የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ከጎ-ቴዲ ስፖርት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የ2008 የፉትሳል ውድድር ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሷል፡፡
ስምንት ክለቦችን በሁለት ምድቦች በመክፈል የተጀመረው ይህ ውድድር የምድብ ሁለት የመጨረሻ ጨዋታዎች ረቡዕ በብሄራዊ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ተከናውኖ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ያለፉ ቡድኖች ታውቀዋል፡፡
የደረጃ ሰንጠረዦቹ ይህንን ይመስላሉ፡-
ምድብ ሀ
1. ቲጂ እና ጓደኞቹ 3 – 7 – 5
2. ሊና ሆቴል 3 – 1 – 5
——–
3. ኪምብሪያ ኢትዮጵያ 3 – 0 – 3
4. አበበ ቢቂላ 3 – (-8) 1
ምድብ ለ
ጂኬ ኢትዮጵያ- 3 – 9 – 9
ኢኤስኤፍ – 3 -10 – 6
—————
ብሉቤል- 3 -(-8) – 0
አሴጋ ፉትሳል – 3 – (-11) – 0
የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች
ቅዳሜ ሰኔ 18
7፡30 ጂኬ ኢትዮጵያ ከ ሊና ሆቴል
8፡30 ቲጂና ከ ኢኤስኤፍ
ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን ቢኒያም አሰፋ ከኢኤስኤፍ በ18 ጎሎች ሲመራ ኤልሻዳይ ቤኩማ ከአሴጋ በ11 ጎሎች ይከተላል፡፡ ለሚ ኢታና ከቲጂና ጓደኞቹ በ10 ጎሎች ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
ውድድሩን ያዘጋጀው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የፉትሳል ኮሚቴ የውድድሩ የመዝጊያ ስነ-ስርዓት የፊታችን እሁድ ሰኔ 19 ከረፋዱ 4 ሰዓት ጀምሮ በደማቅ ሁኔታ እንደሚከናወን አስታውቋዋል፡፡