ምሽት ተካሄደ

በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ስር በተካሄዱ ስድስት የውድድር ዓይነቶች የ2011 ኮከቦች የሽልማት መርሃግብር ዛሬ ምሽቱን በካፒታል ሆቴልና ስፓ ተካሂዷል። የ2011 ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተጫዋቾችና አሰልጣኞች እጩዎች ከነበረባቸው ጨዋታ መልስ በመርሃግብሩ እንዲታደሙ በማሰብ ከተያዘለት ሰዓት እጅጉን ዘግይቶ በጀመረው በዚሁ መርሃግብር በፌደሪሽኑ ስር በሚካሄዱ ውድድሮች በዓመቱ የተሻለ አፈፃፀም የነበራቸው ተጫዋቾች አሰልጣኞችና ዳኞች እውቅና የተሰጠ ሲሆን ዘንድሮ በተለየ መልኩ […]

ነገ የሚካሄደው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ኮከቦች ምርጫ እጩዎች ታውቀዋል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በ2011 ባካሄዳቸው 6 ሊጎች ላይ ጎልተው የወጡ ተጫዋቾች እና የተለያዩ የእግርኳስ ባለሙያዎችን ቅዳሜ ኅዳር 27 ቀን 2012 በካፒታል ሆቴል ከምሽቱ 12፡00 በሚደረግ ሥነ-ሥርዓት ለመሸለም ተዘጋጅቷል። የሽልማቶቹ ዘርፍ ኮከብ አሠልጣኝ፣ ኮከብ ተጫዋች፣ ኮከብ ግብ አስቆጣሪ፣ ኮከብ ግብ ጠባቂ እንዲሁም ምስጉን ዋና ዳኛ እና ምስጉን ረዳት ዳኛ ሲሆኑ በተጨማሪም የሕይወት ዘመን ተሸላሚ እና […]

አዲሱ የባህር ዳር ከተማ የሴቶች ቡድን በርከት ያሉ ተጨዋቾችን ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል

ባህር ዳር ከተማ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ዘንድሮ የእንስቶች ቡድን በማቋቋም ወደ ውድድር ለመግባት ዝግጅቱን እያደረገ ይገኛል። ከቀናት በፊት ሰርካዲስ እውነቱን አሰልጣኝ አድርገው የቀጠሩት ባህር ዳር ከተማዎች ለሚሳተፉበት የሴቶች ከፍተኛ ሊግ ውድድር ዝግጅታቸውን በባህር ዳር ዓለማቀፍ ስታዲየም እያደረጉ ይገኛሉ። አዲስ የተመሰረተው ቡድኑ በአሰልጣኝ ሰርካዲስ እየተመራ 25 ወጣት ተጨዋቾችን ከተለያዩ ክለቦች እና ፕሮጀክቶች በማምጣት የዓመታዊ ውድድሩን መጀመር […]

የ2012 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ እና ከፍተኛ ሊግ ዕጣ ወጥቷል

የ2011 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ክለቦች ዓመታዊ ስብሰባና የ2012 የውድድር ዘመን የእጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓት ዛሬ ረፋድ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ተካሂዷል። ዝግጅቱን በመክፈቻ ንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን የሥራ አስፈፃሚ አባል እና የእግርኳስ ልማትና የሴቶች እግርኳስ ዋና ሰብሳቢ የሆኑት ወ/ሮ ሶፊያ ኤልማሙን በንግግራቸው አንዳንድ የወንድ ፕሪምየር ሊግ ክለቦች ያላቸው ክለቦች የሴቶች ቡድን ለመያያዝ ሲያቅማሙ መስተዋሉ አግባብነት […]

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የዕጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓት የቀን ለውጥ ተደረገበት

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ እና ሁለተኛ ዲቪዚዮን የ2012 የውድድር ዘመን የዕጣ ማውጣት መርሀ ግብር የቀን ለውጥን ተደርጎበታል፡፡ የሁለቱ ውድድሮች የዕጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓት ቀድም ብሎ ቅዳሜ ህዳር 13 ይደረጋል ተብሎ የነበረ ቢሆንም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዛሬ ይፋ እንዳደረገው ከሆነ በአንድ ሳምንት ተገፍቶ ህዳር 20 እንዲከወን መደረጉ ታውቋል፡፡ ፌዴሬሽኑ የዕጣ ማውጣቱ ቀን ላይ ለውጥ ቢያደርግም […]

ሶከር ኢትዮጵያ

ሶከር ኢትዮጵያ በ ‘አብርሀም ገ/ማርያም የማስታወቂያ ድርጅት’ ስር የሚሰራ ድረገፅ ሲሆን በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በሚያተኩሩ ዜናዎች፣ ቁጥራዊ መረጃዎች፣ ታሪኮች፣ ጥልቅ ዘገባዎች፣ አስተያየቶች እና ትንታኔዎች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

ዘርፍ

ማኅደር

top