ሳላዲን ሰኢድ በጉዳት ከቡድኑ ውጪ ሆኗል

በ2017 የጋቦን አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ በመጪው ቅዳሜ ከሌሶቶ ብሄራዊ ቡድን ጋር ጨዋታ የሚያደርገው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ነገ ወደ ስፍራው ያመራል፡፡

አሰልጣኝ ገብረመድህን ሃይሌ 25 ተጫዋቾችን በመጥራት ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ዝግጅት ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን 7 ተጫዋቾች በመቀነስ ወደ ሌሶቶ ይዘዋቸው የሚጓዛቸውን ተጫዋቾች ከቆይታ በኋላ ይፋ ያደርጋሉ፡፡

ሳላዲን ሰኢድ በጉዳት ምክንያት ወደ ሌሶቶ እንደማይጓዙ ከተረጋገጡት መካከል አንዱ ሆኗል፡፡ ብሄራዊ ቡድኑ ዛሬ ረፋድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ባደረገው ጨዋታ በጉዳት አቋርጦ የወጣው ሳላዲን ጉዳቱ ሀርምስትሪንግ መሆኑ ሲታወቅ ለ15 ቀናት እረፍት እንደሚያስፈልገው በህክምና ባለሙያዎች እንደተነገረው አሁን እየተካሄደ ባለው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግሯል፡፡

ሳላዲን ሰኢድ የቡድኑ አምበል ተደርጎ በአሰልጣኝ ገብረመድህን ሃይሌ ተመርጦ የነበረ ቢሆንም በጉዳት ከቡድኑ ውጪ በመሆኑ በምትኩ ስዩም ተስፋዬ በአምበልነት ተመርጧል፡፡ ነገረ ግን ስዩም ተስፋዬ ከፓስፖርት ጋር በተያያዘ ጉዳይ የመጓዙ ጉዳይ አጠራጣሪ በመሆኑ በ3ኛ አምበልነት የተያዘው ጌታነህ ከበደ ቡድኑን ይመራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *