ጸጋዓብ ዮሴፍ ከቀድሞ አሰልጣኙ ጋር በድጋሚ ተገናኝቷል

ያለፉትን ሁለት ዓመታት በዋናው የሀዋሳ ከተማ ቡድን ሲጫወት የቆየው ፀጋአብ ዮሴፍ ወደ ፋሲል ከነማ አምርቷል፡፡

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ተስፋ ከሚጣልባቸው ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ጸጋዓብ ዮሴፍ በአሰልጣኝ ተመስገን ዳና ፕሮጀክት የእግርኳስ ህይወቱን ጀምሮ በሀዋሳ ከተማ የ17 እና 20 ዓመት በታች ቡድን ውስጥ በማሳለፍ በ2010 የውድድር ዓመት ወደ ዋናው ቡድን በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ አማካኝነት በማደግ በቡድኑ ውስጥ ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴን ሲያደርግ ታይቷል። የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ዘንድሮ ይበልጥ ጎልብቶ ይቀርባል ተብሎ ቢጠበቅም ብዘለም የመሰለፍ እድል ሳያገኝ ቀርቷል። ከክለቡ ጋር በፈጠረው አለመግባባትም የ18 ወራት ውል እየቀረው በስምምነት በመለያየት ወደ ፋሲል ማምራቱ ታውቋል።

ከሳምንት በፊት ከዐፄዎቹ ጋር የተለያየው ያስር ሙገርዋን ክፍተት እንደሚሸፍን የሚጠበቀው ጸጋዓብ የአንድ ዓመት ከስድስት ወራት ቆይታን በፋሲል ከነማ እንደሚያደርግ ሶከር ኢትዮጵያ ከክለቡ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *