” የስኬታችን ምስጢር አንድነታችን እና ዲሲፕሊን ነው ” አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ

ቅዱስ ጊዮርጊስ በዛሬው እለት ዳሽን ቢራን ማሸነፉን ተከትሎ የሊጉን ዋንጫ 2 ጨዋታ እየቀረው ማሸነፉን አረጋግጧል፡፡

ከጨዋታው በኋላ አስተያየታቸውን የሰጡት የቅዱስ ጊዮርጊሱ ረዳት አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ ሻምፒዮንታቸውን በማረጋገጣቸው ደስታ እንደተሰማቸው ተናግረዋል፡፡

” እንደ ቡድኔ እና እንደራሴ የለፋንበት ዋንጫ ነው። የለፋንበትን ዋንጫ በጥሩ ሁኔታ መውሰዳችንን አረጋግጠናል። በጣም ደስተኛ ነኝ። ” ብለዋል አክለውም ለቅዱስ ጊዮርጊስ አባላት እና ደጋፊዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

” ለቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎችና ለተጫዋቾች እንዲሁም አባላት ይህን 13ኛ ዋንጫ ቤታችን ስላስገባን እንኳን ደስ አላችሁ እንድትሉልኝ እፈልጋለሁ። ”

አሰልጣኝ ዘሪሁን ለቅዱስ ጊዮርጊስ ስኬታማነት አንድነት እና የስራ ዲሲፕሊን የድላቸው ምስጢር እንደሆነ ያምናሉ፡፡

” ስኬታችን አንድነታችን እና በጥሩ ዲሲፕሊን እያንዳንዱን ጨዋታ ተጫውተን ውጤት ይዘን መውጣታችን ያመጣው ነው። ትልቁ የስኬታችን ሚስጥር ይህ ነው። ” ሲሉ አጠቃለዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *