የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የሌሶቶ ጉዞውን ጀምሯል፡፡ ወደ ማሴሩ የሚጓዙ 18 ተጫዋቾችን ትላንት ያሳወቁት አሰልጣኝ ገብረመድህን ሃይሌ በተጠባባቂነት ይዘውት የነበረው ደስታ ዮሃንስን 19ኛ ተጫዋች አድርገው ወስደውታል፡፡
ደስታ ፓስፖርቱ በጊዜ ባለመጠናቀቁ እና የስዩም ጉዳይ ባለመለየቱ በተጠባባቂነት ተይዞ የቆየ ሲሆን የስዩም ጉዞ ባለመሳካቱ ምክንያት አሰልጣኙ የመስመር ተከላካዩን ክፍተት ለመድፈን በማሰብ ለፌዴሬሽኑ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት አብሮ ሊጓዝ ችሏል ፡፡
የሀዋሳ ከተማው የመስመር ተከላካይ መልካም የውድድር ጊዜ እያሳለፈ መሆኑኖ ተከትሎ ለመጀመርያ ጊዜ ለብሔራዊ ቡድን ጥሪ ከቀረበላቸው ተጨዋቾች አንዱ ሆኗል፡፡
በተያያዘ ዜና ስዩም ተስፋዬ የፓስፖርቱ ጉዳይ እስከ ዛሬ ጠዋት ተጠናቆ ከቡድኑ ጋር አብሮ ይጓዛልጠ ተብሎ ቢጠበቅም ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ ነገር ግን በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ ፓስፖርቱ የሚመጣ ከሆነ ዘይቶም ቢሆን ከዋልያዎቹ ጋር ሊቀላቀል እንደሚችል ስዩም ለሶከር ኢትዮዽያ ተናግሯል
” ፖስፖርት እንድሰጥ ተጠይቄ የነበረው ሆቴል እንደገባሁ ነበር፡፡ ኬንያ የሚገኘው ካናዳ ኤምባሲ ቪዛ ጠይቄ ስለነበር ከናይሮቢ በጊዜ ፓሰፖርቴን እንዲያስመጡልኝ ጠይቄ ነበር፡፡ ፌዴሬሽኑም ደብዳቤ የላከ ቢሆንም ምላሽ አልተገኘም፡፡ ጥረት እየተደረገ ነው ፤ ከተሳካ በዚህ ሁለት ቀን የማመራ ይሆናል” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡
ተጨማሪ ዜናዎች በብሄራዊ ቡድኑ ዙርያ
ወደ ሌሶቶ የሚያመሩ 18 ተጫዋቾች ታውቀዋል ፤ ጌታነህ ቡድኑን በአምበልነት ይመራል