ራምኬል ሎክ ወደ ድሬዳዋ ከተማ አምርቷል

ድሬዳዋ ከተማ የመስመር አጥቂው ራምኬል ሎክን በአንድ ዓመት ውል በእጁ አስገብቷል።

ራምኬል ሎክ በ2010 የውድድር ዓመት ቅዱስ ጊዮርጊስን ለቆ ወደ ፋሲል ከነማ በሁለት ዓመት ውል አምርቶ የነበረ ቢሆንም ባለፈው ሳምንት አንድ ዓመት ቀሪ ውል እያለው ከክለቡ ጋር መለያየቱ የሚታወስ ነው። ይህን ተከትሎም በዮሀንስ ሳህሌ ወደሚሰለጥነው ድሬዳዋ ከተማ በአንድ ዓመት ውል አምርቷል። የቀድሞው የባንክ እና ኤሌክትሪክ አጥቂ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አብሯቸው ከሰራው አሰልጣኝ ዮሀንስ ጋርም በድጋሚ የሚገናኝ ይሆናል።

የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን በመቐለ እያከናወነ የሚገኘው ድሬዳዋ ከተማ እስካሁን አምስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል።