ኢትዮጵያ ቡና ከ ደደቢት – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ኢትዮጵያ ቡና 3-0 ደደቢት
2′ 16′ 84′ ሳዲቅ ሴቾ


ተጠናቀቀ!!!!
ጨዋታው በኢትዮጵያ ቡና 3-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

90′ መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 3 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

ጎልልል!!! ቡና
84′
ሳዲቅ ሴቾ ከመስኡድ የተሻረለትን ኳስ በቀላሉ ወደ ግብነት ቀይሮ ሀት-ትሪክ ሰርቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ
78′
አማኑኤል ዮሃንስ ወጥቶ ጥላሁን ወልዴ ገብቷል፡፡ አማኑኤል ሜዳውን ለቆ ሲወጣ ከደጋፊዎች ሞቅ ያለ ጭብጨባ ተለግሶታል፡፡

ቢጫ ካርድ
73′
ሽመክት ጉግሳ በመስኡድ ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡ ሳምሶን ጥላሁንም የዳኛውን ውሳኔ በመቃወሙ ካርድ ተመዞበታል፡፡

ቢጫ ካርድ
69′
መስኡድ መሃመድ ኳስ አላግባብ በማባከኑ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

***ደደቢቶች በሙሉ ሃይል በማጥቃት እና የቡናን ፈጣን ደመልሶ ማጥቃት በመመከት መካከል ሆነው ግራ የተጋቡ ይመስላሉ፡፡ አማካዮቹ ከተከላካዮቹ ርቀው እየተጫወቱ በመሆኑም ቡናዎች በቀላሉ ወደ ደደቢት የግብ ክልል ለመግባት አስችሏቸዋል፡፡

65′ ጨዋታው ሃይል ያመዘነበት ሆኗል፡፡ ዳኛውም የሃይል አጨዋወቶችን በመፍቀድ ላይ ይገኛሉ፡፡

64′ አህመድ ረሺድ በአንድ ሁለት ቅብብል ከኤልያስ የተሻገረለትን ኳስ ሳይደርስበት ብርሃነ አድኖበታል፡፡

63′ ዳዊት ከፍፁሞ ቅጣት ምት ክልል ውጪ የሞከረውን ኳስ ሄሱ ይዞበታል፡፡

ቢጫ ካርድ
60′
ጋቶች ፓኖም የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

59′ ሳዲቅ የሞከረውን ኳስ ብርሃነ ሲመልሰው መስኡድ ወደ ጎል አሻምቶ የደደቢት ተከላካዮች አውጥተውታል፡፡

56′ ብርሃኑ ቦጋለ በቮሊ የመታው ኳስ በግቡ ቋሚ ለጥቂት ወጥቷል፡፡

50′ አብዱልከሪም ያሻማውን ኳስ ሳዲቅ ሳይደርስበት ብርሃነ እና ምኞት ተረባርበው አውጥተውታል፡፡

46′ ሳሚ ሳኑሚ በግማሽ ጨረቃው የተመቻቸ ኳስ ቢያገኝም የመታው ኳስ ኢላማውን ስቶ ወጥቷል፡፡ ሳኑሚ ከጉዳት መልስ የቀድሞ አቋሙን ማግኘት ተስኖታል፡፡

ተጀመረ
ሁለተኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡

የእረፍት ሰአት ለውጥ – ደደቢት
ያሬድ ዝናቡ ወጥቶ ኄኖክ ካሳሁን ገብቷል፡፡
ታሪክ ጌትነት ወጥቶ ብርሃነ ፍስሃዬ


እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በቡና 2-0 መሪነት ተጠናቋል፡፡

45′ መደበኛው 45 ደቂቃ ተጠናቆ 2 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

44′ ሳሚ ሳኑሚ ከርቀት የሞከረው ኳስ በግቡ አናት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

41′ አማኑኤል ከመስመር በግሩም ሁኔታ ተጣዋቾችን አልፎ የሞከረው ኳስ ለጥቂት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

40′ ቡናዎች በጭቃማው ሜዳ የተቸገሩ አይመስሉም፡፡ ማራኪ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይም ይገኛሉ፡፡

***የደደቢት ተጫዋቾች በርካታ ጥፋቶች በመፈፀም ላይ ይገኛሉ፡፡

33′ ጋቶች ፓኖም መሬት ለመሬት የመታውን ቅጣት ምት ታሪክ ይዞታል፡፡

ቢጫ ካርድ
32′
ብሩክ ተሾመ በመስኡድ ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

25′ ሳሚ ሳኑሚ ከግቡ በቅርብ ርቀት ያገኘውን ኳስ ሞክሮ ሄሱ በድንቅ ቅልጥፍና አድኖታል፡፡

20′ ዳዊት ፍቃዱ ከቀኝ መስመር የመታው ኳስ ኢላማውን ስቶ ወጥቷል፡፡

16′ አብዱልከሪም በአንድ ሁለት ቅብብል ወደ ግብ የሞከረውን ኳስ ታሪክ ሲተፋው በቅርብ ርቀት የነበረው ሳዲቅ ሴቾ ሁለተኛውን ግብ አስቆጥሯል፡፡

14′ ከበርካታ ቅብብሎች በኋላ የደረሰውን ኳስ ጋቶች ከርቀት ሞክሮ ኢላማውን ሳያገኝ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

10′ ብርሃኑ ቦጋለ የመታውን ቅጣት ምት ሄሱ ሀሪሰን በቀላሉ ይዞታል፡፡

* * * ሜዳው በተደጋጋሚ በጣለው ዝናብ ለመጫወት አስቸጋሪ ቢሆንም የጨዋታው አጀማመር መልካም የሚባል ነው፡፡ የደጋፊው ድባብም ግሩም ነው፡፡

ጎልልል!!!! ቡና
2′ ሳዲቅ ሴቾ ከማዕዘን ምት የተሻማውን ኳስ በግንባሩ በመግጨት ቡናን ቀዳሚ አድርጓል፡፡

ተጀመረ!!!!
ጨዋታው በደደቢት አማካኝነት ተጀምሯል፡፡


ኢትዮጵያ ቡና

1 ሀሪሰን ሄሱ
13 አህመድ ረሺድ – 5 ወንድይፍራው ጌታሁን- 16 ኤፍሬም ወንድወሰን – 15 አብዱልከሪም መሀመድ

3 መስኡድ መሃመድ (አምበል) – 25 ጋቶች ፓኖም – 9 ኤልያስ ማሞ

24 አማኑኤል ዮሃንስ – 7 ሳዲቅ ሴቾ – 14 እያሱ ታምሩ

ተጠባባቂዎች
99 ወንድወሰን ገረመው
11 ጥላሁን ወልዴ
12 አክሊሉ ዋለልኝ
4 ኢኮ ፊቨ
18 ሳላምላክ ተገኝ
26 ሲሪል ፋይስ
27 ዮሴፍ ዳሙዬ

 


ደደቢት

22 ታሪክ ጌትነት
29 ምኞት ደበበ – 14 አክሊሉ አየነው – 6 ብሩክ ተሾመ – 2 ተካልኝ ደጀኔ
19 ሽመክት ጉግሳ – 4 ያሬድ ዝናቡ – 8 ሳምሶን ጥላሁን – 10 ብርሃኑ ቦጋለ
17 ዳዊት ፍቃዱ – 11 ሳሙኤል ሳኑሚ

ተጠባባቂዎች
30 ብርሃነ ፍስሀዬ
15 ጆን ቱፎር
21 ኄኖክ ካሳሁን
90 ዮሃንስ ፀጋዬ
24 ተስሎች ሳይመን
28 ጆሴፍ አግዮኪ
32 ክዌሲ ኬሊ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *