የሴካፋ ክለቦች ዋንጫ በአዘጋጅ እጦት ምክንያት ላይካሄድ ይችላል

የምስራቅ አፍሪካ ሃገራት እግርኳስ ማህበር (ሴካፋ) በመጪው ሐምሌ 9 በታንዛኒያዋ መዲና ሊያሰናደው ያሰበው የክለቦች ሻምፒዮናን ማስተናገድ እንደማይችል የታንዛኒያ እግርኳስ ፌድሬሽን ገልጿል፡፡

የምስራቅ አፍሪካ ሃገራት የውስጥ ሊጎችን በሚያሸንፉ ክለቦች መካከል የሚደረገው የሴካፋ ክለቦች ዋንጫ ዘንድሮ በአዘጋጅ ማጣት ምክንያት ላይካሄድ እንደሚችልም ተነግሯል፡፡

የታንዛኒያ እግርኳስ ፌድሬሽን የውድድሩ አዘጋጅ ሆኖ የቀረበ ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት ውድድሩን ማዘጋጀት እንደማይችል ተነግሯል፡፡ የክፍለ አሃጉሩ ብቸኛ ተወካይ በመሆን በኮንፌድሬሽን ካፕ የምድብ ጨዋታዎች ላይ የሚሳተፈው ያንግ አፍሪካንስ ውድድሩን በመጪው ክረምት የሚያደርግ መሆኑ እንደምክንያት ተጠቅሷል፡፡

ያንጋ የታንዛኒያ ሊግ እና የታንዛኒያ ዋንጫን ያሸነፈ ቢሆንም የኮንፌድሬሽን ካፕ የምድብ ጨዋታዎች የሚያደርግ በመሆኑ አይሳተፍም፡፡ በ2015 በተመሳሳይ መልኩ የሱዳኖቹ ኤል ሜሪክ እና አል ሂላል በነበረባቸው የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ከውድድሩ መቅረታቸው ይታወሳል፡፡

የታንዛኒያ እግርኳስ ፌድሬሽን ከሴካፋ ካጋሜ የክለቦች ዋንጫ ይልቅ ትኩረቱን በክረምት ወራት ለሚደረገው የካፍ ኮንፌድሬሽን ካፕ የምድብ ጨዋታዎች ትኩረቱን ሰጥቷል፡፡ በውድድሩ ላይ የታንዛኒያው ተወካይ ያንጋ መሳተፉም ከወዲሁ የፕሮግራም መጣበብ በማምጣቱ ውድድሩን ላለማዘጋጀት ወስኗል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *