የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 24ኛ ሳምንት ዛሬ ሲጀምር አዳማ ከተማ ወላይታ ድቻን በመርታት ሁለተኛ ደረጃውን አጠናክሯል፡፡ ታፈሰ ተስፋዬ ለከፍተኛ ግብ አግቢነት የሚያደርገውን ጉዞም አሳምሯል፡፡
በርካታ የሁለቱም ቡድኖች ደጋፊዎች በተገኙበት የተደረገውን ጨዋታ አዳማ ከተማ ከእንቅስቃሴ ብልጫ ጋር 3-1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
በ43ኛው ደቂቃ በጨዋታው ጥሩ ሲንቀሳቀስ የዋለው ሚካኤል ጆርጅ ከዮናታን የተሻገረለትን ኳስ በግንባሩ በመግጨት በግሩም ሁኔታ ግብ አስቆጥሮ ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል፡፡
ከእረፍት መልስ ሙባረክ ሽኩር በራሱ መረብ ላይ እንዲሁም ታፈሰ ተስፋዬ ባስቆጠሯቸው ግቦች አዳማ መሪነቱን ወደ 3 ማስፋት ችሏል፡፡
ከግቦቹ መቆጠር በኋላ የተሻለ መንቀሳቀስ የቻሉት ወላይታ ድቻዎች በአላዛር ፋሲካ አማካኝነት ግብ አስቆጥረው ወደ ጨዋታው ለመመለስ ጥረት ቢያደርጉም ሳይሳካላቸው ጨዋታው በአዳማ ከተማ 3-1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
ውጤቱ አዳማ ከተማ 2ኛ ደረጃውን እንዲያጠናክር ሲረዳው ለወላይታ ድቻ ከ15 ጨዋታ በኋላ የመጀመርያ ሽንፈት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
በዛሬው ጨዋታ አንድ ግብ ያስቆጠረው አንጋፋው አጥቂ ታፈሰ ተስፋዬ የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ሰንጠረዡን በ14 ግቦች መምራቱን ቀጥሏል፡፡ ታፈሰ ዘንድሮ በከፍተኛ ግብ አግቢነት ካጠናቀቀ በፕሪሚየር ሊጉ ታሪክ ለ4 ጊዜያት ከፍተኛ ግብ አግቢነት ክብርን ያገኘ የመጀመሪያው ተጫዋች ይሆናል፡፡
የደረጃ ሰንጠረዥ
ከፍተኛ ግብ አግቢዎች
ቀጣይ የ21ኛ ሳምንት ጨዋታዎች
እሁድ ሰኔ 12 ቀን 2008
09፡00 ደደቢት ከ ሲዳማ ቡና (አአ ስታድየም)
11፡30 መከላከያ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (አአ ስታድየም)
ሰኞ ሰኔ 13 ቀን 2008
09፡00 አርባምንጭ ከተማ ከ ሀዋሳ ከተማ (አርባምንጭ)
09:00 ኤሌክትሪክ ከ ሀዲያ ሆሳዕና (አአ ስታድየም)
10፡00 ኢትዮጵያ ቡና ከ ድሬዳዋ ከተማ (አበበ ቢቂላ-ዝግ ስታድየም)
11፡30 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ዳሽን ቢራ (አአ ስታድየም)