በፊፋ ወርሃዊ ደረጃ ኢትዮጵያ 2 ደረጃዎችን አሽቆልቁላለች

አለም አቀፉ የእግርኳስ የበላይ አካል ፊፋ የጁን ወር የሃገራት ብሄራዊ ቡድኖች ደረጃን ይፋ አድርጓል፡፡

የሜይ ወር ላይ የተደረጉ ኢንተርናሽናል ጨዋታዎችን መሰረት አድርጎ በወጣው ደረጃ ኢትዮጵያ በቁልቁለት ጉዞዋ ቀጥላ 125ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡ ከአፍሪካ ሃገራት ደግሞ 39ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡

ያለፉትን ሁለት ወራት ምንም አይነት ኢንተርናሽናል ጨዋታ ያላደረገችው ኢትዮጵያ በሜይ ወር 123ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ከኢትዮጵያ ጋር በአንድ ምድብ የምትገኘው አልጄርያ አሁንም የአህጉሪቱ ቁንጮ መሆኗን ቀጥላለች፡፡ ሌሎቹ በምድባችን የሚገኙት ሌሶቶ እና ሲሸልስ155ኛ እና 180ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

አርጀንቲና የአለምን ደረጃ መምራቷን ስትቀጥል ቤልጅየም እና ኮሎምቢያ ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል፡፡


የአፍሪካ ደረጃ
(በቅንፍ የተቀመጠው የአለም  አቀፍ ደረጃቸው ነው)

1. አልጄርያ (32)

2. አይቮሪኮስት (36)

3. ጋና (37)

4. ሴኔጋል (41)

5. ግብፅ (45)

6. ቱኒዚያ (47)

7. ኬፕ ቬርዲ (49)

8. ዲሪ ኮንጎ (52)

9. ጊኒ (55)

10. ካሜሩን (58)

:

:

39. ኢትዮጵያ (125)

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *