ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሱዳኑ አል ሂላል ጋር ለሚያደርገው የወዳጅነት ጨዋታ ዛሬ 08:30 ላይ ወደ ስፍራው ተጉዟል፡፡
ፈረሰኞቹ 20 ተጫዋቾችን ጨምሮ በአጠቃላይ 30 የልኡካን ቡድን ይዘው የተጓዙ ሲሆን በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ምርጫ ውስጥ የተካተቱት ሳላዲን ሰኢድ ፣ ምንተስኖት አዳነ ፣ አስቻለው ታመነ እና በሃይሉ አሰፋ አብረው ተጉዘዋል፡፡ በዚህም ምክንያት የመጀመርያዎቹ የብሄራዊ ቡድን ልምምዶች ያመልጣቸዋል፡፡
ለኢትዮ-ሱዳን ወዳጅነት እና ግንቦት 20 በአል ማድመቂያነት በቅዱስ ጊዮርጊስ እና አል ሂላል መካከል የሚደረገው ጨዋታ ሀሙስ ይካሄዳል፡፡