በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ወደ ሌሶቶ አቅንቶ 2-1 ያሸነፈው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ ገብቷል፡፡
ዋልያዎቹ ዛሬ ጠዋት 12:00 ላይ ከማሴሩ የተነሱ ሲሆን ቀኑን በበረራ አሳልፈው ምሽት 2:30 ላይ አዲሰ አበባ ደርሰዋል፡፡
የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ጁነይዲ ባሻ እና የስራ አስፈፃሚ አባላትም ለቡድኑ አቀባበል አድርገዋል፡፡
ወደ ሌሶቶ ከተጓዘው የልኡካን ቡድን መካከል ጌታነህ ከበደ ከቡድኑ ጋር አብሮ ያልመጣ ሲሆን በዛው ወደ ክለቡ አምርቷል፡፡ ቀሪዎቹ ተጨዋቾቹ ከነገ ጀምሮ ለክለባቸው አገልግሎት ለመስጠት የሚያመሩ ይሆናል