ገብረመድህን ኃይሌ የጅማ አባቡና አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ

አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ቀጣዩ የጅማ አባቡና አሰልጣኝ ሆነው መሾማቸውን ሶከር ኢትዮዽያ አረጋግጣለች፡፡

ጅማ አባቡና ትላንት ወደ አዲስ አበባ ተጉዞ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር አቻ ከተለያየበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ አሰልጣኝ ደረጄ በላይ በሰጡት ድህረ ጨዋታ አስተያየት  ከክለቡ ጋር መለያየታቸውን ይፋ ያደረጉ ሲሆን ክለቡም አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር ምልመላ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

በመስከረም ወር መጨረሻ ከኢትዮዽያ ብሄራዊ ቡድን ጋር የነበራቸው ኮንትራት መጠናቀቁን ተከትሎ ክለብ አልባ ሆነው የቆዩት አሰልጣኝ ገብረመድህን ዛሬ ከደቂቃዎች በፊት ከክለቡ ጋር ይፋዊ ኮንትራት የተፈራረሙ ሲሆን ነገ ከሰአት በክለቡ ልምድ ሜዳ ተገኝተው ስራቸውን ይጀምራሉ፡፡

በተያያዘ ዜና ክለቡን በፕሪምየር ሊጉ ለማቆየትና ጠንካራ ተፎካካሪ እንዲሆን ለማድረግ ባሉበት ክፍተቶች ላይ ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ተጨዋቾችን ለማስፈረም እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *