Soccer Ethiopia

ወልቂጤ ከተማ ለሊግ ኩባንያው ጥያቄ አቀረበ

Share

በኮሮና ወረርሺኝ ምክንያት የሊጉ ውድድር መሠረዙን ተከትሎ ክለቡ ለኮሚሽነር እና ዳኞች ተብሎ ያስገቡትን ክፍያ እንዲመለስለት ጥያቄ አቀረበ።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2012 የውድድር ዘመን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በቅርቡ በተደረገ ውይይት ሙሉ በሙሉ ሌሎች ውድድሮች ፕሪምየር ሊጉን ጨምሮ መሰረዙ ይታወሳል፡፡ውሳኔውን ተከትሎ ወልቂጤ ከተማ ለጨዋታ ታዛቢዋች እና የዳኛ ውሎ አበል 870,000 መክፈሉ አስተውሶ ይህ ክፍያ የሰላሳ ሳምንት ያካተተ ቢሆንም ቀሪ ጨዋታ ባለመከናቸው የ13 ጨዋታ ታሳቢ ተደርጎ ብሩ ተመላሽ ይሁንልን ሲሉ ጠይቀዋል።

በተያያዘ ዜና ወልቂጤ ከተማ የስራ አስፈፃሚ ባደረጉት ስብስባ የፌዴሬሽኑን ውሳኔ አክብሮ ለተጫዋቾች እና ለሠራተኞቹ የደሞዝ ክፍያ እንደሚፈፅም ማረጋገጫ ሰጥቷል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ

ሶከር ኢትዮጵያ

ሶከር ኢትዮጵያ በ ‘አብርሀም ገ/ማርያም የማስታወቂያ ድርጅት’ ስር የሚሰራ ድረገፅ ሲሆን በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በሚያተኩሩ ዜናዎች፣ ቁጥራዊ መረጃዎች፣ ታሪኮች፣ ጥልቅ ዘገባዎች፣ አስተያየቶች እና ትንታኔዎች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

ዘርፍ

ማኅደር

top