አምረላ ደልታታ ወደ ጅማ አባጅፋር አምርቷል

ከአዳማ ከተማ ጋር የውል ጊዜ የነበረው አምረላ ደልታታ በስምምነት ተለያይቶ ለጅማ አባጅፋር ፊርማውን አኑሯል፡፡

በስልጤ ወራቤ የክለብ እግር ኳስን ከጀመረ በኋላ በ2007 በሀድያ ሆሳዕና እስከ 2009 ድረስ ቆይታ ካደረገ በኋላ ወደ ወላይታ ድቻ አምርቶ የተጫወተ ሲሆን በድቻ በተለይ በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ጥሩ ጉዞ ሲያደርጉ ከነበሩ ተጫዋቾች መካከልም አንዱ ነበር፡፡ በ2011 የጦና ንቦቹን በመልቀቅ ለጥቂት ጊዜ ከሜዳ ከራቀ በኋላ አምና በውድድር ዘመኑ አጋማሽ አዳማ ከተማን መቀላቀል ችሏል፡፡ አሁን ደግሞ የውል ጊዜ እየቀረው ክለቡን በመልቀቅ ወደ ጅማ አባጅፋር ተጉዟል፡፡

በአዲሱ አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው እየተመሩ በርካታ ተጫዋቾች ያስፈረሙት ጅማዎች በአዳማ ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን እያደረጉ ይገኛሉ፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