የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በስፖርታዊ ጨዋነት ጉድለት ምክንያት ኢትዮጵያ ቡና ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር በ25ኛው ሳምንት የሚያደርገው ጨዋታ ተሰርዞ ለሀዲያ ሆሳዕና ፎርፌ ለመስጠት ወስኖ የነበረ ቢሆንም የክለቡ ይግባኝ ተቀባይነት አግኝቶ ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴው ውሳኔን ሽሯል፡፡
ፌዴሬሽኑ ይፋ ያደረገው ደብዳቤ ይህንን ይመስላል፡-
*የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ውሳኔ ሰለማሳወቅ፡-*
*በአዲስ አበባ ስታድየም የኢትዮጵያ ቡና እና ሃዋሳ ከነማ እግር ኳስ ቡድኖች ሰኔ 3/2008 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታቸውን በካሄዱበት ወቅት የተከሰተውን የሰፖርታዊ ጨዋነት መጓደል አስመልክቶ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዲስፕሊን ኮሚቴ ሰኔ 6 ቀን 2008 ዓ.ም በተራ ቁጥር 3 የተወሰነውና የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ አንድ ጨዋታ እንዳይጫወት የተላለፈው ውሳኔ በፌዴሬሽኑ ይግባኝ ሰሚ ኮሜቴ የተሻረ በመሆኑ ፤ የሃዲያ ሆሳእና እና የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለቦች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ በወጣው የውድድር ፕሮግራም መሰረት የሚቀጥል መሆኑን እንገልጻለን፡፡ ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ ዝርዝር ውሳኔው እንደደረሰን እናሳውቃለን፡፡
*የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን