ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ ዳሽን ቢራ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ኢትዮ ኤሌክትሪክ 3-1 ዳሽን ቢራ
39′ ፒተር ኑዋድኬ 72′ ፍፁም ገብረማርያም 90+3′ አዲስ ነጋሽ | 8′ አስራት መገርሳ


ተጠናቀቀ!!!
ጨዋታው በኤሌክትሪክ 3-1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

ጎልልል!!!!!
90+3′ አዲስ ነጋሽ ከዳሽን ተከላካዮች ቀምቶ በግብ ጠባቂው አናት ላይ የሰደደው ኳስ ግብ ሆኗል፡፡

90′ መደበኛው የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጠናቆ 4 ደቂቃ ተጨምሯል ፡፡

88′ እጅግ ለማመን የሚከብድ …. ተስፋዬ መላኩ ወደ ግብ ጠባቂው የመለሰው ኳስ ኢላማውን ስቶ የግቡን አግዳሚ ሲመልስ ተክሉ ተስፋዬ አግኝቶ ወደ ግብ ሲመታ የዳሽን ተጫዋች መልሶት ግብ ከመሆን አግዶታል፡፡ ለዳሽን የሚያስቆጭ አጋጣሚ ነበር፡፡

85′ ዳሽን ቢራዎች ጫና ለመፍጠር ጥረት ቢያደርጉም የኤሌክትሪክን የተከላካይ መስመር ጥሰው መግባት አልቻሉም፡፡

ጎልልል!!!! ኤሌክትሪክ
72′
ፍፁም ገብረማርያም ከተከላካዮች አምልጦ ኤሌክትሪክን መሪ አድርጓል፡፡

የተጫዋች ለውጥ
68′
ደረጄ መንግስቴ ወጥቶ ምንያህል ይመር ገብቷል፡፡

66′ ፒተር ኑዋዲኬ ከርቀት የመታው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

61′ ፒተር ኑዋዲኬ በመልሶ ማጥቃት ያገኘውን የግብ ማግባት አጋጣሚ አልተጠቀመበትም፡፡ ፒተር ለፍጹም የማቀበል አማራጭ ቢኖረውም የመታው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

51′ ደረጀ መንግስቱ ከቅጣት ምት የተሻገረውን ኳስ በጭንቅላቱ ገጭቶ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

ተጀመረ
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡

የእረፍት ሰአት ቅያሪ
ሸሪፍ ዲን ወጥቶ ሳሙኤል አለባቸው ገብቷል፡፡

**** ነጭ በቀይ ማልያ ለብሶ የገባው ኤሌከትሪክ በሁለተኛው አጋማሽ ሙሉ ቀይ ማልያ ለብሰው ገብተዋል፡፡


እረፍት !!!
የመጀመርያው አጋማሽ በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡

45′ የመጀመሪያው አጋማሽ መደበኛ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 2 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

ጎልልል!!!! ኤሌክትሪክ
39′
ፒተር ኑዋድኬ መሬት ለመሬት የመታው ቅጣት ምት ከመረብ አርፎል፡፡ 1-1

ቢጫ ካርድ
37′
ዮናስ ግርማይ በፍፁም ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡ አስራት መገርሳም የዳኛን ውሳኔን በመቃወሙ ቢጫ ካርድ አይቷል፡፡

34′ ፍፁም ከመስመር የተሻገረለትን ኳስ በአግባቡ ቢቆጣጠረውም ምቱ ጥንካሬ የሌለው በመሆኑ ደረጄ በቀላሉ ይዞታል፡፡

የተጫዋች ለውጥ
24′
አሳልፈው መኮንን (ጉዳት) ወጥቶ ማናዬ ፋንቱ ገብቷል፡፡

17′ ፒተር ኑዋዲኬ ጥሩ የግብ ማግባት አጋጣሚ ቢያገኝም የመታው ኳስ በተከላካዮች ተደርቦ ወጥቷል፡፡

14′ ማንኮ ክዌሳ የመታውን ቅጣት ምት ደረጄ አውጥቶታል፡፡

ጎልልል!!!! ዳሽን ቢራ
8′ አስራት መገርሳ ከማዕዘን ምት የተሻገረውን ኳስ ወደ ግብነት ቀይሮታል፡፡

ተጀመረ!!!
ጨዋታው በዳሽን ቢራ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡


የኢትዮ ኤሌክትሪክ አሰላለፍ

1 አሰግድ አክሊሉ

2 አወት ገ/ሚካኤል – 21 በረከት ተሰማ – 26 ሲሴይ ሀሰን – 15 ተስፋዬ መላኩ

20 አሳልፈው መኮንን – 4 ማንኮ ክዌሳ – 9 አዲስ ነጋሽ – 10 ብሩክ አየለ

16 ፍፁም ገብረማርያም – 28 ፒተር ኑዋድኬ

ተጠባባቂዎች
22 ገመቹ በቀለ
14 አማረ በቀለ
7 አለምነህ ግርማ
23 ማናዬ ፋንቱ
27 አሸናፊ ሽብሩ
8 በሃይሉ ተሻገር
17 አብዱልከሪም ሱልጣን


የዳሽን ቢራ አሰላለፍ
1 ደረጄ አለሙ

23 ዮናስ ግርማይ – 3 ሱሌይማን አህመድ – 26 ያሬድ ባየህ – 21 አምሳሉ ጥላሁን

11 ኤርሚያስ ሃይሉ – 4 አስራት መገርሳ – 6 ደረጄ መንግስቴ – 30 ተክሉ ተስፋዬ

25 መሃመድ ሸሪፍ ዲን – 9 ኤዶም ሆውሶሮቪ

ተጠባባቂዎች
31 ቴዎድሮስ ጌትነት
2 አሌክስ ተሰማ
18 ብርሃኑ በላይ
20 ኦስማን ካማራ
8 ምንያህል ይመር
12 አዲሱ አላሮ
5 ሳሙኤል አለባቸው
17 መስፍን ኪዳኔ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *