ኢትዮጵያ ቡና በጎንደሩ የደጋፊዎች ጉዳት ዙርያ መግለጫ ሰጥቷል

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 21ኛ ሳምንት ዳሽን ቢራ ከኢትዮጵያ ቡና ባደረጉት ጨዋታ የተፈጠረውን የደጋፊዎች ጉዳት እና መሰል ተያያዥ ጉዳዮች አስመልክቶ ኢትዮጵያ ቡና ዛሬ በደሳለኝ ሆቴል መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ጨዋታውን ለመታደም በክለቡ የደጋፊዎች ማህበር በኩል ወደ ስፍራው ያቀኑ ደጋፊዎች ከዳሽን ቢራ ደጋፊዎች ጥቃት የተሰነዘረባቸው ሲሆን ጥቃቱን ተከትሎ በ33 (ረዳት ዳኛውን ጨምሮ) ሰዎች ላይ ከከባድ እስከቀላል ጉዳቶች እንደደረሰ ክለቡ በመግለጫው አስታውቋል፡፡

ለጥቃቱ መንስኤ ነው ተብለው ከተፈረጁ ምክንያቶች መካከል አጥቂው ሳዲቅ ሴቾ በ65ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ከጨዋታ ውጪ ነው ለሚለው የምስል ማስረጃ ያቀረበ ሲሆን በዳሽን ቢራ በኩል በተሰጠው መግለጫም በእጅጉ ማዘኑን ኢትዮጵያ ቡና ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ቡና የቦርድ ሊቀመንበር መቶአለቃ ፈቃደ ማሞ በሰጡት አስተያየት የፀጥታ አጠባበቁን ተችተዋል፡፡ “ከዚህ ከጎንደር የዳሽን ጨዋታ ጋር አብረው ተያይዘው የሚሄዱ ሁለት ጉዳዮች አሉ፡፡ አንዱ ጉዳይ ይሄ ሁሉ ሰው መፈንከቱ ፣  መጎዳቱ ፣ አንዳንድ ሰዎችም እስካሁን ድረስ ከሆስፒታል እንዳልወጡ ማስረጃ በእጃችን አለ፡፡ የፀጥታ አጠባበቁ እጅግ በጣም ደካማ ነበር፡፡ ይህ ሁሉ ወንጀል ሲፈፀም አንድም ሰው በፀጥታ ሃይል አልተያዘም፡፡ ይህ በጣም ያሳዝናል፡፡

“ሁለተኛ ለዳሽን ቢራ እና ለአስተዳደሩ ከፍተኛ ከበሬታ አለን፡፡ የተሰጠው መግለጫ ግን እጅግ በጣም የወረደ እና ከችግሩ ለመሸሽ ተራ አሉባልታዎች የታዩበት ነው፡፡ ችግሩን በተመለከተ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን ጉዳዮን በአግባቡ መርምሮ ውሳኔ የሚሰጥበት አግባብ ይኖራል ብለን እንጠብቃለን፡፡ ከዛ በላይ ግን የዳሽን ቢራ አስተዳደር ራሱን ሊፈትሽ ይገባል የሚል አቋም አለን፡፡” ብለዋል፡፡

13244056_1019038214852694_3375596526697913378_o

የቡና ደጋፊዎች ዳሽን ቢራ ይወርዳል ፋሲል ከተማ ይወጣል ብለው መዘማራቸው ለጥቃቱ መንስኤ ነው ለሚለውም ሊቀመንበሩ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ “የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች ጎንደር የሄዱት ቡድናቸውን ለመደገፍ ነው፡፡ ማንንም ለመደገፍ አይደለም፡፡ ያሉት “ዳሽን ይወርዳል ፋሲል ይወጣል” ነው፡፡ ፋሲልም ዳሽንም የጎንደር ክለቦች ናቸው፡፡ ምርጫ የማድረግ መብት የኛ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ጥቃቱ ደርሷል ቢሉ በፍፁም ተቀባይነት የለውም፡፡”

ሁለት አቻ በተጠናቀቀው ጨዋታ ለበርካታ ደቂቃዎች ጨዋታው ተቋርጦ የተጀመረ ሲሆን ከጨዋታው መጠናቀቅ በኃላ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ከደረሰባቸው ጥቃት ራሳቸውን ለመከላከል ወደ ሜዳ ሲገቡ የሚያሳይ ምስል ክለቡ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ አሳይቷል፡፡ የደጋፊ ማህበሩ አመራሮች፣ የቡድን መሪው አቶ ሰይፈ እና የክለቡ የህክምና ባለሙያ ይስሃቅ ስለጠቅላላ ጉዳዮች አስተያጣቸውን ሰጥተዋል፡፡

PicsArt_1464379167492

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *