አቡበከር ናስር ብሔራዊ ቡድኑን ይቀላቀል ይሆን ?

አቡበከር ናስር ብሔራዊ ቡድኑን ይቀላቀል ይሆን ?

በቅርቡ ለብሔራዊ ቡድን ጥሪ የተደረሰው አቡበከር ናስር ቡድኑን ይቀላቀል ይሆን የሚለውን ጉዳይ ሶከር ኢትዮጵያ አጣርታለች።

በአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዚህ ወር አጋማሽ ላይ ለ2026 የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ከግብፅ እና ከጅቡቲ ጋር ለሚያደርጋቸው ጨዋታዎች ለ24 ተጫዋቾች ጥሪ መደረጉ ይታወቃል።

ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾችም ዛሬ ካዛንቺስ በሚገኘው ጁፒተር ሆቴል ከረፋዱ 5:00 ጀምሮ ሪፖርት በማድረግ ዝግጅት እንዲጀምሩ መገለፁም ይታወሳል። ጥሪ ከተደረገላቸው ተጫዋቾች መካከል ብቸኛው ከኢትዮጵያ ውጭ ጥሪ የተደረገለት ለደቡብ አፍሪካው ሱፐር ስፖርት ዩናይትድን የሚጫወተው አቡበከር ናስር ነው።

ይህን ተከትሎ ኢትዮጵያዊው አጥቂ አቡበከር ናስር ብሔራዊ ቡድኑን ይቀላቀላ ይሆን የሚለውን ጉዳይ ሶከር ኢትዮጵያ አጣርታለች። እንዳገኘችው መረጃ ከሆነ አቡበከር ትናንት ወደ አዲስ አበባ መግባቱን የሰማን ሲሆን ዛሬ አልያም ከሰሞኑን ብሔራዊ ቡድኑን እንደሚቀላቀል እና ዝግጅት እንደሚጀምር አውቀናል።