Soccer Ethiopia

ኢእፌ

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባዔ የሚደረግበት ቀን ታውቋል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዓመታዊው ጠቅላላ ጉባዔ ቀን እና ቦታ ታውቋል። በመስከረም 2013 ይደረጋል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ጉባዔው መንግስት ባወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት ቀኑ ላልታወቀ ጊዜ መራዘሙን ከዚህ ቀደም መዘገባችን ይታወሳል፡። ሆኖም ስፖርቶች ወደ ውድድር በመመለሳቸው እና ተጥሎ የነበሩ ገደቦች በመነሳታቸው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቀደም ብሎ አራዝሞት የነበረውን ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔን ኅዳር 26 […]

የፌዴሬሽኑ ቴክኒክ ኮሚቴ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ጥያቄ አቀረበ

የፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ በአሰልጣኝ ቅጥር ዙርያ የተጠየቀውን ምክረ ሀሳብ አቅርቦ ውድቅ የተደረገበት ቴክኒክ ኮሚቴ ጋዜጣዊ መግለጫ ሊሰጥ ነው። አወዛጋቢው የሰሞኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአሰልጣኝ ሹም ሽርን አስመልክቶ የተለያዩ ጉዳዮች እየተነሱ መሆናቸው ይታወቃል። የዚህ ጉዳይ መሪ ተዋንያን በመሆን የፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ምክረ ሀሳብ እንዲያቀርብ ተጠይቆ ባለ ዘጠኝ ነጥብ ሰነድ በሙሉ ድምፅ ተፈራርሞ በቃለ ጉባዔ አፅድቀው […]

የስታዲየሞች ግምገማ ዛሬ ተጠናቀቀ

በተዋቀረ ሦስት ኮሚቴዎች አማካኝነት በየሀገሪቱ በተመረጡ ስታዲየሞች እና መሠረተ ልማቶች ዙሪያ ሲደረግ የነበረው ግምገማ ዛሬ ተጠናቋል፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ሌሎች አካላትንም በአባልነት አካቶ በተዋቀሩ ሦስት ኮሚቴዎች አማካኝነት ውድድሮች በድጋሚ እንዲጀምሩ እና በተመረጡ ሜዳዎች ውድድሮች እንዲደረጉ ቅድመ ግምገማ ላለፉት ስምንት ቀናት ሲደረግ ቆይቶ ዛሬ ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡ ኮሚቴዎቹ ተዟዙረው አስራ ሰባት ሜዳዎች […]

ሲዳማ ቡና የእግድ ውሳኔ ተላለፈበት

በተጫዋቹ ሙጃሂድ መሐመድ ክስ ቀርቦበት የተወሰነበትን ውሳኔ ተግባራዊ አላደረገም በሚል ሲዳማ ቡና ከፌዴሬሽኑ ማንኛውም አገልግሎት እንዳያገኝ ታግዷል። በ2011 አጋማሽ ላይ ሙጃሂድ መሐመድ በሲዳማ ቡና ማልያ እየታጫወተ ሳለ ጉዳት ያጋጥመዋል። ለስድስት ወር ከሜዳ እርቆ ከጉዳቱ አገግሞ ሲመለስ ቀሪ የአንድ ዓመት ኮንትራት ቢኖረውም ክለቡ በ2012 የውድድር ዘመን ከቡድኑ ይቀንሰዋል። ተጫዋቹም ይህ የተቀነስኩበት መንገድ ተገቢ አይደለም የአንድ ዓመት […]

የኢትዮጵያ ክለቦች በአህጉራዊ ውድድር ላይ አይሳተፉም?

በዚህ የውድድር ዓመት በካፍ ውድድሮች ላይ የሚሳተፉ ክለቦች እንደሌሉ ቢወሰንም በቀጣይ የኢትዮጵያ ክለቦች በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ እና ኮንፌዴሬሽን ውድድሮች ላይ የመሳተፋቸው ነገር አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል። የአፍሪካ እግርኳስ የበላይ አካል የሆነው ካፍ በትላንትናው እለት የ2020/21 የቻምፒየንስ ሊግ እና የኮንፌዴሬሽን ውድድሮች የሚደረጉበትን የጊዜ ሰሌዳ አስታውቋል። ካፍ መርሐ-ግብሩን ሲያወጣ ጎን ለጎን በተሳታፊ ክለቦች አግባብነት ጋር በተያያዘ ያስተላለፈው ኮስታራ […]

