አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ለ24 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል

አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ለ24 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከግብፅ እና ጂቡቲ ጋር ለሚያደርጋቸው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ለ24 ተጫዋቾች ጥሪ ተደርጓል።

መጋቢት 12 በላርቢ ዛውሊ ስታዲየም (ሞሮኮ) ከግብጽ ጋር እንዲሁም መጋቢት 15 ኤል ጀዲዳ (ሞሮኮ) በሚገኘው ኤል አብዲ ስታዲየም ደግሞ ከጂቡቲ ጋር የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ አምስተኛ እና ስድስተኛ ጨዋታቸውን የሚያደርጉት ዋልያዎቹ አሰልጣኝ የሆኑት መሳይ ተፈሪ ከዚህ በታች ለተዘረዘሩ 24 ተጫዋቾች ጥሪ አቅርበዋል።

ግብ ጠባቂዎች

ሰዒድ ሀብታሙ – ሀዋሳ ከተማ
አቡበከር ኑራ – ኢትዮጵያ መድን
ቢኒያም ገነቱ – ወላይታ ድቻ

ተከላካዮች

ብርሃኑ በቀለ – ሲዳማ ቡና
ራምኬል ጀምስ – ኢትዮጵያ ቡና
አሥራት ቱንጆ – ድሬዳዋ ከተማ
አማኑኤል ተርፋ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
አሕመድ ረሺድ – ድሬዳዋ ከተማ
ፍሬዘር ካሳ – ባህር ዳር ከተማ
ያሬድ ካሳዬ – ኢትዮጵያ መድን
ወልደአማኑኤል ጌቱ – ኢትዮጵያ ቡና
አብዱልሰላም የሱፍ – ድሬዳዋ ከተማ
አስቻለው ታመነ – መቻል

አማካዮች

አማኑኤል ዮሐንስ – መቻል
ወገኔ ገዛኸኝ – ኢትዮጵያ መድን
በረከት ወልዴ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ብሩክ ማርቆስ – ሀዲያ ሆሳዕና
አብዱልከሪም ወርቁ – መቻል
ሀብታሙ ተከስተ – ፋሲል ከነማ

አጥቂዎች

አቡበከር ናስር – ሱፐር ስፖርት ዩናይትድ
አሕመድ ሁሴን – አርባምንጭ ከተማ
ቸርነት ጉግሳ – ባህር ዳር ከተማ
መሐመድ አበራ – ኢትዮጵያ መድን
በረከት ደስታ – መቻል

ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ከመጋቢት 4 ጀምሮ በቀጣይ በሚገለፅ ሆቴል በመሰባሰብ ዝግጅታቸውን እንደሚጀምሩም ፌዴሬሽኑ አሳውቋል።