ሀዋሳ ከተማ የእገዳ ውሳኔ ተላለፈበት

በቀድሞ ተጫዋቹ ገብረመስቀል ዱባለ በቀረበበት ክስ የተወሰነበትን ውሳኔ ተግባራዊ አላደረገም በሚል ሀዋሳ ከተማ በዛሬው ዕለት ማንኛውም አገልግሎት ከፈፀዴሬሽኑ እንዳያገኝ ታግዷል። በ2010 በጨዋታ ላይ እያለ የጉልበት ጉዳት ያጋጠመው ገብረመስቀል ዱባለ አንድ ዓመት ቀሪ የኮንትራት ዘመን እያለው በ2011 ክለቡ መቀነሱን ተከትሎ ቅሬታውን ወደ ፌዴሬሽኑ በመውሰድ መክሰሱ ይታወቃል። ጉዳዩን የተመለከተው የፌዴሬሽኑ ዲሲፕሊን ኮሚቴም ክለቡ ተጫዋቹን መቀነስ እንደማይችል እና […]

“መንግሥት የሚሰጠውን ውሳኔ እየጠበቅን ነው” አቶ ባህሩ ጥላሁን

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ቅጥር ዙርያ ቅድሚያ ሰጥቶ ይወያያል የተባለው የፌዴሬሽኑ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የዛሬው ስብሰባ ውሎ። የሥራ አስፈፃሚ አባላት የሆኑት ኮሎኔል ዐወል አብዱራሂም፣ አሊሚራህ መሐመድ፣ ሶፊያ አልማሙን እና አብዱረዛቅ መሐመድ ባልተገኙበት ዛሬ ረፋድ 4:00 በፌዴሬሽኑ ፅህፈት ቤት በተካሄደው መደበኛ ስብሰባ በዋናነት ይነሳል የተባለው የዋልያዎቹን የአሰልጣኝ ቅጥር ሳይመለከቱት እንዳለፉ እና ይልቁንም ከተጨዋቾች ዝውውር ጋር በተያያዘ […]

‘አወዛጋቢው ሕግ’ ገለፃ ተደረገበት

“የባላጋራ ቡድን ተጫዋችን ለረጅም ጊዜ መከታተል፣ አብሮ መሮጥ እና አጠገቡ መቆም ክልክል ነው” የሚለው ሕግ ማብራሪያ ተሰጥቶበታል። የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ውድድሮች በቀጣይ ዓመት የሚጀመሩበትን መንገድ አስመልክቶ የመነሻ ሰነድ አዘጋጅቶ ለክለቦች እያቀረበ ይገኛል። ከዚህ ቀደም ፌዴሬሽኑ የተዘጋጀውን መነሻ ሰነድ ለወንዶች ፕሪምየር፣ ከፍተኛ እና አንደኛ ሊግ ክለቦች ማቅረቡ ይታወሳል። በዛሬው ዕለትም የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ እና ሁለተኛ […]

የሴቶች ውድድሮች የሚጀመሩበትን መንገድ አስመልክቶ መነሻ ሰነድ ቀረበ

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ እና ሁለተኛ ዲቪዚዮን ውድድሮች የሚጀመሩበትን ሂደት አስመልክቶ በዛሬው ዕለት የመነሻ ሰነድ ቀርቧል። ሰነዱ ከቀረበ በኋላም ውይይት ተደርጓል። የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከጤና ሚኒስቴር ጋር በጋራ ያዘጋጀውን የውድድር ማስጀመሪያ የመነሻ ሰነድ ለክለቦች እያቀረበ ይገኛል። የዛሬ ሁለት ሳምንትም ፌደሬሽኑ የወንዶች ፕሪምየር ሊግ፣ ከፍተኛ እና አንደኛ ሊግ ክለቦችን በሁለቱ የሊግ እርከን ከሚገኙ የሴቶች ክለብ ተወካዮች […]

“ለእግርኳሱ ተገቢውን ክብር ስጡ” አቶ ኢሳይያስ ጂራ

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ ጂራ የተጫዋቾችን ዝውውርን በተመለከተ ሃሳብ ሰጥተዋል። የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከጤና ሚኒስቴር እና ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር በመተባበር ውድድሮች የሚጀመሩበትን መንገድ በተመለከተ የመነሻ ሰነድ አዘጋጅቶ ለክለቦች እያቀረበ ይገኛል። በዛሬው ዕለትም ፌዴሬሽኑ በሁለቱ የሊግ እርከኖች ላይ የሚሳተፉ የሴቶች ክለብ ተወካዮችን በካፍ የልህቀት ማኅከል ሰብስቦ መነሻ ሰነዱን አቅርቧል። ሰነዱ ከቀረበ በኋላም የፌዴሬሽኑ […]

ሶከር ኢትዮጵያ

ሶከር ኢትዮጵያ በ ‘አብርሀም ገ/ማርያም የማስታወቂያ ድርጅት’ ስር የሚሰራ ድረገፅ ሲሆን በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በሚያተኩሩ ዜናዎች፣ ቁጥራዊ መረጃዎች፣ ታሪኮች፣ ጥልቅ ዘገባዎች፣ አስተያየቶች እና ትንታኔዎች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

ዘርፍ

ማኅደር

top